" ነበሩ ፓስፖርት የአገልግሎት ጊዜው እስኪያበቃ ጥቅም ላይ መዋሉን ይቀጥላል " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
በኢትዮጵያ የተመረተ አዲስ ፓስፖርት ዛሬ ይፋ ሆኗል።
ፓስፖርቱ የግለሰቡን ባዮግራፊክ መረጃ ብቻ ሳይሆን የጣት ዐሻራ የያዘ የኤሌክትሮኒክስ ቺፕስ አለው ተብሏል።
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚመረተው ይህ ፓስፖርት፤ የቪዛ ገጾቹ የኢትዮጵያን መልክ የያዙ መሆናቸው ተጠቅሷል።
ይህም ከዚህ ቀደም በውጭ ሀገር አምራች ድርጅት እጅ የነበረውን ዲዛይን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሸፈን አድርጓል ተብሏል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በአዲስ የዘርጋው የኢ-ፓስፖርት ሲስተም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በጃፓኑ ቶፓን ሴኩሪቲ ኢትዮጵያ አ.ማ. አማካይነት የተሰራ ነው።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፤ ነበሩ ፓስፖርት የአገልግሎት ጊዜው እስኪያበቃ ጥቅም ላይ መዋሉን የሚቀጥል ሲሆን የዕድሳት ጊዜው ሲደርስ በኢ-ፓስፖርት ይተካል ተብሏል።
አገልግሎት መ/ቤቱ ፤ " 14 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈትም አገልግሎቱን ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቋል " ያለ ሲሆን " ከአንድ ነጥብ 5 ሚልየን በላይ ኢ-ፓስፖርት ታትሞ ተዘጋጅቷል " ሲል ገልጿል።
አዲሱ የኢ-ፓስፖርት በነበረው ዋጋ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እንደሚሆን የተነገረ ሲሆን ደንበኞች ባሉበት ፓስፖርታቸውን በፍጥነት ማግኘት እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል።
" አዲሱን ኢ-ፓስፖርት በሁለት ወር ከ10 ቀን ማግኘት ይቻላል " ሲል አገልግሎቱ አሳውቋል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊ ዳዊት ፥ " አዲሱ ኢ-ፓስፖርት እስከአሁን ኢትዮጵያ ካላት ፓስፖርት በአይነቱና በደረጃው እጅግ ከፍ ባለ ጥረት የተዘጋጀ የጉዞ ሰነድ ነው " ብለዋል።
#EPA
@tikvahethiopia