የፋኖ ግዙፍ ኃይል - አለመማከል
ፋኖነት የጀግንነት መንፈስን የሚያነሳሳ፣ የነፃነት ጥሪን የሚያስተጋባ ልዩ እሴት ነው! ፋኖ ለእኛ ለአማራዎች የኩራታችን ምንጭ ነው። አሁን ላይ ፋኖ ከ80 በላይ ግዙፍ ክፍለ ጦሮች ያሉት፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በጽናትና በጀግንነት የታነጸ ኃይል ነው። ይህ ቁጥር በራሱ የሚናገር ነው፤ ይሄ ሁሉ ክፍለ ጦር የተደራጀው በአመት ከምናምን ብቻ መሆኑ ደግሞ እጅግ አስደናቂ ያደርገዋል። ይህ ሁሉ ኃይል በአንድ ዓመት ከምናምን ውስጥ መገንባቱ አስደናቂ ብቻ ሳይሆን ታሪካዊም ነው። ...