አሁን ከመሼ ንፁሀንና እስረኞች በድሮን ተጨፈጨፉ
ኢትዮ 251 ሚዲያ
ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም
በሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ ጅሁር ከተማ ላይ በአገዛዙ በተፈጸመ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት ንፁሀን ተገደሉ፤ ከባድና ቀላል ቁስለኛም ሆኑ።
ጅሁር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ፖሊስ ጣቢያው ላይ በደረሰ በዚህ ጥቃት ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የጉዳቱ አሀዛዊ መረጃ ባይወጣም ቀላል የማይባል ጉዳት እንደደረሰ ግን የከተማዋ የመረጃ ምንጮች ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጠዋል።
የኢትዮ 251 ሚዲያ የመረጃው ምንጮች እንዳሉት በፖሊስ ጣቢያው የነበሩ የታሰሩ ሰዎችም ጭምር በድሮን ጥቃቱ ሳይሞቱ እንዳልቀሩ አንስተዋል።
ከ 2:30 እስከ 3:00 ባለው ጊዜ ውስጥ ጥቃቱ መፈፀሙን ያነሱት ምንጮቹ በትምህርት ቤቱና በፖሊስ ጣቢያው አካባቢ ያሉ ንፁሃን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል በርካቶችም ተገድለዋል፣ ወደ 10 የሚጠጉ ቁስለኞችም ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ ተመልክተናል ሲሉ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጠዋል።
https://t.me/tagayamhara