የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የተከታታይ ጤና ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና (CPD) ዕውቅና ሰጪ ተቋም ሆኖ በድጋሜ ፈቃድ አጊኝቷል።
ካምፓሱ የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ አቅራቢዎች እና የስልጠና ኮርሶች ዕውቅና ሰጪ ተቋም (CPD Accreditor) ሆኖ እንዲያገለግል በድጋሜ ዕውቅና ከጤና ሚኒስቴር ማግኘቱን አሳውቋል።
በዚህም ካምፓሱ ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት የሚያስችለው ሲሆን፤ ፈቃዱ ለሦስት ዓመት የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።
በኢትዮጵያ ተከታታይ የጤና ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና Continuing Professional Development (CPD) የሚሰጡ ከ250 በላይ ተቋማት እንዳሉ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡