ፈገግተኛው ጀናዛ
****
(ምን ብታይ ይሆን እንዲህ ፈገግ ያልከው)
ጌታዬ ሆይ! ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ ሠይፍ የሰላ
አድርግልኝ
መዲነቱል ሙነወራ ውስጥ ጀናዛ በማጠብ ሥራ ላይ የተሠማራ አንድ ግለሠብ በሬሳ አጠባ ወቅት ከገጠሙት ድንቅ ነገሮች መካከል አንዱን እንዲህ ሲል ይተርክልን ይዟል…
"ተክለ ሰውነቱ ከሲታ ሲበዛ የቀጨጨ አካሉ በተበጫጨቀ ልብስ የተሸፈነ ካገኘ በልቶ ካጣም ባዶ ሆዱን የሚያድር የአላህ ባርያ። ለሊት ለተሀጁድ ቆሞ የጌታውን ቁርአን እያነበነበ የሚያነጋ። ከሰዎች አይቀላቀልም ብቸኝነት የህይወት ጌጡ ናት። በተበጫጨቀ ጨርቅ የተሸፈነ ጀናዛውን ወደ ማጠቢያ ክፍሉ ይዘነው ገባን በተዘረጋው የጀናዛ ማጠቢያ እንጨት ላይ አስተኝተን ልብሱን አወለቅንለት።
ጆሯችን መልካም ይሰማ ዘንድ በማሰብ ቁርአን በስፒከር ከፍ አድርገን ከፍተን ማጠብ ጀመርን።
ነፍሴ በእጄ በሆነችው ጌታ እምላለሁ ጀናዛው የቁርአን አንቀፆቹን ሲሰማ ፈገግ አለ ከፈገግታው የተነሳ ጥርሶቹ ተከፍተው ድዶቹ ይታዩ ጀመር።
ቁርአኑን ስንዘጋው የተከፈቱት ነጫጭ ጥርሶቹ ይከደናሉ የቁርአኑን ድምፅ ከፍ ስናደርገው
ፈገግታና ሳቅ ከፊቱ ላይ ይታያል። በግርምት ተውጠን የሱን መልካም ኻቲማ እንዲወፍቀን አላህን እየተማፀንን አጥበን ጨረስን" ይሉናል
የታሪካችን አቅራቢ።
ገጠመኙን እንዲህ በማለት ቀጠሉት "ከተቀበረ ከአስራ ሁለት አመታት በኋላ የመቃብሩ ስፍራ ለልማት ተፈለገና ተለዋጭ ቦታ ተሰጠን
በቅርብ ጊዜ የሞቱትን አፅማቸውን አውጥተን ወደ አዲሱ የመቃብር ስፍራ ወሰድን። ከቀናት በኋላ ተጠራንና ወደቦታው አቀናን ከአንድ ጉድጓድ አጠገብ ስራውን ያቆመ አንድ ዶዘር ወዳለበት አካባቢ ስንጠጋ ደስ የሚል ጠረን
ይሸተን ጀመር ወላሂ ከፈኑ እንኳ አልበሰበሰም ሰውነቱም አልተቀየረም ከሰአታት በፊት የተቀበረ
አዲስ ጀናዛ ነበር የሚመስለው አፈር አካሉን መብላትን እንቢ አለች ቁርአንን ታቅፎ የኖረን ሰውነት ለመብላት እንዴትስ ያስችላታል?! ከፈኑን
ስንገልጠው ያ ቁርአን ሲሰማ የሚንቀሳቀሰው ጀናዛ ነበር"
«የውመል ቂያማ ለቁርአን ባልደረባ አንብብ ደረጃውንም ከፍ ብለህ ውጣ ያንተ ማረፊያ የመጨረሻ አንቀፅ ቀርተህ በቆምክበት ስፍራ ላይ ነው ይባላል»
እውነተኛ ታሪክ እንጂ ልቦለድ አይደለም
አንብቦ ለሌላ ባካፈለ ሰው ላይ ሁሉ የአላህ እዝነት ይስፈንበት
https://t.me/tewihd