🇪🇹 አዲስ አበባን መነሻ ያደረጉ አራት ፈጣን መንገዶችን ለመግንባት የአዋጭነት ጥናት እየተደረገ መሆኑ ታወቀ
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ፤ የሀገሪቱን መንገዶች ግንኙነት የማሳደግ አላማ ያለው እና የሀገሪቷንን ኢኮኖሚ ልማት የሚያሳድጉ አራት አዳዲስ የፍጥነት መንገዶችን ለማስገንባት የአዋጭነት ጥናት በመካሄድ ላይ መሆኑን አስታወቀ።
በባለስልጣኑ የኢንጂነሪንግ ግዢ ዳይሬክተር የሆኑት ፍሬው በቀለ እንዳሉት ለመገንባት የታቀደው ፈጣን መንገድ መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ጅማ፣ ደሴ፣ ደብረ ማርቆስ እና ነቀምትን ያገናኛል።
ለመሰራት እቅድ የተያዘባቸው መንገዶች በተራሮች እና ከፍተኛ ከፍታ ባለባቸው ክልሎች የሚገነቡ በመሆናቸው ከፍተኛ የሆነ ቁፋሮን ጨምሮ የተለያዩ አይነት ተግዳሮቶች ስለሚያጋጥሟቸው በቂ የሆነ የገንዘብ በጀት ያስፈልጋቸዋል ተብሏል። በዚህም ባለስልጣኑ የመንግስት እና የግል ዘርፍ አጋርነት ሞዴልን በመከተል ግንባታውን እንደሚያከናውን ገልጿል። በተለይም የአዲስ አበባ ጅማ እና የአዲስ አበባ ደብረማርቆስ ፈጣን መንገድ ሞዴል ፕሮጀክትን ለማፀድቅ በፋይናንስ ሚኒስቴር ስር ለሚገኘው የመንግስት እና የግል ሴክተር አጋርነት ቦርድ እንዳቀረበ የመንግስት ሚዲያ ዘግቧል።
📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦
👉 APK ፋይል ሊንክ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉 @sputnik_ethiopia