ክሪፕቶ ከረንሲን በኢትዮጵያ መተግበር የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ተገለጸ
ከወረቀት እና የሳንቲም ገንዘብ በተጨማሪ የዲጂታል ገንዘቦች የክፍያና ኢንቨስትመንት አማራጭ እየሆኑ እንዳሉ ይገለፃል፡፡
ሀገራት ከእነዚህ መገበያያ አማራጮች ክሪፕቶከረንሲ (ምናባዊ ገንዘብ) በመባል የሚታወቀውን በህጋዊ መንገድ በግብይት ስርዓቱ በስፋት ጥቅም ላይ እያዋሉት ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያም ምናባዊው የዲጂታል መገበያያ በስፋት ገበያ ላይ እየዋለ በመሆኑ እንዴት መቆጣጠር ይቻላል የሚል ጥያቄ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መነሳቱ የሚታወስ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ በሰጡት ምላሽ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ክሪፕቶ ከረንሲን እንደ መገበያያ መጠቀም የተፈቀደ እንዳልሆነ ቢጠቅሱም፤ የዓለም የንግድ ስርዓት ተለዋዋጭ እንደመሆኑ ባንኩ በሒደት መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላልም ነው ያሉት፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ደረጄ ፍቃዱ አለም ወደዚህ የመገበያያ ስርዓት እየተቀየረ ከመጣ ኢትዮጵያም ተግባራዊ ማድረጓ የማይቀር ነው ብለዋል፡፡
በሌሎች ሀገራትም ሆነ በሀገራችንም የሚጠቀሙ መኖራቸውን እና ጠቀሜታ ያለው መሆኑን፤ እንዲሁም የሚፈጥረው ተፅዕኖ ቢኖርም አጣጥሞ ማስኬድ እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡
ከቁጥጥር አንፃር የሚነሱ መመሪያዎችም ሆነ ህጎች እንዲሁም የአሰራር ስርዓቶች ቴክኖሎጂ እንደመሆኑ ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ እየታየ ጥናት ተደርጎ ህግም ሆነ መመሪያ የሚወጣበትን ሂደት መፍጠር እንደሚቻል አመላክተዋል፡፡
ይህንን ሃሳብ የሚቃረኑት ሌላኛው የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ እዮብ አዳሙ ኢትዮጵያ አሁን ላይ የምናብ መገበያያውን ልትጠቀም የምትችልበት አስቻይ ሁኔታ እንደሌለ ይገልፃሉ፡፡
ሀገሪቱ ያላት የፋይናስ ስርዓት ጠንካራ ባልሆነበት ሁኔታ ትግበራ ውስጥ ቢገባ ጉዳቱ የሚያመዝን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በምክርቤቱም በህግ የታገደው ለዚህ የሚመጥን ሲስተም ባለመዛርጋቱ እና መቆጣጠር ስለማይቻል ነው ብለው እንደሚያምኑም ሃሳባቸውን ገልፀዋል፡፡
ክሪፕቶ ከረንሲን በስፋት ለመገበያያነት የሚያውሉ ሀገራት ቁጥር እየጨመረ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete