#Islam
ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዓ.ወ) ተከታዮች ብቻ የተሰጠችው ከሺህ ወራት በላጯ ሌሊት !
(በሴራን ታደሰ)
የኢስላም ሃይማኖት ምሁራን እንደሚሉት፥ ከነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዓ.ወ) መላክ አስቀድሞ በምድር ላይ ኖረው ያለፉ ሕዝቦች ዕድሜያቸው ረጅም ነበር፤ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ዓመታትን በሕይወት የመቆየት ዕድል ነበራቸው።
በአንፃሩ የነቢዩ (ሰ.ዓ.ወ) ተከታዮች ዕድሜ በአማካይ ከ60 እና ከ70 ዓመት የማይዘልና በጣም አጭር ነው። በመሆኑም የነቢዩ ተከታዮች በአምልኮም ሆነ በበጎ አድራጎት ተግባራት በሚያስመዘግቡት ምንዳ ከቀድሞዎቹ ሕዝቦች ጋር ተወዳዳሪ ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል አልነበራቸውም።
አላህም ይህን ሊያካክስላቸው ከረመዳን ሌሊቶች አንዷን በምርታማነቷ ከሺህ ወራት ጋር ተመጣጣኝ እንድትሆን አደረገላቸው። ይህች ሌሊት ለይለቱል ቀድር ወይም የመወሰኛዋ ሌሊት በመባል ትታወቃለች። የረመዳን ወርን ክብር ካላቁት ነገሮች አንዷም ይህችው ለይለቱል ቀድር ናት።
ነቢዩ (ሰ.ዓ.ወ) ለይለቱል ቀድርን ከመጨረሻዎቹ 10 የረመዳን ቀናት በተለይ ኢ-ተጋማሽ በሆኑት ውስጥ ተጠባብቃችሁ ፈልጓት ብለዋል። ይህም በረመዳን 21፣ 23፣ 25፣ 27፣ እና 29 መሆኑ ነው። አብዛኛዎቹ የሃይማኖቱ ምሁራን ወደ 27ኛዋ ሌሊት ቢያደሉም፣ለዚህ ቁርጥ ያለ ማስረጃ ወይም ማረጋገጫ የለም።
አላህ ሌሊቷ ተለይታ እንዳትታወቅ ያደረገበት የራሱ ምስጢር አለው ይላሉ የኢስላም ምሁራን። ምዕመናን ሌሊቷ የቷ እንደሆነች ለይተው ቢያውቁ ኖሮ፤ በዚያች ሌሊት ብቻ ሥርዓተ አምልኮን በመፈጸም ረመዳንን ላይጾሙ፣ ዓመቱን ሙሉ ፈጣሪያቸውን ላያመልኩ ይችሉ ነበር። ያ እንዳይሆን ለመከላከል አላህ ለይለቱል ቀድርን ድብቅ ሌሊት አደረጋት።
ለይለቱል ቀድር ከሌሎቹ ሌሊቶች የምትልቀው ቁርዓን የወረደባት እና የመወሰኛ ሌሊት በመሆኗ ነው። የምዕመናን ዓመታዊ ጉዳዮች አላህ ዘንድ ቀርበው ውሳኔ የሚያገኙት በዚህች ሌሊት ነው።በመሆኑም በዚህች ሌሊት ምዕመናን የአላህን ምህረት፣ ጸጋ እና ውዴታ ለማግኘት የአምልኮ ተግባራትን ከወትሮው በበለጠ ትጋት እና ትኩረት ያከናውናሉ።
በሌላ አባባል፥ በዚህች ሌሊት የሚከናወን አምልኮተ ሥርዓት ከረመዳን ዉጪ ለ1 ሺህ ወራት ወይም ለ83 ዓመት ከ3 ወር ከሚከናወነው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ምንዳን ያስገኛል።
በመሆኑም በዚህች ሌሊት ምዕመናን ሥርዓተ አምልኮን እና በጎ−ምግባራትን ከወትሮው በበለጠ መጠን እና ጥራት ያከናውናሉ፤ለአብነትም፥ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን ይከውናሉ፣ ቁርዓን ይቀራሉ፣ የሌሊት ሶላት ይሰግዳሉ፣ ዱዓ ያደርጋሉ (ፈጣሪያቸውን ይለምናሉ)። በዚህች ሌሊት ከሚደረጉ ተወዳጅ ዱዓዎች መካከልም፥ "አላህ ሆይ፥ አንተ ይቅር ባይ ነህ፤ ይቅር ማለትን ትወዳለህ፤ ይቅር በለን!" የሚለው ተጠቃሽ ነው።
Credit - Ethiopian Broadcasting Corporation (Seran Tadesse)
@tikvahethiopia