የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከታጋይ አምሓራ
በሁሉም የአማራ ግዛት ለሚገኙ ለህዝብ ነፃነት ታጋዮች ለፋኖ አመራሮችና አባላት፤
ለታላቁ የአማራ ህዝብ፤
ለጨለማው ኃይል ተቃዋሚ ለሆኑት ለሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፤
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!
የብርሃን ሁሉ ምንጭ የሆነው፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል ከድንግል ማርያም የተወለደው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ክርስቲያኖች በደስታና በሰላም የሚከበርበት ወቅት ነው። ታጋይ አምሓራ ይህንን ታላቅ በዓል ምክንያት በማድረግ በሁሉም የአማራ ግዛት ለሚገኙ የህዝባችን ነፃነት ተፋላሚ ለሆናችሁ የፋኖ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ለታላቁ የአማራ ህዝብና የአሁኑን የጨለማ ኃይል በብርቱ በመቃወም ለሚታገሉት ለመላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን በታላቅ አክብሮት ያስተላልፋል።
የገና በዓል የብርሃን መገለጫ፣ የጽድቅ ተስፋ፣ የጨለማ ኃይሎች ድል መንሻ አብሳሪ ነው። በዚህ ብሩህ በዓል የአሁኑን የጨለማ ኃይል በብርቱ በመፋለም የጀመርነውን የነፃነት ትግል አጠናክረን በመቀጠል የጭቆናውን ቀንበር ሰብረን በመጣል ብርሃን የሆነ የወደፊት ጊዜ እንደምንፈጥር ያለንን ጽኑ እምነት እናድሳለን። ልክ እንደ ልደቱ ብርሃን የጨለማውን ኃይል ድል እንደሚያደርግ ሁሉ የኛም ትግል የአብይ አህመድን የጨለማ አገዛዝ በመደምሰስ በመጨረሻ ድል እንደሚቀዳጅ አንጠራጠርም።
ውድ የፋኖ አመራሮችና አባላት! በያላችሁበት የትግል ግንባር የአብይ አህመድን የጨለማ አገዛዝ በመፋለም ለህዝባችሁ ነፃነት የምታደርጉት ተጋድሎ እጅግ የሚያኮራ ነው። ይህ የልደት በዓል ለትግላችሁ አዲስ ኃይልና ብርታት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። አንድነታችሁን አጠናክራችሁ፣ ጽናታችሁን አስታጥቃችሁ ለተጣለባችሁ የነፃነት አደራ ቃል በገባችሁት መሰረት እንድትወጡ እናሳስባለን።
የተከበርከው የአማራ ህዝብ! ይህ የገና በዓል የደስታና የሰላም ብቻ ሳይሆን ለረጅም ዘመናት የናፈቅነውን ነፃነትና ከዚህ የጨለማ አገዛዝ ጋር ያለንን ትግል በተሻለ የምናቀጣጥልበት ወቅትና የስኬት ጊዜ እንዲሆንልን እንመኛለን። ፋኖ ለዚህ የጨለማ አገዛዝ ብቸኛው ተስፋችሁ ነውና ድጋፋችንን እናጠናክር።
ውድ የአብይ አህመድን የጨለማ አገዛዝ የምትቃወሙ ኢትዮጵያውያን! የአማራ ህዝብ የሚያደርገው ትግል ለህልውና፣ ለፍትህ፣ ለእኩልነት፣ ለአንድነትና ከጨለማ ለመውጣት ያለመ በመሆኑ ለሁላችንም የሚጠቅም ትግል ነው። በዚህ የገና በዓል መንፈስ ለእውነትና ለብርሃን በመቆም ትግላችንን እንድትደግፉና እንድትተባበሩን እንጠይቃለን።
በመጨረሻም ለወገን ኃይል በበዓል ምክንያት መዘናጋት እንዳይኖር ማስታወስ እንወዳለን።
መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ!
ድል ለአማራ ህዝብ!
ታጋይ አምሓራ