Repost 2022
ጥበብ ከጲላጦስ እስከ ቅፅ³ ድረስ the same chapter ነው ምን አልባት ምዕራፎችሁ ውስጥ የሚነሱት ሰዎችና አሳቦች ይለያዩ ይሆናል። ካልረሳውት ምዕራፎችሁ ሀሳብ ፡ እምነት : ሞት : ሴት : ውበት ነው።
ታድያ ከነዚህ ውስጥ "ውበት" የሚለው chapterን Define የሚያደርጉት ወንዶች ብቻ ናቸው። እና በስጨት ያደርገኛል በእውኑ አለም ስለ ውበት የሚጠበቡት ሴቶች ሆነው ሳለ ይህን ጥልቀት የሚተነትኑት ግን ወንዶች ናቸው። ከዛሬ 5-6 ወር በፊት መሸሸት ብሎ እኔም ከስራ ወደቤት እየገባው በነበረበት ሰዓት ከጀርባዬ ሁለት ሴቶች እያወጉ ነበር። በርግጥ "ሁለት ሴቶች ተቀምጠው ሲያወጉ ምንም የረባ ነገር አይወጣቸውም" እንዳለው ካህሊል ውይይታቸውን ንቄ አላለፍኩትም ነበር።
እያወሩ ነው አንዷ ሴት ተለቅ ያለች ወደ 30 ዓመት እድሜ የምትጠጋ ነች አንዷ ደግሞ የገጠር ንጹህ ታዳጊ ልጃገረች ነች። ታዳጊዋ ገና ከገጠር እንደመጣችና ብዙም ከተማውን እንዳለመደችው አነጋገሯ ያስታውቃል። Like "origin woman" አዳም ረታ ``በማህፀኗ ዓየር ያላስገባች ድፍን ሴት`` ነች ማለት ይቀላል። እኔ ከፊት ከፊት ስሄድ እነርሱም ከዋላዬ እየተከተሉ ያወጋሉ። ይህቺ የገጠር ንጹህ ሴት ተናዳ ታወራለች የምታወራው የወንድሟን የማብሸቂያ ስድብ እንዲያቆም ነግራው አለማቆሙን ነው።
ትልቋ ሴት ትጠይቃለች- "ቆይ ምን ልሁን ነው የምትይው?"
ልጅቷ-"በቃ አረጀሽ አስጠሊታ እየሆንሽ ነው ይለኛል"
"እና ምን ችግር አለው"
"እንዴ ደጋግሞ 'አረጀሽ አረጀሽ' ይላል አትበለኝ ስለው ደግሞ ይብስበታል"
-"ወይኔ እውነቱን እኮ ነው አረጀሽ በቃ"
ስትላት ታዳጊዋ የማጉረምረምና የመከፋት ድምፆችን አሰማች። ለምን ግን¿ 🤔
እላይ በኑሮ ተሰቅላለች የምትባለው ሴት እና ሁሉንም የተረዳች አዋቂ የምትባል ሴት አልያም ምንም የማታውቀው ንጹህ ሴት፤ አንድ የሚያደርጋቸው ፍርሃት ቢኖር የማርጀት ወይንም የውበት መርገፍ ፍርሃት ነው። ይሄ profile ሲደበዝዝ ውብ የሆኑ ነገሮች የማብቂያ ጊዜያቸው እንደደረሰ የማመን አባዜ ተጠናውቷቸዋል። Money Heist የተሰኘው Movie ላይ በርሊን የሚባለው ገፀባህሪ ለአንድ ያልጠነከረ አዕምሮ ላለው ወጣት ምክር ቢጤ ይወረውርበታል። ልጁ አብራው በምዘርፈው ሴት ፍቅር ክንፍ ብሏል። ወላ ከእርሷ ጋር አግብቶ ልጅ ወልዶ መኖር አላማው አድርጎታል። እና በሁለቱ መኃከል ያለው ነገር የእውነት እንደሆነ እና ልጆች እንደሚያፈሩ ለበርሊን ይነግረዋል። በርሊንም ያለው ይሄን ነው። ቃል በቃል ባይሆንም የማስታውሰውን ማለት የፈለገውን ነው የጻፍኩት።
`` ከእርሷ ጋር አንድ ላይ ሆናችሁ የመጀመርያ ልጃችሁን አርግዛ መጣው መጣው ብሏት ሆስፒታል አልጋ ላይ በህመም እያማጠች ሳለ የምታስበባቸው የተወሰኑ ነገሮች ቢኖሩ ህመሟን እና የእርጅና መንገድ ላይ እንደሆነች ብቻ ነው። ታድያ የሚመጣው ልጅ የደስታ እሳቤ ቢሆንም ከሁለት ጭን እንደወጣ ኒኩለር ነው። ሁለምንም ነገር ከነበር ወደአልነበር ይለውጠዋል። ምክንያቱም ከእንግዲህ እንደበፊቱ እሆናለው የልጄ አባትም በድሮ ፍቅሩ ይቀጥላል የሚለው አሳብ እንደማይሆን በመገንዘብ ባሏን የማጣት ቀሽም የመክሸፍ ስሜታዊ ሀሳብ ይከባታል!``
በመጨረሻም ውበት ምንድነው ብዬ መጠየቅ የምፈልገው ሴትን ልጅ ነው። ስለ ውበት ከሴት በላይ የሚጠበብ የለም እንዴት ላምጣው እና እንዴት ይዘቱን ሳይለቅ ለዓመታት ላቆየው የሚለው የማሰብ ሂደት ለሴት ልጅ የተሰጠ የእግዜር ሰይጣን ነው። ቅዱስነቱ በእድሜ የታጠረ እርኩሰት እንደማለት ነው።