🫴ራትክሊፍ እና አሞሪም ተገናኝተው ነበር !
አዲሱ የክለባችን አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እና ሰር ጂም ራትክሊፍ ዩናይትድ አሰልጣኙን ከመሾሙ አንድ ሳምንት በፊት በአካል ተገናኝተው ነበር።
ከራትክሊፍ በተጨማሪ ሰር ዴቭ ብሬይልስፎርድ ሌላኛው ከሩበን አሞሪም ጋር ለንግግር የተቀመጠው ሰው እንደነበር ተገልጿል።
ድርድሩ የተደረገው ዩናይትድ በዩሮፓ ሊጉ በወቅቱ አሰልጣኝ እየተመራ ከፌኔርባቼ ጋር በተጫወተበት ሳምንት ነው።
ክለቡ ጨዋታ እየኖረው ድርድሩ መካሄዱ ዳን አሽዎርዝን አለማስደሰቱ እና ይህ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ላይ ሴራ እንደመጠንሰስ ነው ብለው አምነው እንደነበር ተመላክቷል።
ራትክሊፍ እና ብሬይልስፎርድ ወደ ሊዝበን አቅንተው ከአሞሪም ጋር በተነጋገሩበት ወቅት በአሰልጣኙ ተደንቀው እንደነበርም ተነግሯል።
ሆኖም በወቅቱ ግንኙነት ዳን አሽዎርዝ ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ ወደ ዩናይትድ እንዲመጣ ባለመፈለጉ ወደ ሊዝበን ለማምራት ፍቃደኛ እንዳልነበር እና በድርድሩም አለመገኘቱ ተዘግቧል።
ይህም በወቅቱ ሰር ጂም ራትክሊፍን ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ ከቷቸው የነበር ሲሆን ከዚያ ጊዜ በኋላም በሁለቱ ሰዎች የነበረው ግንኙነት እጅግ መቀዝቀዙ ተገልጿል።
ዳን አሽዎርዝ ኤሪክ ቴንሀግ ሲሰናበቱ ከኤዲ ሀው ወይም ከጋሬዝ ሳውዝጌት አንዱ ወደ ዩናይትድ እንዲመጡ ፍላጎት ነበረው ተብሏል።
ዘገባው የ ዘ አትሌቲክሱ ላውሪ ዊትሁዌል ነው ።
👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMk8VGf4F/
#Manchesterunited