ተማሪዎች አንስተዉት የነበረዉን ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ መልሻለሁ ሲል የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ገለፀ።
ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች የቀን የምግብ በጀትን ከ22 ብር ወደ 1መቶ ብር ከፍ እንዲል ካደረገ በኋላ አዲስ የምግብ ዝርዝር ይወጣል ተብሎ ለተማሪዎች መነገሩን የዩኒቨርስቲው የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ትካቦ ገ/ስላሴ ለኢትዮ ራዲዮ ጣቢያ ተናግረዋል።
በአዲሱ የምግብ ዝርዝር መሠረት በፊት ሁለት ዳቦ የነበረዉ የተማሪዎች ቁርስ ወደ አንድ ዳቦ ተቀነሶ በመቅረቡ፤ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ተቃውሞ ማንሳታቸውን ዶ/ር ትካቦ ነግረውናል።
በነበረዉ ግርግር መስታወቶችን ሲሰብሩ የነበሩ ተማሪዎች እንደነበሩም ነው የገለፁት።
ከተፈጠረው ግርግር በኋላ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሰዎች ህይወት አልፏል እየተባለ ሲወራ እንደነበርም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ዶ/ር ትካቦ ምንም የሞተ ሰዉ የለም የተማሪዎችን ጥያቄም በተቻለ መጠን ለመመለስ ሞክረናል አሁን ሙሉ ለሙሉ ወደ ትምህርት ተመልሰዋል ነው ያሉት።
የተማሪዎች ጥያቄ ቢመለስም፤ አሁንም ድረስ የመምህራን የደሞዝ ጥያቄ አልተመለሰም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ መንግስት በዚህ ጉዳይ ምላሽ ሊሰጠን ይገባል ብለዋል።
©ኢትዮ ሬድዮ
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete