ወደ መቶ ብር ከፍ ያለው የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት የተለየ ለውጥ ያመጣል ተብሎ አይጠበቅም ተባለ
የዩኒቨርሲቲዎች በጀት 100 ብር ሆነ ማለት ድሮ ተማሪዎች ሲመገቡ ከነበረበት የምግብ አይነት የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት አይደለም ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የዩኒቨርስቲዎች የምግብ በጀት በቀን ከ22 ብር ወደ 100 ብር መሻሻሉን ተከትሎ፤ ከሰሞኑ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች የምግብ ተመኑ ሲያድግ በተቃራኒው ግን የሚቀርበው የምግብ አይነትና መጠን ያነሰ በመሆኑ ቅሬታቸውን እያቀረቡ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ አሐዱም ይሄንን የተማሪዎች ቅሬታ በመያዝ ትምህርት ሚኒስቴርን አነጋግሯል።
በዚህም በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶ/ር ሰሎሞን አብርሃ በሰጡት ምላሽ፤ የምግብ በጀቱ 100 ብር ሆነ ማለት የግድ የተለየ ለውጥ ይመጣል ማለት እንዳልሆነ ገልፀው፣ "የምግብ አይነቱም ሙሉ ለሙሉ አስደናቂ በሆነ መልኩ ይቀየራል ማለት አይደለም፣ ሊቀየርም አይችልም" ሲሉ ገልጸዋል።
ድሮውንም ተማሪዎች በተመደበላቸው 22 ብር ብቻ ሲመገቡ እንዳልቆዩ የሚገልጹት ዶ/ር ሰሎሞን፤ "ከፌዴራል መንግሥት የሚመደበው 22 ብር አነስተኛ መሆኑ ስለሚታወቅ ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው አካሄድ ሲያስተካክሉ ቆይተዋል" ብለዋል።
አሐዱም "የትምህርት ሚኒስቴር ያደረገው ማሻሻያ በቂ ነው ወይ? አሁን ካለው የገበያ ሁኔታ ጋርስ ተመጣጣኝ ነው?" ሲል ዩኒቨርስቲዎችን ጠይቋል።
የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነ የትምህርት ሚኒስቴር ለተማሪዎች የቀን ምግብ 22 ብር ቢመደብ፤ ከዛ በላይ ወጪ እንደበረው እና ተቋማቱ ለሌላ ሥራ የሚያገኙትን ገንዘብ ለምገባ የሚያውሉበት ሁናቴ መኖሩን ገልጸዋል።
"ዩንቨርስቲዎች በሚመደው 22 ብር ብቻ ተማሪዎቻቸውን አይመግቡም ነበር" ሲሉ ዶ/ር ሰሎሞን ያነሱትን ሃሳብ ተጋርተዋል።
"አሁን የተሻሻለው በጀት በተወሰነ ደረጃ ችግርን ይቀርፋል ተብሎ የሚጠብቅ ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የተደረገው ማሻሻያ ቁጥሩ ትልቅ ቢመስልም ቀድሞ ሲወጣ ከነበረው ወጪ አንጻር ሲታይ አሁንም ተጽዕኖ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
በአንጻሩ ሌላው አሐዱ ያነጋገራቸው የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ቶሎሶ ዳኒ፤ "አሁን ካለው የዋጋ ንረት አንጻር 22 ብር ተማሪዎችን መመገብ አይችልም ነበር፡፡ በተደረገው ጥናት መሰረት ወደ መቶ ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል" ያሉ ሲሆን፤ የተመደበው በተማሪ 100 ብር በቂ እንደሚሆንም ገልጸዋል።
በንጽጽር ሲታይ ቀድሞ ከነበረው 22 ብር ወደ መቶ ብር ከፍ መደረጉ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ መሆኑን አንስተዋል።
ዶ/ር ሰሎሞን የዩንቨርስቲዎቹን ፕሬዝዳንቶች ሃሳብ ሲያጠናክሩ፤ ዩኒቨርስቲዎች ከሚመደብላቸው የተለያየ በጀት እያዟዟሩ በቀን ከ80 እስከ 150 ብር በማውጣት ተማሪዎችን ሲመግቡ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ከመሻሻሉ በፊት አንድ እንጀራን እስከ 24 ብር ድረስ የሚገዛ ዩኒቨርስቲ እንደነበረ ጠቅሰው፤ "ድሮ ይመደብ የነበረው በጀት አንድ እንጀራ እንኳን በቅጡ የማይገዛ ነበር" ሲሉ አክለዋል።
በመሆኑም ይህ አካሄድ የዩኒቨርሲቲዎችን እንቅስቃሴ ስላስተጓጎለና የአሰራር ስርዓታቸው ላይም ችግር ስለፈጠረ፣ የምግብ ሜኑ ሲዘጋጅ ጥናት ተጠንቶ ሀገር አቀፍ የተማሪ ህብረት ተወካዮች ጭምር በአካል በተገኙበት የዩኒቨርሲቲዎች ምግብ ማሻሻያ መደረጉን ለአሐዱ ተናግረዋል።
አክለውም ተማሪዎች አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ማድረግ ያለባቸው የሚመደብላቸው በጀት በአግባቡ ለእነርሱ መድረሱን እና በቀን የመቶ ብሩ በጀት ተሰልቶ በሳምንት 700 ብር ወጪ መደረጉን፣ እንዲሁም ያንን ወጪ ታሳቢ ያደረገ ሜኑ መቅረብና አለመቅረቡን ማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች ህብረት አደረጃጀትም ሀላፊነት በመውሰድ በአግባቡ መከታተል እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete