#ፋይዳ #NationalID
" ከፍርድ ቤት እና ከብሔራዊ ደኅንነት ጥያቄው ከዛ እስካልመጣ [የግል መረጃ] ለመንግስት የሥራ አስፈጻሚ አይሰጥም " - አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ
ኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራምን በይፋ ካስተዋወቀችበት ጀምሮ እስከ አሁን 12 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ተመዝግበዋል፤ እስካሁንም ይህንን አገልግሎት ከ50 በላይ ከሆኑ አገልግሎቶች ጋር የማስተሳሰር ሥራም ተሰርቷል።
ይህ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ መንግስት ከሚበጅተው በጀት በተጨማሪ ለተግባራዊነቱ ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ 300 ሚሊዮን ዶላር ብድር እንዲሁም 50 ሚሊዮን የሚሆን ድጋፍ አግኝታለች።
የፋይዳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ ኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ትግበራን ዘግይታ መጀመሯ ላይ ቢስማሙም በአንጻሩ ግን የተሻለ ቴክኖሎጂ እና ልዩ ልዩ እሳቤዎችን እንድታካትት ረድቷቷል ይላሉ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወሳኝ አገልግሎቶች ላይ በአስገዳጅነት ጭምር መቅረቡ የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ከፍ እንዳደረገው ይታመናል። አሁን ላይ በቀን ከ60ሺ ሰዎች በላይ የመመዝገብ አቅም መፈጠሩን ከፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃም ያመለክታል።
አሁን ካሉት የመመዝገቢያ ሳጥኖች ተጨማሪ በቅርቡ 3000 የሚያህል እንደሚጨመር ዋና ዳይሬክተሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ይህም የተመዝጋቢዎችን ቁጥር በዚህ ዓመት መጨረሻ ወደ 30 ሚሊዮን ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የጣት አሻራ የሰጡ ዜጎች ብዛት 33 ሚሊዮን፤ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያገኙ ዜጎች 5.6 ሚሊዮን በላይ እንደዮኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የባዮሜትሪክ ዳታን መሰረት ያደረገ የዲጂታል መታወቂያ ተግባራዊ ያደረጉ ሲሆን ለአብነትም ናይጄሪያ በዓለም ባንክ ድጋፍ ከ10 ዓመታት በላይ በፈጀው ጉዞዋ ከ107 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን መዝግባለች።
ሀገራት የባዮሜትሪክ መረጃዎችን ያካተተ ምዝገባ በሚያከናውኑበት ወቅት በመሰረታዊነት ሦስት ተግዳሮቶች ይገጥሟቸዋል። እነዚህም ከዜጎች ጋር ያለ የተግባቦት ክፍተት፤ የዲጂታል ክህሎት ማነስ እና የደኅንነት ጥያቄዎች ናቸው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከቤተሰቦቹ የተነሱ ጥያቄዎችን ሰብስቦ ምላሽ እንዲሰጥባቸው ለጽ/ቤቱ አቅርቧል።
በተለይም ከመሰረታዊ ዓላማ እና ከግል መረጃ ደኅንነት ጋር የተያያዙ፤ ከቤተሰቡ የተሰበሰቡ ጥያቄዎችን ለፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ ምላሽ እንዲሰጥባቸው አድርጓል።
የፋይዳ ዋና ዓላማው ምንድን ነው?
"ፋይዳ" ከሌሎች መታወቂያዎች ጋር ለንጽጽር የሚቀርብ እንዳልሆነ ዋና ሥራ አስኪያጁ ያስረዳሉ። ይህም ፋይዳ የተናበበ የዜጎች መረጃ በብሔራዊ ደረጃ እንዲኖር የሚያስችል መሰረተ ልማት እንደሆነ ነው የሚገልጹት።
አቶ ዮዳሄ፥ "ፋይዳ እንደ Social Security ቁጥር ነው" በማለትም አሁን ላይ ከሌሎች መታወቂያዎች ጋር የሚደረጉ ንጽጽሮች ይህን ካለመረዳት እንደሆነ ይጠቅሳሉ።
ሌሎች መታወቂያዎችንስ ይተካል ?
ፋይዳ፤ የነዋሪነት መታወቂያ ላይ ያለው መረጃ ከፖስፖርት መረጃ ጋር እንዲሁም ከጤና፤ ከፋይናንስ መሰል አገልገሎቶች ጋር ትስስር እንዲፈጠር የሚያስችል እንጂ ሌሎቹን የመተካት ዓላማ እንደሌለው ገልጸዋል። "ሲስተሞቹ እየተናበቡ ሲሄዱ ነው ብዙ ጥቅም ማግኘት የሚቻለው" ሲሉ ዋና ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል።
ለምን የደም አይነት አልተካተተም ?
የደም አይነትም ሆነ የእናት ስም በፋይዳ የዲጂታል መታወቂያ የማይሰበሰቡት ለሚሰጠው መረጃ ማረጋገጫ ማቅረብ አስቸጋሪ በመሆኑና ለሲስተሙ የተመጠነ መረጃ መውሰድ (Data Minimization) እንደ ስትራቴጂ በመያዙ መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
የሚሰበሰበው መረጃ የት ይቀመጣል ?
የዜጎች የግል መረጃ ከተሰበሰበ በኋላ ደኅንነቱ በተጠበቀ በብሔራዊ መረጃ ቋት እንደሚቀመጥ የገለጹት አቶ ዮዳሄ፥ የተቋማቸው ዋና ተልዕኮም ይሄንን ብዙ ሀብት የወጣበት መረጃ በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ እንዲሁም ከተጠቃሚ አካላት ጋር ማስተሳሰር እንደሆነ አስረድተዋል።
የዜጎች የግል መረጃ ለሦስተኛ ወገን ተላልፎ ይሰጣል ?
በርካቶች በስጋት የሚጠቅሱት አንዱ ዋነኛ ጉዳይ መረጃቸው ለሦስተኛ ወገን ተላልፎ ስለመሰጠቱ ነው። ለዚህ ጥያቄ አቶ ዮዳሄ ሲመልሱ "ከፍርድ ቤት እና ከብሔራዊ ደኅንነት ጥያቄው ከዛ እስካልመጣ [የግል መረጃ] ለመንግስት የሥራ አስፈጻሚ አይሰጥም" ብለዋል።
ከዚህ በላይ በአግባቡ ዲዛይን ካልተደረገ የግል መረጃን አደጋ ላይ የሚጥለው ብለው ያነሱት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከባለቤቱ ፈቃድ ውጪ እርስ በእርስ የሚያወሩ ከሆነ እንደሆነ አስረድተዋል።
ለዚህም በቅርቡ ላይ "Verify Fayda 2" የተሰኘ ሲስተም ማበልጸጋቸውን በመጥቀስ ለሁሉም የተለየ Token እንዲኖራቸውና የሚያስፈልጋቸውንና የተፈቀደላቸውን መረጃ ብቻ እንዲወስዱ የሚያስችልና ያለ መረጃ ባለቤቱ ፈቃድ ሁለት ተቋማት እርስ በእርስ መረጃ እንዳይቀያየሩ የሚያስችል እንደሆነ ጠቅሰዋል።
ፋይዳ ለምን አስገዳጅ ሆነ ?
አንዳንድ ተቋማት ፋይዳን ግዳጅ ሲያደርጉት አንዳንድ ተቋማት ደግሞ ሳይቀበሉ ሲቀሩ ይስተዋላል። ይህንን አስመልክቶ ጥያቄ የቀረበላቸው ዋና ሥራ አስኪያጁ "ፋይዳ ስላለኝ መኪና ልንዳ ማለት አትችልም፤ እንዲሁ ፖስፖርት ለማውጣት ሌሎች የሚያስፈልጉ ነገሮች አሉ" ሲሉ ፋይዳን አስገዳጅ የማድረግ እና ያለማድረግ ጉዳይ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ እንደሚወሰን ገልጸዋል።
ከሁሉም ነገር ጋር እንዲተሳሰር እንደማይጠበቅ የገለጹት አቶ ዮዳሄ ለዲጂታል ኢኮኖሚው ከሚጠቅሙ አገልግሎት ጋር በዋነኛነት እንደሚያያዝ አንስተዋል።
ለአብነትም በቅርቡ ሲም ካርድ ለማውጣት ፋይዳ በግዳጅነት እንደሚቀመጥ እንዲሁም በፖስፖርት እና በአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂዎች ላይ የፋይዳ ቁጥር እንደሚካተት አንስተዋል።
ፋይዳ በቀጣዩ ምርጫ ላይ አገልግሎት ላይ ይውላል ?
አቶ ዮዳሄ ምርጫ ቦርድ ሲስተም ቢኖራቸውና ትስስር መፍጠር ከተቻለ ተቋማቸው ዝግጁ መሆኑን ገልጸው " ለዩኒክነስ ያስፈልገናል ካሉ ቢያስተሳስሩት ደስ ይለናል . . . እንኳን እንደ ምርጫ ቦርድ አይነት ትልቅ የዲሞክራሲ ተቋም ጋር ቀርቶ ከፊንቴኮች ጋርም ትስስር ፈጥረናል" ሲሉ ምላሻቸውን አስቀምጠዋል።
📱 አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡትን ምላሾች ይመልከቱ https://youtu.be/b_X_LnM4cTA?feature=shared
@tikvahethiopia