ዳግም ምዝገባ እንዲያካሄዱ ጥሪ ከቀረበላቸው 102 ተቋማት መካከል 84 የሚሆኑት ምዝገባ ባለማካሄዳቸው እርምጃ እንደተወሰደባቸዉ ተገለጸ
በኢፌዴሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን በ2017 ዓ.ም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የትምህርት ስልጠና መስኮቻቸውን በአዲስ የፍቃድ አሰጣጥ ደረጃ መሠረት ለመገምገም እና እንደ ሀገር ወጥነት ያለው የፍቃድ አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዳግም ምዝገባ እየተካሄደ እንደሆነ ይታወቃል ።
ባለፈው አመት የካቲት ወር ላይ ባለድርሻ አካላትን በማወያየት መመሪያ እና ስታንዳርድ ፀድቆ ስራ ላይ የዋለ ሲሆን ፤ተቋማቱ በፀደቀው መመሪያ እና ስታንዳርድ እየሰሩ መሆናቸው ሲገመገም መቆየቱን የኢፌዴሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ማርታ አድማሱ ገልፀዋል።
ባለስልጣኑ በሚሰራው የማጣራት ሂደት ምዝገባውን እንዲያካሂዱ ጥሪ ከቀረበላቸው 102 ተቋማት 84 የሚሆኑት ምዝገባውን ባለማካሄዳቸው በገዛ ፍቃዳቸው ከመማር ማስተማር ስርዓቱ እንደወጡ ተናግረዋል፡፡
84 ተቋማት ከስርዓቱ አጠቃላይ ሪፖርታቸዉን በሚቀጥሉት 2 ሳምንታት ውስጥ ካላከናወኑ ፍቃዳቸው እንደሚነጠቅ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊዋ አክለዉ ተናግረዋል፡፡ በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ዉስጥ የመውጫ ፎርም መሙላት ግዴታቸዉ እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡
የመውጫ ፎርሙን ባልሞሉ ተቋማት ላይ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አመላክተዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete