🇲🇿 🌀 በሞዛምቢክ ፤ በሳይሎን ቺዶ አውሎ ነፋስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 73 ደርሷል፣ ከ540 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል
በካቦ ዴልጋዶ እና ናምፑላ ግዛቶች ላይ የደረሰው አውሎ ነፋስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በማፈናቀል እና ወሳኝ የሆኑ መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል ሲል የሀገሪቱ ብሔራዊ አደጋ እና የአደጋ መከላከል ኢኒስቲትዩት ዛሬ አስታውቋል።
መንግስት ከ1,300 በላይ ሰዎችን የሚያስተናግዱ የአስቸኳይ ጊዜ መጠለያዎችን አቋቁሟል፤ ፕሬዝዳንት ፊሊፔ ኒዩሲም ለተጎጂዎች ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።
የጉዳት ግምገማው በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትን፣ የአምልኮ ቦታዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን እና የዓሣ ማጥመጃ ጀልባዎችን ያወደመ ወይም በከፍተኛ ሁኔታ መጉዳቱን ያሳያል። በትምህርት ላይ የደረሰው ተፅእኖው ደግሞ 15,429 ተማሪዎች እና 224 መምህራን ላይ ተፅእኖ እንደሚያደርስ ተዘግቧል።
የሰብዓዊ እርዳታ እየተሰጠ ቢሆንም በአካባቢው ባለሥልጣናት መሠረት በአደጋው የተጎዱትን 182,000 የሚገመቱ ግለሰቦች ለመርዳት ተጨማሪ ገንዘብ በአስቸኳይ ያስፈልጋል ሲሉ ባለስልጣናት ገልጸዋል። አውሎ ነፋሱ አልፏል፤ ሆኖም ከፍተኛ ሙቀት እንደሚኖር ይጠበቃል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉 @sputnik_ethiopia