ጆከር #2
.
.
ትናንት አየሁት።
አታምኑኝም ከቁጥር አንዱ #የተሻለ_ሆኖ_አግኝቼዋለሁ። ለየት ለማለት ያደረግኩት ጥረት የለም!
.
.
ብዙ ግዜ ቁጥር ሁለት ፊልም አይሳካም። እንኳን ከአንዱ ሊሻል የመጀመርያው በልጦት ቁጭ ይላል። expectation Kills innovation እንዲል።
joker 2 ያልተወደደበት ልክ ያስደነግጣል። ቁጥሮች ልጥቀስ! Rotten tomatoes የተባለ የተመልካች rating መሰብሰብያ ላይ ክፍል አንዱ 68% ተወዳጅነት ሲያገኝ ቁጥር ሁለቱ ግን 32% 😮
.
ዳይሬክተሩ Todd Philips ቁጥር ሁለትን በማሳመር የሚታወቅ ነበር። ወላ ፊልምን እንዳማረበት ሶስት ክፍል ያዘልቃል። the hangover ምስክሬ ነው።
.
ጆከር ቁ.2 በተመልካች አለመወደዱን ሳይ ልወደው እንደምችል ገምቼ ነበረ። ጣመኝ ፣ አልጣመኝ የምትል የዘመኔን የደቦ ምላስ አላምናትምና።
.
ለምን ተወዳጅ መሆን ቸገረው የሚለውን ለማብራራት የዳይሬክተሩን(Todd philips) intention በተለያዩ አቅጣጫዎች ልጠርጥር..
.
.
#Scape_goat
.
Scape goat የሚባል የኦሪት ስርአት እንደፊልም ሴራ ተጠቅሟል!
scape goat ማለት በኦሪት ለመሰዋእት የሚቀርብ እንስሳ ነው። infact ሁለት ናቸው። የማሳበቢያ ፊየል እና የመሰዋዕቱ በግ። የመሰዋቱ በግ ከታረደ በሗላ ለፈጣሪ ስጋው ይቀርባል።
.
ፊየሉስ? ፊየሉ አናት ላይ ካህን እጁን ይጭን እና የህዝቡን ሁሉ ሀጢአት ወደሱ እንዲሔድ ይለምናል። እንደተላለፈበት ሲያምን ከከተማ አስወጥቶ ይለቀዋል። ማን እንዲበላው ነው ብለን ነገር ብንፈልግ የምናገኘው መልስ አውሬ ይሆናል። በኦሪት ለፈጣሪና ለአውሬ መሰዋዕት ይቀርብ ነበር። wird ነው አይደል ስርአቱ? አንተ የማታቀርብ መስሎህ ማለት ነው። ጆከር ላይ ታየዋለህ ለማን እያቀረብክ እንደሆነ!!!
.
አየህ..አሪፍ ተቀባይ ሰጪው እየሰጠው እንደሆነ እንዳያውቅ የሚያደርግ ነው ይባላል። የሳኮፓዞች የወል በሀሪ።
.
scape goat በየቤቱ ይገኛል። black sheep ይሉታል በቤተሰብ ደረጃ ሲወርድ። በመልክ እና በቅልጥፍና የልጆችን attention ወደራሱ የሳበ ልጅ ለሆን ይችላል። አካል ጉዳት ኖሮበት የቤተሰቡ ሀብት እሱን ለማስታመም ያዋለ ልጅ/አባት/እናት ሊሆን ይችላል። ብቻ ለጉድለት ተጠቃሽ አካል አይጠፋም። ወይ ጠጥቶ እየገባ የሚማታ ገንዘብ የማይሰጥ አባት u name it.
.
ላጡት ነገር ተጠያቂ የመፈለግ ልምምድ ከቃኤል የጀመረ ነው። በዚህ የሚታማ አንድ ብሔረሰብ አውቃለሁ። በሁሉም ቤት አንድ ጠሽ አይጠፋም። ወላጆች ተስማምተው የቤቱን ጦስ ወደ አንድ ልጅ አስተላልፈው ቤታቸውን ያስባርካሉ።
.
ፒዲዲ
ዲዲ አለማቀፋዊ scape goat የሆነ ይመስለኛል። ዲዲ ቤት የተገኘው ያሁሉ ዘይት፤ የተያዙበት ድምጽና ምስሎች ጥፋተኛ ያደርጉታል። የሚዲያ ዘመቻው ግን አልገባኝም። ወላ ወንድ ሲከካ ድምጽ ብለው ለቀዋል። ፈቅዶ የተደረገ ሁላ ተገድጄ እያለ ነው። ለግል ጥፋታቸው ሳይቀር አብረውት የተነሱትን ፎቶ እየለጠፉ scape goat እያደረጉት ነው።
.
ጆከር ቁጥር አንድ ላይ ከፒዲዲ የባሰ ጥፋት ያደረሰ ግለሰብ ነበር። ጥፋቱን የመራው Artur ይባላል። የጎተም ከተማ ህዝብ hero አደረገው። ለምን? አንደኛ gottam city ዜጎቿን ልታኖራቸው አልቻለችም። በሙስና ተጨማልቃለች። ፍትህ እና ስራ እኩል ጠፍተዋል። ፖሊስና ሌባው አይለይም። የአዋቂዎች ቀልድ ቡሊ ሆኗል። ይሔ የተሰላቸ እና አንድ የሚያደርገው ያጣ ህዝብ hero እየፈለገ ነበር።
.
ህዝቡ ላለበት አዘቅት በድንገት የሚጠቁመው አገኘ። ጆከር! ባቡር ውስጥ የሚደበድቡትን 3 የሀብታም ልጆች ሲገድል ፊቱን ማስክ ተቀብቶ ነበር። ገዳዩ ከለበሰው ማስክ ጋር ሲብጠለጠል ቆይቶ በአንድ late night show ላይ በድንገት ሀላፊነቱን የሚወስድ ሰው ሆኖ ታየ። artur flake ይባላል። በቀጥታ የሚተላለፍ show ላይ የህዝቡን ብሶት ዘረዘረ። ሲከራከረው የነበረውን ጋዜጠኛውም እዛው ሾተው።
.
ከግድያው በሗላ በቋፍ የነበረው ህዝብ ግንፍል ብሎ ወጣ። ወዳገኘው ወረወረ። የከለከለች እንስት ተደፈረች። አጥቶ ያልገዛውን ወርቅ ዘርፎ ለበሰው። ከተማዋ ነደደች። ይህ የከፋውና ያኮረፈ ህዝብ Artur flakeን አንተ ነህ ነጻ አውጫችን ብሎ አነገሰው። ስሙም ተለውጦ ጆከር ተባለ።
..
የመጀመርያው ፊልም ያለቀው ጆከር ነግሶ Gotham city ስትነድ ነበረ።
.
ክፍል 2 የክፍል 1 antithesis ነው።
.
ክፍል 2 ሲጀምር Artur እስር ቤት ነው። ጠበቃው split ወይም Did አለብኝ በል ትለዋለች። "joker የሚባል ስብእና ነው የገደለው እኔ አይደለሁም" ቢል የስነልቦና ችግር ነው ተብሎ የአይምሮ ጤና ማገገሚያ ይገባል። ሊፈታም ይችላል። ሌዲጋጋ የምትሰራትም ካራክተር ተጠግታ አንተ Arthurን አይደለህም ጆከርን ነህ እያለች ታማልለዋለች። ወላ ፑሲ ትሰጠዋለች። ልጅ ጸንሼልሀለሁ ትለዋለች። ሁሉም ሰው ከማንነቱ ይገፋዋል። ፍርድ ቤት ቀርበው የሚመሰክሩበት በሙሉ Arturን እንዲጸየፈው የሚያደርጉ ናቸው። በወቅቱ በታሰረበት እስርቤት ያሉትም ፖሊሶች አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃት እያደረሱበት ማንነቱን እንዲጸየፍ አድርገውታል።
.
ተመልካቾቹ እኔና እናንተም ከበዳዮቹ እንድንቀላቀል ስውር ጥሪ ይደርሰናል።
.
ፊልሙ ከወጣ በሗላ ፊልሙን የተቹ ተመልካቾች ፊልሙ ውስጥ እንደገቡ አላወቁም። Artur ላይ በሚደርሰው ተደጋጋሚ ጉንተላ እየተበሳጨን እየነደደን እንድንሔድ ተደርገናል። አጸፋውን እየጠበቅን ሳለን.....(ፊልሙን ያላያችሁ እዚህ ጋር አቋርጣችሁ ብታዩት አሪፍ ነው መጨረሻውን ልናገር ስለሆነ)
.
የጎተም ህዝብ በሙሉ villain(ሙጅሪም) ከሆነ አክተሩ Artur ሊሆን ይገባ ነበር። እየጠበቅን ያለነው በቀል ነው። ነፍሳችን Arturን መሆን ታክቷታል። jokerን እየፈለገች ነው። በቀላችንን የሚበቀልልን ደማችንን የሚመልስልን እየጠበቅን ሳለ አርተር "split የለብኝም! ጆከር የሚባልም የለም። ሁሉንም ያደረግኩት እኔ ነኝ" ብሎ ሀላፊነቱን ወሰደ።
.
ከፍርድቤቱ ደጃፍ ሀጢአታቸውን በሙሉ መሪዎቻቸው ላይ የሚጭን ካህን እየጠበቁ ነው። ልትወገር እንደነበረችዋ ሴት በአንድነት የሚያስወግዱት ተጠያቂ አካል ፈልገዋል። scape goat ያልኳችሁ እሱን ነው። ጆከር ግን እራሱን scape Goat አድርጎ ቁጭ አለ።
.
ደነገጡ!
ወላ ተናደዱ።
jokerን ካላመጣህ አሉት። ያለበዚያ አንተኑ እንሰዋሀለን ነው።
.
(በአንድ ግጥሜ ላይ እንዲህ ብዬ ነበር...
.
#ቀድሞ_መውጣት_ክፉ_መሪ_መሆን_ወንጀል፡፡
ቀድሞ በመውጣቱ
ልክ ነው እያሉ የተከተሉቱ
ሰብረው ስለወጡ አንዴ ከበረቱ
መሪ ተጸጽቶ~
ተሳስቼ ነበር የጀመርነው መንገድ ወደ ሞት ያወርዳል!
ቢል
መንጋው ተጸጽቶ ለጀመረው መንገድ መሪውን ይሰዋል
#መገን! )
.
ፍርድቤቱን በቦንብ አፈንድተው Artur ን አዳኑት። የሱን አይነት አለባበስና ሜካፕ የተቀባ Joker በመኪና ይዞት እየሔደ