" በነገው ዕለት አንድ ቡድን ወደ ስፍራው ያቀናል " - አምባሳደር ነብያት ጌታቸው
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ ፤ በማይናማር ታግተው የነበሩ 246 ዜጎችን በቀጣይ ሳምንት ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ነው አሳውቀዋል።
" በማይናማር በከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለማስወጣት በቶኪዮ እና በኒውዴሊ ባሉ ኤምባሲዎች በኩል ሥራዎች እየተሠሩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" አሁን ላይ 246 ኢትዮጵያዊያን ከማይናማር ወጥተው ወደ ታይላንድ ደርሰዋል " ሲሉ ጠቅሰዋል።
" እነሱን ለመርዳትና የማጣራት ሥራ ለመሥራት በነገው ዕለት አንድ ቡድን ወደ ስፍራው ያቀናል " ብለዋል።
በተመሳሳይ በመካከለኛው ምስራቅ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለማስወጣት የሚደረገው ጥረት ቀጣይነት እንዳለውም ጠቁመዋል። #ኤፍኤምሲ
@tikvahethiopia