💥የተኩላውና የግመሉ ወግ
*******'' የወንዙ ውሃ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው። ተኩላው በዚህ በኩል፣ ግመል በዝያ ማዶ ቆመው ይተያያሉ። ተኩላው ለግመል ጠራውና ማውራት ጀመሩ፦
ተኩላ; ውሃውን ተሻግረህ ነው እንዴ የወጣኸው?
ግመል; አዎን።
ተኩላ; ጥልቀቱ ምን ያህል ነው?
ግመል; እስከ ጉልበት ይደርሳል።
ተኩላው ራመድ…ራመድ እያለ ወንዙ ውስጥ ዘው ብሎ ይገባል። ገና እንደ ገባ ውሃው ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሮት ግራና ቀኝ ያናውጠው ጀመር። ብቻ ግን እንደምንም እየተንፈራፈረ ዳር ላይ ወዳለ ድንጋይ ዘልቆ ከመስመጥ ተረፈ።
እንደምንም ራሱን ካረጋጋ በኋላ ወደ ግመሉ ዞሮ
"እስከ ጉልበት ነው የሚደርሰው" አላልከኝም? ብሎ ሲጮኽበት
ግመሉም ረጋ ብሎ
“አዎን እስከ ጉልበቴ ነው የሚደርሰው!” አለው።"
ትምህርት ውሰድ!
በጉዳይህ ላይ የምታማክረው
1ኛ, ታማኝና አላህን የሚፈራ
2ኛ, ፍላጎትህና ሁኔታህን ሊረዳህ የሚችል ሰው መሆን አለበት።
ያገኘኸውን ሁሉ የምታማክርና የሁሉንም ተሞክሮ ለመተግበር የምትጥር ከሆንክ ግን ምን አልባትም ልትወጣው በማትችለው ነገር ሰምጠህ ልትቀር ትችላለህ።
ምክንያቱም፦
👉ሁሉም የሚመክርህ
🔹በሚያውቀውና
🔸ራሱ በሞከረው ልክ ነው!
@tewihd