ለ4ኛ ጊዜ በመሰጠት ላይ የሚገኘው የቅደመ-ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ዛሬ አራተኛ ቀኑ ላይ ደርሷል፡፡
ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ በ87 የፈተና ማዕከላት እየተሰጠ ሲሆን፤ 176,045 ተፈታኞች ፈተናውን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ከ18 ሺህ በላይ ተፈታኞች ፈተናውን እየወሰዱ እንደሚገኙ በዩኒቨርሲቲው የትምህርትና ምርምር ተቋም የፈተና ማዕከል ዳይሬክተር ብርሃኑ አበራ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
ባለፉት ሦስት ቀናት በነበረው የፈተና አሰጣጥ፤ ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ወደ ፈተና ጣቢያ ለመገባት ከሞከሩ ጥቂት ተማሪዎች እና አልፎ አልፎ የመብራት መቆራራጥ ከማገጠሙ በስተቀር ሌላ በዩኒቨርሲቲው ያጋጠመ ችግር አለመኖሩን ኃላፊው ለትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዴስክ ተናግረዋል፡፡
የቅደመ-ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ነገ ጥር 30/2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡
ምስል፦ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete