በመዲናዋ በትምህርት ቤቶች አካባቢ አዋኪ ተግባራትን የሚፈፅሙ አካላት ቁጥር መቀነሱ ተገለጸ
በአዲስ አበባ ከተማ በግልም ይሁን በመንግሥት ትምህርት ቤቶች አካባቢ አዋኪ ተግባራትን የሚያከናውኑ አካላት ማለትም አልኮል ቤቶችን፣ ጫት ቤቶችን፣ ቁማር ቤቶችን እና ቪዲዮ ቤቶችን የሚከፍቱ አካላትን ለመቆጣጠር በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተከትሎ ተግባራቱ ላይ መቀነስ መታየቱ ተገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፤ ተቋማቸው ከንግድ ቢሮ፣ ከትምህርት ቢሮ፣ ከሰላም እና ፀጥታ ቢሮ፣ ከፖሊስ እንዲሁም ከምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን ጋር በመሆን የተለያዩ የኦፕሬሽን ሥራዎች በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለውም በዚህ የኦፕሬሽን ሥራ መሠረት አዋኪ ተግባር ሲፈጽሙ ተገኝተው የታሸጉ ተቋማት መኖራቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ተመልሰው ሲከፈቱ ዘርፋቸው እንዲቀይሩ የተደረጉ ስለመኖራቸውም ተናግረዋል። በተጨማሪም የንግድ ፈቃዳቸውን እንዲመልሱ የተደረጉ አካላት እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡
አሐዱም "አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች የንግድ ተቋማት መሀል ሊባሉ በሚችሉ ቦታዎች ላይ እንደመገኘታቸው ተቋማቱን ለመቆጣጠር ፈታኝ አይሆንም ወይ?" ሲል ዋና ሥራ አስኪያጁን ጠይቋል፡፡
"አብዛኛው ጥቆማ የሚመጣው ከማህበረሰቡ ነው" ያሉት ሻለቃ ዘሪሁን፤ "ከሕዝቡ የሚደበቅ ነገር ስለማይኖር ለሥራው አስተዋፅኦ ያደርጋል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የመማር ማስተማሩን ሥራ የሚረብሽ ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት ጉዳት የሚያስከትሉት ከኅብረተሰቡ የወጡትን ታዳጊዎች ላይ እንደመሆኑ፤ ሁሉም 'ያገባኛል' የሚል ስሜት ድርጊቱን ሊከላከል ይገባል ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከቀናቶች በፊት በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች አቅራቢያ 9 መቶ 66 አዋኪ ድርጊቶች መገኘታቸውን የገለጸ ሲሆን፤ በድርጊት ላይ ተሳትፈው በተገኙ 1 ሺሕ 163 ተቋማት ላይ የማሸግ እና ዘርፍ ቀይረው እንዲሰሩ የማድረግ እርምጃ መወሰዱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
በድርጊቱ ከተሳተፉ ተቋማት መካከል ከፍተኛ ቁጥር የያዙት ጫት በማስቃም እና ሺሻ በማስጨስ ተግባር ላይ የተሰማሩ ተቋማት መሆናቸውንም ቢሮው አመላክቷል።
ምንጭ፡ አሐዱ ራዲዮ
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete