🇺🇳🇸🇩 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ በሱዳን የተገደሉ ሦስት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ሰራተኞች ግድያ እንዲመረመር ጠየቁ
የዓለም የምግብ ፕሮግራም ሐሙስ እለት በተደረገ የአየር ድብደባ ሶስት ሰራተኞቹ መገደላቸውን በትናንታው ዕለት አስታውቋል።
🗣 "ዋና ጸሃፊው ታህሳስ 9 ቀን በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት ያርቡስ በሚገኘው የድርጅቱ የመስክ ጽህፈት ቤት ላይ በደረሰው በአየር ጥቃት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሶስት ሰራተኞች በመገደላቸው መደንገጣቸውን ” የአንቶኒዮ ጉቴሬስ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ትናንት ተናግረዋል። “ዋና ጸሐፊው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በእርዳታ ሰራተኞች እና ተቋማት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ሁሉ አውግዘዋል። ጥልቅ ምርመራ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል” ብለዋል።
ክስተቱ የሱዳን ግጭት በሚሊዮን በሚቆጠሩ ድጋፍ በሚሹ ሰዎችን እና ሕይወት አድን እርዳታ ለማድረስ በሚሞክሩ የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች ላይ እያሳደረ ያለውን "ውድመት መጨመሩን" ያሳያል ሲል መግለጫው አክሏል።
በሱዳን ከጎርጎሮሳውያኑ ሚያዚያ 2023 ጀምሮ በሱዳን ጦር ኃይሎች እና በወታደራዊው ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል ግጭት እየተካሄደ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት እንደገለጸው፤ ግጭቱ ከ20,000 በላይ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ መሰረትም የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሚሊዮን ተሻግሯል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉 @sputnik_ethiopia