ብዙ መጠሪያ ስሞች ያሉት ማይክ ታይሰን የሚሉት ቡጢኛ መቼስ ጉደኛ ሰው ነው። በጉብዝናው ዓመታት ከ400 ሚሊየን ዶላር በላይ ከስፖርቱ አግኝቷል። እንደ Rolls-Royce እና ፌራሪን የመሳሰሉ ከመቶ በላይ ውድ መኪኖች፣ ስድስት ቅንጡ ቤቶች፣ በርካታ የዳይመንድ ጌጣጌጦችን ሲሰበሰብ ኖረዋል። ለልብስ ብቻ ከሶስት ሚሊየን ዶላር በላይ ያወጣ እንደነበር ይነገራል።
ሲዝናና እና ሲገዛ ለነገ አይልም። ከጓደኞቼ ጋር ዎክ እያረኩ ድንገት ወደሆነ መዝናኛ ቦታ እንሂድ ሲሉኝ ለሰከንድ ሳላቅማማ ወዲያው አዲስ መኪና ገዝቼ ይዣቸው ሄዳለሁ ይላል።
ብራዘር እኔ እኮ ገንዘብ አጠፋለሁ..አይበረክትልኝም አትበል። ማይክ ታይሰን አለልህ። ይበትናል ቢባል እንኳ አይገልጸውም። የሚስቱን ገላ መታጠቢያ ገንዳ በተለየ ሁኔታ ለማሰራት ያወጣውን ብትሰማ ታብዳለህ። ለልደቷ ድግስ ብቻ ከ400K ዶላር በላይ አውጥቷል። [ያውም በእነሱ 80'ዎቹ ውስጥ]። በስፖርቱ እጅግ ስኬታማ ነበር። ከ56 ግጥሚያዎች ውስጥ 50ውን አሸንፈዋል። ያውም 44ቱን በዝረራ።
የጉብዝና ወራቱ ሲያልፉ ጡረታ ወጣ። ቁጭ ብሎ ጥሪቱን መብላት ጀመረ። ሱስ አጧጧፈ። ከዕፅ ጋር ተመቸቸ። ቁማር አስከተለ። ዝነኛው ቡጢኛ በአጭር ጊዜ ቀውስ ላይ ቀውስ እየጨመረ ተቃወሰ። በዚህ ላይ አስገድዶ የመድፈር ክስ እና እስር። የሃብቱ ተራራ በፍጥነት ተናደ። የገላ መታጠቢያን በወርቅ ያሰራላት ሚስቱ 9 ሚሊየን ዶላር ወስዳ ተሸበለለች። ተለየችው። ሌላ አገባ። እሷም ሃብቱን ተካፍላ እብስ አለች። ቀሪ ሃብቱን ቁማር እና መጠጥ ቤቶች ተከፋፈሉት። ጭራሽ መኪኖቹን እና ቤቶቹን በሙሉ በመሸጥ ወደ ዕዳ ገባ። 400 ሚሊየን ዶላሩ ጨርሶ ከ30 ሚሊየን በላይ ዕዳ ተሸካሚ ሆነ። በብድር የተገዘችን መኪና ይዞ ለማደሪያ ጓደኛው ቤት በጥገኝነት ገባ።
በወቅቱ በሰጠው አንድ ቃለመጠይቅ እንዲህ አለ
[ ለሰላምታ የሚጠይቀኝ ሰው አልነበረም። የሚፈልጉኝ በሙሉ አበዳሪዎቼ ናቸው። እራሴን ጠላሁ። በጥልቀት መውደቄን አየሁ። የባከነ ሕይወት መምረጤን ተረዳሁ። እንደምንም በምንም ዋጋ ዕዳዬን ከፍዬ ከሰው ዓይን ዞር ማለት..ከአሜሪካ መራቅ ፈልግኩ ]
ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ አዲስ ፀሐይ ወጣች።
ከሱስ አገገመ። ከቁማር እና ዕፅ ራቀ።
በተቋማት ታግዞ ዕዳውን ለመክፈል ዳግም ወደ ቦክሱ ሪንግ ተመለሰ። በተለያዩ ስፖንሰሮችም ታገዘ። ዕዳውንም መክፈል ቻለ። እንዳውም አሁን እስከ 10 ሚሊየን ዶላር የተጣራ ሃብት አፈራ።
እነሆ...
ዛሬ ንጋት በ58 ዓመቱ ከወጣቱ ጄክ ፓውል ጋር ዳግም ቡጢ ይጋጠማል። በዚህም ተጨማሪ ሚሊየን ዶላሮችን ይዝቃል። 70 ሺህ ተመልካች ፊት የሚደረገውን የቡጢ ግጥሚያ Netflix ለ280 ሚሊየን ደንበኞቹ በቀጥታ ያስተላልፋል።
እኔ ጠብ፣ ጠበኞች፣ ቡጢ እና ቡጢኞችም አይመቹኝም። ሰው እንዴት በድብድብ እንደሚዝናና አይገባኝም። ሞሐመድ አሊ በፖለቲካዊ ሃሳቦቹ እና በቀጥተኝነቱ ደስ ይለኛል። በርግጥ ታይሰንም ፖለቲካዊ እሳቤዎቹን በንቅሳቶቹ ይነግረናል። ብዙ ንቅሳቶች አሉት።
[ አርቱር አሼ: በቴኒስ የገነነ ጥቁር
Spike Lee: ነጮች በፊልሞቻቸው ያሳነሳቸውን ጥቁር አሜሪካዊንን በፊልሞቹ ለማቃናት የተጋ
.
.
ማኦ ዜዶንግ
ቼ ጉቫራ
ፊቱ ላይ የ{Maori} ጎሳ ታጋይነት ምልክት ]
እነዚህ ነቅሳቶቹ Political statement ናቸው።
የሆነ ሆኖ...
በዚህኛው ግጥሚያ ግምቴ ለወጣቱ Jake Paul ነው። በመካከላቸው የ30 ዓመት የዕድሜ ልዩነት አለ። ታይሰን ነገሩ ከከበደው ከዚህ ቀደም የሆሊፊልድን ጆሮ ነክሶ ደም በደም እንዳረገው ታሪክ እራሱን ልደግም ይችላል። በተረፈ ማይክ ታይሰን ወድቆ የመነሳት ተምሳሌት ነው።
-ፀሐፊ ጥላዬ ያሚ
-Source mereja