TGStat
TGStat
Qidiruv uchun matnni kiriting
Ilg‘or kanal qidiruvi
  • flag Uzbek
    Sayt tili
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Saytga kirish
  • Katalog
    Kanal va guruhlar katalogi Kanallar qidiruvi
    Kanal/guruh qo‘shish
  • Reytinglar
    Kanallar reytingi Guruhlar reytingi Postlar reytingi
    Brendlar va shaxslar reytingi
  • Analitika
  • Postlarda qidiruv
  • Telegram'ni kuzatish
TIKVAH-ETHIOPIA

22 May, 18:47

Telegram'da ochish Ulashish Shikoyat qilish

Prev Next
ወደ ኢትዮጵያ ይዞ መግባት የሚቻለው የውጭ ምንዛሪ መጠን ምን ያህል ነው ?

ወደ ኢትዮጵያ ይዞ መግባትና ከኢትዮጵያ ይዞ መውጣት ስለሚቻለው የገንዘብ መጠን በተመለከተ የብሔራዊ ባንክ ባለፈው አመት መመሪያ አውጥቷል፡፡

ይኸው መመሪያ ነዋሪነቱ በኢትዮጵያ የሆነ አንድ ሰው ከውጭ ሀገራት መልስ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የውጭ ምንዛሪ ይዞ ከገባ በ30 ቀናት ውስጥ በንግድ ባንኮች ወይም በተፈቀደላቸው የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ወደ ብር መቀየር አለበት ወይም ወደ ውጭ ምንዛሪ ባንክ ሒሳቡ ማስገባት ይኖርበታል ይላል፡፡ ከውጭ ያስገባው የገንዘብ መጠን ከ4ሺህ ዶላር በላይ ከሆነ ግን ወደ ባንክ ሒሳቡ ሲያስገባው ለጉምሩክ ማሳወቅ እንዳለበት መመሪያው ይደነግጋል፡፡

ሁለተኛ የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከ90 ቀናት በላይ በኢትዮጵያ ለመቆየት ከፈለገ ከውጭ ይዞት የገባውን የውጭ ምንዛሪ በ 90 ቀናት ውስጥ ወደ ውጭ ምንዛሪ የባንክ ሒሳቡ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡ ይዞት የገባው የገንዘብ መጠን ከ 10 ሺህ ዶላር በላይ ከሆነ ግን፣ ወደ ብር ሲቀይረው አለያም ወደ ባንክ ሒሳቡ ሲያስገባው ለጉምሩክ ማሳወቅ/ማስመዝገብ አለበት ይላል መመሪያው፡፡

የኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ የውጭ ዜጋ የውጭ ምንዛሪውን የቪዛ ጊዜው እስኪያልቅ ድረስ መያዝ ይችላል፡፡

ስለ ጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየት የሰጡ የባንክ ባለሙያ ፥ አንድ ሰው ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ለጉምሩክ ማሳወቅ/ማስመዝገብ  ከሚጠበቅበት መጠን በታች የሆነ የውጭ ምንዛሪ ከያዘ በጉምሩክ እንዲያስመዘግብ አይገደድም ብለዋል፡፡

ለምሳሌ ከ10 ሺህ ዶላር በታች ይዞ የሚገባ ሰው ሳያስመዘግብ ወይም ማሳወቅ ሳያስፈልገው በቀጥታ ይዞት መግባት ይችላል ማለት ነው፡፡ ከ10 ሺህ ዶላር በላይ ከሆነ አሳውቅ የሚባለው አንደኛ ወደ ጥቁር ገበያው ወስደህ እንዳትሸጠው ነው ፤ ሁለተኛ ለምን አላማ ከ10 ሺህ ዶላር በላይ ይዘህ እንደገባህ መግለፅ አለብህ ይላሉ ባለሙያው፡፡ ለንግድ ከሆነም በአግባቡ ማሳወቅ ይጠበቅብሀል፡፡

ሆኖም መመሪያው ከ10 ሺህ ዶላር በላይ ከሆነ አስመዝግብ ቢልም ከዛም በታች ከሆነ ማስመዝገቡ እንደሚመረጥ ገልጸዋል። ሳታሳውቅ ያስገባኸውን ዶላር፣ ስትመለስ ይዘህ መውጣት አትችልም፡፡

ቀደም ሲል ከአንድ ዶላር ጀምሮ ተመዝግቦ ይግባ የሚል አሰራር ነበር አሁን እንደዛ ባይባልም በተለይም የተረፈህን ይዘህ ስትወጣ ችግር ላይ ላለመውደቅ ከጅምሩ አስመዝግበህ መግባቱ ይመረጣል ባይ ናቸው፡፡

ለምን ቢባል ከውጭ ይዞት ከመጣው የዶላር መጠን ያልተጠቀመበት ካለና እሱን ይዤ ልውጣ ቢል ችግር ይገጥመዋል፡፡ የራሴን ዶላር የተረፈኝን ነው ይዤ የምወጣው ቢል ማስረጃ አቅርብ ስትገባ አሳውቀሀል ወይ ? ይባላል፡፡ ከኢትዮጵያ በጥቁር ገበያ ገዝቶ የያዘውስ ቢሆን ምን ማረጋገጫ አለ ሊባል ይችላል፡፡ ስለዚህ የቀረውን ገንዘብ በዶላር ይዞ ለመውጣት ይቸገራል ብለዋል ባለሙያው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ እንደዛ ቢልም የመነሻው ሀገር ራሱ ይህን ያህል ገንዘብ በካሽ ይዞ እንዲወጣ ላይፈቅድለት ይችላል ሲሉም ገልፀዋል፡፡ ለምን በባንክ አታስተላልፍም ይባላል፡፡ በባንክ የምታዘዋውርም ከሆነ ለምን ምክንያት እንደሆነ ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት ወይም ለሌላ አላማ ስለመሆኑ መገለፅ አለበት እንደሚባል አስገንዝበዋል፡፡ በተለይም በአውሮፓና በአሜሪካ ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚደረግበት ይናገራሉ ባለሙያው፡፡ ህጋዊ ስለመሆኑ ግብር የተከፈለበት ስለመሆኑና ለህጋዊ አገልግሎት እንደሚወጣ አሳውቆ ነው መውጣት ያለበት ባይ ናቸው፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

214.1k 1 608 513
Katalog
Kanal va guruhlar katalogi Kanallar to‘plamlari Kanallar qidiruvi Kanal/guruh qo‘shish
Reytinglar
Telegram-kanallar reytingi Telegram-guruhlar reytingi Postlar reytingi Brendlar va shaxslar reytingi
API
Statistika API'si Postlar qidiruvi API'si API Callback
Kanallarimiz
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
O‘qish
Blogimiz Telegram tadqiqoti 2019 Telegram tadqiqoti 2021 Telegram tadqiqoti 2023
Kontaktlar
Справочный центр Qo‘llab-quvvatlash Email Vakansiyalar
Har xil narsalar
Foydalanuvchi shartnomasi Maxfiylik siyosati Ommaviy oferta
Botlarimiz
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot