#Update
🔴 “ 100 ብር ከተበጀተ በኋላ ከቀረበልን ይልቅ የበፊቱ ምግብ ጥራት አለው ” - የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች
🔵 “ እንደ እውነቱ ከሆነ በ100 ብር በተሰጠው የምግብ ዝርዝር መሰረት ለማስተናገድ የማንችልበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው ” - ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች ከአዲሱ የምግብ ሜኑ ጋር በተያያዘ የምግብ ጥራት ፣ የኮስት ሸሪንግ ጉዳይ ለይ ቅሬታ እንዳላቸው በመግለጽ፣ የሚመለከታቸው አካላት መመሪያውን በድጋሚ እንዲያጤኑት ጠይቀዋል።
በአዲሱ የምግብ ሜኑ መሰረት ከቀረላቸው ምግብ ይልቅ የድሮው ጥራት እንደነበረው አስረድተው፣ ማስተካከያ ካልተደረገበት ትርፉ ከፍተኛ ኮስት ሸሪንግ/ የወጪ መጋራት እዳ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት በበኩሉ፣ ከምግብ ሜኑው ትግበራ ጋር በተያያዘ ቅሬታ እያቀረቡ ያሉት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሆኑ፣ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለዚህ ተጠቃሽ እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከደባርቅ ዩኒቨርቲ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አካልን ያነጋገረ ሲሆን፣ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጠተዋል።
ዩኒቨርሲቲው በሰጠው ማብራሪያ ምን አለ ?
" መንግስት የተማሪ በጀት ከ22 ነበር ወደ 100 ብር ማሳደጉ ይታወቃል። 22 ብር እያለ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውንም ሌላም በጀት አጣበው እየደጎሙ አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።
ከሌላ በጀት እየተነሳ፣ እየተዘዋወረ አገልግሎት ከመስጠት ለራሱ ወጥ የሆነ የመንግስትንም ያገናዘበ የሀገሪቱን አቅም ያገናዘበ፣ በምግብ ጥራት ሊመጥን የሚችል (አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር እንዴት እንዳጠናው ባናውቅም) ብር መድቧል።
በ100 ብር ምን መመገብ ይቻላል ? የምግብ ዓይነቱስ ምን ቢሆን ? ብሎ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ኮሚቴ ተዋቅሮ የአካባቢውን ግብዓት መሰረት ባደረገ አሰራር ዩኒቨርሲቲዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ብሎ ለአንድ ተማሪ ምን ያክል ምስር፣ ክክ፣ እንጀራ፣ ዳቦ ያስፈልጋል ብሎ የምግብ ዝርዝር ቋሚ በሆነ መልኩ አቅርቦልናል።
ለኛ የተሰጠን ስራ ግራሙን መቀየር አይደለም። ዝርዝሮቹ 10 ቢሆኑ (ለምሳሌ አዲስ አበባ፣ ደባርቅ፣ መቐለ፣ ደብረ ብርሃን የሚገኝ ሌላም) አንድ ላይሆን ስለሚችል ያን መሰረት አድርገን አገልግሎት እንሰጣለን ” ብሏል።
ስለተማሪዎቹ ቅሬታ ዩኒቨርሲቲው ምን አለ?
“ ተማሪዎች ‘በዚህ አንስማማም የተሰጠው የምግብ ዝርዝር የጥራት ችግር ያመጣል’ የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ነገር ግን ስራውን ከመጀመራችን ከ4 ቀን በፊት ከተማሪዎች ጋር ውይይት አድርገን መግባባት ላይ ደርሰን ነበር።
ተማሪዎቹ ጥያቄ ካላቸው በኀብረቶቻቸው አማካኝነት እንዲያቀርቡልን፣ እኛም ቀጥታ ከትምህርትና ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ጥያቄ ካለን በሰላማዊ መልኩ አቅርበን የተሻለ አገልግሎት መስጠት አለብን በማለት ተስማምተን ነው ወደ ስራ የገባነው።
ተማሪዎቹ ‘ምግቡ ድሮ 22 ብር እያለ የተሻለ የሚመስል ነገር ነበረው። ስለዚህ በጀቱ ሲጨምር የምግብ ጥራቱም በዛው ልክ መጨመር አለበት’ የሚል አመለካከት አላቸው።
እኛ ደግሞ የምግብ ጥራቱን የማንጨምርበት ምክንያት መጀመሪያም አሁን ከተመደበው በጀት እኩል/ አንዳንዴም እንደ ወቅቱ የገበያና የፀጥታ ሁኔታ እላፊ ሊሆን ይችላል እንጂ በ22 ብር ብቻ አልነበረም ሲመገቡ የነበረው።
ለምሳሌ ፦ ተማሪዎቻችንን ስንመግብ የነበረው እንጀራ በ23 ብር እየገዛን ነበር። ስለዚህ 22 ብር ብቻ በቂ አልነበረም። በተዘዋዋሪ ተማሪዎቻችን ይህን ያውቁታል። እንዲያው አመፅ ለማስነሳት ምክንያት ፈልገው ካልሆነ በስተቀር።
ሌላው ጥያቄያቸው ‘አሁን የተመደበው 100 ብር ቀጥታ ኮስት ሸሪንግ ላይ ነው የሚያርፈው’ የሚል ሲሆን፣ ይህ ከእኛ አቅም በላይ ነው። ስለዚህ ጥያቄውን ይዘን ለሚመለከተው አካል እናቀርባለን።
ነገር ግን መንግስት ‘የምግብን ኮስት ሸሪንግ ተማሪው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል’ ካለ አለ ነው። በተዘዋዋሪ 100ም ሆነ 1000 የተጠቀመውን ያክል ነው የሚከፍለው።
የተማሪዎቹ ጥያቄ ‘ከመጣው ዝርዝር አንፃር የምግብ ጥራቱ በጣም ያንሳል’ የሚል ስለሆነ የምግብ ጥራቱ ይጨምር ከተባለም፣ በእኛ ዩኒቨርሲቲ analysis ሰርተናል። ከዝርዝሩ ውስጥ በርበሬና የሻይ ቅመም አልተካተተም።
የበርበሬና የሻይ ቅመም እንኳን ሳናስገባ ራሱ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅቶ በሰጠን መመሪያ ዋጋ ሽንኩርት ፣ ዳቦ፣ እንጀራ፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ጨው የመሳሰሉትን ግብዓቶች ለአንድ ተማሪ የገዛንበትን ዋጋ ስንሰራው 115 ብር እስከ 120 ብር ይመጣል ስለዚህ ከተማሪው በላይ ለኛ ነው ጥያቄ የሆነብን።
አንደ እውነቱ ከሆነ በ100 ብር በተሰጠው የምግብ ዝርዝር መሰረት ለማስተናገድ የማንችልበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው።
ይህ ዋጋ የተሰራው አሁን ባለንበት የገበያ ሁኔታ ሲሆን፣ ነገ ሊጨምርም ይችላል። እንኳን ኦቨር ጥራት ተማሪዎች እንደሚጠይቁት ልናደርግ በ100 ብር አጣጥመን ስናስበው ጨረታ በሰጠናቸው ውል በያዝንባቸው ከ100 ብር በላይ ነው የሚመጣው። ይህን በሰነድ ማረጋገጥ ይቻላል።
ስለዚህ በ100 ብሯ ግዴታ አብቃቅተን ማስተናገድ ይጠበቅብናል። ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ዊዝድሮውም፣ ሌላም መረጃ አለ ያንን መሰረት አድርገን ኦዲት እናደርጋለን። በዚህ መሰረት ብሩን ከፍ እናደርጋለን ቁጥጥራችን ከፍ ይላል።
ለኛም አስጨናቂ ነው የሆነብን ተማሪው ‘አልፈልገውም’ ያለው የምግብ ዝርዝር ራሱ ከተሰጠን በጀት በላይ ነው። ስለዚህ የግንዛቤ ፈጠራዉ እንደ ሀገር አቀፍ አስተያየትም ስላልተሰጠበት ለኛ ፈተና የሆነብን ነገር ይሄ ነው።
ለጊዜው በድሮው የምግብ ዝርዝር ነው እየተጠቀምን ያለነው። እንደኛ ዩኒቨርስቲ ተጨባጭ ጥያቄ ‘አዲሱን አትጀምሩት በድሮው ይቀጥልልን’ የሚል ነው ከተማሪዎቹ የተነሳው።
ለዚህ ደግሞ የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች ለስራ ጉዳይ አዲስ አበባ ነው ያሉት ትምህርት ሚኒስቴር ጠርቷቸው። እናም ይህንን ጉዳይ ያነሱታል ብዬ አስባለሁ።
ይህ ጉዳይ በብዙ አቅጣጫ ቢታይ ዝም ተብሎ አንድ ወገን ላይ ብቻ ጣት የሚቀሰርበት አይደለም። አሁን ላይ ተማሪው የምግብ ጥራት ይልና ኮስት ሸሪንግንም ያነሳል።
‘የምከፍል ከሆነ የምግብ ጥራቱ መጨመር አለበት ነው’ ነጥቡ። እኛ ደግሞ በ100 ብር አስተናግዱ ሲባል እንደ ምግብ ዝርዝሩ 100 ብሩ አያሰራንም አይበቃንም እያልን ነው ያለነው ” ብሏል።
መፍትሄውን በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው ምን አለ ?
“መንግስት የሰጠው ሜኑ አለ። ተማሪዎች ጥያቄ ካላቸው በሰላማዊ መልኩ ከዩኒቨርሲቲው ማኔጅመን፣ ከተማሪዎች ኀብረት ጋር በመሆን ጥያቄ አቅርቦ መግባባት ላይ መድረስ ነው።
መግባባት ላይ ከተደረሰ ይህንንም ሊቀበሉ ይችላሉ። መንግስተም ኮንሲደር የሚያደርገው ነገር ሊኖር ይችላል። ስለዚህ የመንግስትን ሀሳብ በጉልበት ከመግፋት ተወያይቶ ጥያቄው ቢፈታ መልካም ነው።
ንብረት እያወደሙ፣ ትምህርት እያቋረጡ ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ በተወካዮቻቸው አማካኝተት ጥያቄያቸዌን አቅርበው ውይይት ይደረግበት ” ሲል አስገንዝቧል።
(የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችን አስተያዬትና የትምህርት ሚኒስቴርን ምላሽ ለማካተት የተደረገው ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን፣ ፈቃደኞች ከሆኑ በቀጣይ እናቀርባለን)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia