ይሄው ነው!
እስክንድር ነጋን እስከ አሁኗ ጽሑፍ ድረስ አልተቸንም። ይህ ብዙ ጊዜ "መሃል ላይ አትንጣለሉ፣ እውነቷን እውነት መሰሏን ሐሰት በሉ እንጂ!" እንድንባል አስችሎናል። እንደ ታጋይ አምሓራ በተቻለን መጠን ትኩረታችንን ጠላት ላይ ለማድረግ ወስነን ነው ስንንቀሳቀስ የቆየነው። የጠላትን ፕሮፓጋንዳ ላለማጠናከርም ነው የውስጥ ጉዳያችንን ለሌሎች ለኞች ትተን የከረምን። ለዚህም ነው እስክንድርንና ሌሎችንም ዝም ብለን ያየናቸው። ለዚህ ጉዳይማ ብዙ አክቲቪስቶች፣ ብዙ ሚዲያዎች እና ገፆች አሉን። አሁን ግን የውስጥ ባንዳንና ትግል ጠላፊን እንዲሁ እያየን ዝም ማለት የምንችልበት ጊዜ አይደለምና ለከባዱ ጉዳይ ታጥቀን ተነስተናል።
እናም በስተመጨረሻ እስክንድር ድርድርም ይባል ውይይት ወደዚያ ገብቷል። ይሄው ነው። እኛ ግን ከአገዛዙ ጋር ድርድርም ሆነ ውይይት ፍፁም የማይታሰብና በሰማዕታት አደራ መረማመድ ነው ብለን እናምናለን።
የአማራ ህዝብ ትግል ፈታኝ ሁናቴዎችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል። በአንድ በኩል ህዝባችንን እየጨፈጨፈ፣ ሀብት ንብረቱን እያወደመ ያለው አገዛዝ አለ። በሌላ በኩል ደግሞ የትግሉን መንፈስ ለማዳከም የሚጥሩ የውስጥ ባንዳዎችና ትግል ጠላፊዎች አሉ። እነዚህ አካላት ሆን ብለው ትኩረታችንን ወደ ጎን በማዞር ትግሉን ለማደናቀፍ ይጥራሉ።
እስክንድር ነጋ ያደረገው እንቅስቃሴ የትግሉን መሰረት የመሸረሽርና ለጠላት እጅ የመስጠት ነው። በእርግጥ መሸርሸር ባይችልም! ሆኖም በዛ ቀጠና ይህ ድርጊት በሰማዕታት ደም የተገነባውን ትግል አደጋ ላይ ይጥላል። ከዚህ በኋላ ዝም ማለት አይቻልም። ጊዜው የውሸት መጋረጃውን ገልጦ እውነቱን የምንጋፈጥበት ነው። በውስጣችን ያለውን ክህደት አውጥተን በመጣል ለትግሉ ስኬት መስራት አለብን።
ለእኛ የትግሉ አላማ ግልፅ ነው። እሱም የአማራን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ እና ነፃነቱን ማስከበር ነው። ይህን አላማ ለማሳካት አላማችንን የሚጋራ ታክቲካል እንዲሁም ስትራቴጂካል ወዳጅ ማፍራት የግድ ይለናል። እያጠፋን ካለ ስብስብ ጋር ግን ምንም ዓይነት ውይይት ሊኖረን አይችልም። አንደራደርም! ትግላችን በሰማዕታት ደም የፀናና በፍፁም የማይደራደር ነው።
ይህ የለውጥና የእርምት ጊዜ ነው! የትግሉ አካል የሆኑ ሁሉ ይህን እውነታ ተረድተው ለትግሉ ስኬት መረባረብ አለባቸው። ጀርባችንን ለጠላት ሰጥተን በውስጣችን ያሉ ባንዳዎችንና ከዳተኞችን እያየን ዝም የምንልበት ጊዜ አብቅቷል። አሁን ጊዜው እርምጃ የምንወስድበትና ትግላችንን የምናጠናክርበት ነው። በቃ ይሄው ነው!
ታጋይ አምሓራ

ነፃነት በትግል እንጂ በልመና አይገኝም!