የኔ አያት አንድ ቀን ቤተክርስቲያን ሄደው ተመለሱ
"ምነው እማማ አልኋቸው" ከፍቷቸዋል
"ኧረ እንደው ይኸ ፈጣሪ እሚባል ነገር" አሉ
"እንዴት" አልኳቸው
"አሁን እዛ አባ ሲያስተምሩ እሳት ውስጥ ይከታል አቃጠለን ሲባል በረዶ ውስጥ ኧረ በረደን ሲባል እሳት ውስጥ እሱም ስራ ፈቶ እኛንም አንገላቶ ማን ፍጠረን አለው" አሉኝ
አንድ ነገር ተረዳሁ ካልተማሩት አያቴ ጭንቅላት ውስጥ የሚፈልቀው ሀሳብ እኛ በመፅሀፍ ስላቀረብነው እንጅ በጣም ትልቅ ነገር ነው።
የኔ አምላክ አሪፍ ነው
ጋሽ ስብሀት እንደሚሉት ሰርቶ ሰርቶ መጥቶ አይቶን "አይ እነዚህ ልጆች አልተመለሱም" ብሎ ሚሄድ ነው ሚመስለኝ እንጅ እቺ ኢምንት ለሆነች ህይወት ሰባ ሰማንያ ለማትሞላ እድሜ እድሜ ልክ እሳት ውስጥ ሲከት አያቴ እንዳሉት በረዶ ውስጥ ሲያመላልስ ሚኖር አምላክ ይኖራል ብየ አላምንም!
ግን ከዛ በላይ አንድ ነገር አለ እግዚአብሄር በአምሳሉ ፈጠረን እንላለን እንጅ እንጅ እኛ ነን በአምሳላችን የፈጠርነው ክፉ ከሆንን እግዚአብሄር ክፉ ነው ደግ ከሆንን ደግሞ ደግ አምላክ ይሆናል
የኔ አምላክ እኔ ደግ ስለሆንኩ ደግ ነው
:-አለማየሁ ገላጋይ