ፓቬል ዱሮቭ በፈረንሳይ ተጥሎበት የነበረው የጉዞ እግድ ለጊዜው ተነሳለት።
የቴሌግራም መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓቬል ዱሮቭ ከፈረንሳይ እንዳይወጣ ተጥሎበት የነበረው እግድ በጊዜያዊነት ተነስቶ ወጥቶ እንዲንቀሳቀስ ፈቃድ ተሰጥቶታል።
ፓቬል ዱሮቭ የዛሬ 6 ወር በፊት በፈረንሳይ ከፓሪስ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቡርጌት ኤርፖርት በቁጥጥር ስር ውሎ እንደነበር ይታወሳል።
የፈረንሳይ መንግስት ዱሮቭ ላይ ምርመራ የከፈተው በቴሌግራም መተግበሪያ ላይ የቁጥጥር ክፍተት አለ፤ መረጃ አይሰጥም፤ መተግበሪያው የወንጀል ድርጊቶች ይፈጸምበታል፤ የአደገኛ እፅ ዝውውር ይከናወንበታል በሚሉ መሰል ክሶች ነበር።
ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ካመራ በኋላም ፍርድ ቤቱ በ5 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 5.56 ሚሊዮን ዶላር ዋስ ተለቆ ጉዳዩን እንዲከታተል፤ ሆኖም ከፈረንሳይ እንዳይወጣ እግድ ጥሎበት ነበር። በሳምንት ሁለት ጊዜም ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት ተገልጾ ነበር።
ፓቬል ዱሮቭ ከፈረንሳይ መንግስት የመንቀሳቀስ መብት ከተሰጠው በኋላ ወደ ዱባይ ማቅናቱ ተነግሯል። ይሀም ከዚህ ቀደም ተቀዛቅዞ የነበረው ቴሌግራም ላይ መሰረት ያደረገው የቶን ዲጂታል ገንዘብ (TON) ባለፉት ቀናት መነቃቃት ታይቆበታል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete