ETHIOPIA NEWS


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri




" ለማመን የሚከብድ ድንቅ ጨዋታ ነበር " ማጓየር

የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግብ ያስቆጠረው ሀሪ ማጓየር የምሽቱ ጨዋታ አስደናቂ እንደነበር ገልጿል።

" ጨዋታው አስደናቂ ጨዋታ ነበር " ያለው ማጓየር ጨዋታውን ተቆጣጥረናል ሶስተኛ ግብ የሚሆን የግብ እድሎችም ነበሩን ብሏል።

ኦሎምፒክ ሊዮን ጥሩ እግርኳስ መጫወቱን የገለፀው ማጓየር ነገርግን እነሱን አስቁመን በጥሩ መንፈስ ጨዋታውን ቀልብሰነዋል ብሏል።

ኮቢ ማይኖ በበኩሉ “ የማይታመን ውጤት ቅልበሳ ነው “ ያለ ሲሆን አክሎም ኳሷ እንደደረሰችኝ በቻልኩት አቅም ለመረጋጋት ሞክሪያለሁ " ሲል ተናግሯል።

ጨዋታውን " የህይወቴ በእብደት የተሞላው ጨዋታ ነው " ሲል የገለፀው ሌኒ ዮሮ ምን እንደተፈጠረ እስካሁን መረዳት አልቻልኩም ብሏል።


ከሩሲያ ጋር ጦርነቱን የጀመረው ዘለንስኪ ነዉ - ዶናልድ ትራምፕ

ትራምፕ ከሩሲያ ከፍተኛ ጥቃት በኋላ ጦርነት በመጀመሩ ዘሌንስኪን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

በዩክሬን በደረሰ እና ከባድ ነዉ በተባለ የሩሲያ ጥቃት 35 ሰዎች ሲሞቱ 1መቶ17 ሌሎች ቆስለዋል።

በሶስት ሰዎች ምክንያት በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል ያሉት ትራምፕ፤ ለዚህ ጦርነት ምክንያት ፑቲን የመጀመሪያዉን ሃላፊነት ይወስዳል፣ ሁለተኛዉ ምን እንደሚያደርግ እንኳን የማያዉቅ የነበረዉ ጆ ባይደን እና ሶስተኛዉ ደግሞ ዘለንስኪ ናቸዉ ብለዋል፡፡

የትራምፕ አስተያየት ሩሲያ እሁድ እለት በዩክሬኗ ሱሚ ከተማ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ከፍተኛ ቁጣን መቀስቀሱን ተከትሎ የመጣ ሲሆን፤ ይህም በዚህ ዓመት ሩሲያ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ያደረሰችዉ እጅግ የከፋ ጉዳት ነዉ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡


አቶ ጽጌ ስጦታው እና አቶ ምስጢረ መዝገቡ ብለው የሚጠሩ ግለሰቦች በቅድስት ቤተክርስቲያኛችን ሥርዓተ እምነት ላይ በወንጀል የሚያስጠይቅ ድርጊት ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
(#EOTCTV ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም)
እራሳቸውን ‹‹መሪጌታ›› ጽጌ ስጦታው እና ‹‹መሪጌታ›› ምስጢረ መዝገቡ ብለው የሚጠሩ ግለሰቦች በቅድስት ቤተክርስቲያኛችን ሥርዓተ እምነት ላይ በወንጀል የሚያስጠይቅ ድርጊት ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው የወንጀል አቤቱታ በቀረበባቸው መሠረት የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ በዛሬው ቀን ተጠርጣሪዎችን በሕግ ቁጥጥር ሥር በማዋል የወንጀል ምርመራውን በማጣራት ላይ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ አባል ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ጠበቃ አያሌው አያይዘው እንደገለጹት ከግለሰቦቹ በተጨማሪ እንዳልካቸው ዘነበ የተባለ ግለሰብ በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም በቤተክርስቲያናችን ላይ ፈጽሞታል ተብሎ በተጠረጠረበት ስም ማጥፋት በቅርቡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ቃሉን ሰጥቶ በዋስትና መለቀቁን እና በአቃቤ ሕግ በኩልም የወንጀል አቤቱታ ክስ ቀርቦ በሒደት ላይ እንደሚገኝ አያይዘው ገልጸዋል።
የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ አባል ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት መረጃ ኮሚቴው ወደ ፊት ጉዳዩን ተከታትሎ የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጸዋል
Via- ኢኦተቤ (EOTCTV)


ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና የሁዋዌ "ቴክ ፎር ጉድ" ግሎባል ውድድርን አንደኛ በመሆን አሸነፉ

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ ግሎባል ውድድርን አንደኛ በመሆን አሸንፈዋል።

ውድድሩ ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በቆየውና በቻይና ቤጂንግ እና ሼንዘን የሚገኙ የቴክኖሎጂ ማዕከሎችን ጉብኝትና የተግባር ስልጠናዎችን ካካተተው ዝግጅት ጋር የተካሄደ ሲሆን፤ የአሸናፊዎች ውጤትም ትናንት ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል።

በስድስት ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን ተማሪዎቹን ከአዲስ አበባ፣ ሃረማያ፣ ጅማ፣ ወልቂጤ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች ማሰባሰቡ ተገልጿል።

በዚህም ውድድር ላይ ኢትዮጵያዊያኑ ከሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካ፤ አርጀንቲና፣ አየርላንድ፣ ማላዊ፣ ቬትናም፣ አረብ ኤምሬትስ እና ሌሎችንም ጨምሮ፤ ከዓለም ዙሪያ ከተውጣጡ 12 ልዩ ቡድኖች ጋር ተወዳድረዋል።

በውድድሩ ላይ የ2025 የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ግሎባል አምባሳደር የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ አሲያ ከሊፋ በእንግድነት ተገኝታለች።

ተማሪዎቹ የእንስሳትን ሕመሞች አስቀድሞ ለመለየት በተዘጋጀውና በአርተፊሻል አስተውሎት (AI) በጎለበተው ኤርሊ ቬት (EarlyVet) በተሰኘው ፕሮጀክታቸው የተወዳደሩ ሲሆን፤ በዚህም ትኩረት ለመሳብ መቻላቸው ተገልጿል።

ይህ የፈጠራ ፕሮጀክት ከተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) በተለይም ግብ 2 "ዜሮ ርሃብ" እና ግብ 15 "ሕይወት በምድር" ከሚለው ጋር የተጣጣመ መሆኑና በግብርና እና በእንስሳት ጤና ላይ ያሉ ወሳኝ ተግዳሮቶችን ይፈታል ተብሎ እንደሚታመን በውድድሩ ተብራርቷል::

Via-አሐዱ


ለትንሳኤ በዓል በ12 ሺህ በር የተገዛን በግ ሰርቀው በ5 ሺህ ለመሸጥ ሲደራደሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ::

የሸካ ዞን ቴፒ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ሚያዚያ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በቴፒ ከተማ አንድነት ቀበሌ ልዩ መጠሪያው ጎንደሬ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ አንድ ግለሰብ ለትንሳኤ በዓል ብሎ በ12 ሺህ ብር የገዛው በግ መሰረቁን ለፖሊስ ቀርቦ ማመልከቱን ተከትሎ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልፆአል።

የቴፒ ከተማ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው መረጃ መሰረት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የሰረቁት በግ በአምስት ሺህ ብር ለመሸጥ ሲደራደሩ የነበሩ ግለሰቦችሁለቱ የስርቆት ወንጀል ፈፃሚዎችና የተሰረቀ በግ የገዛው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እነንደሚገኝ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ዘግቧል።
አዩ ዘሀበሻ


የኬንያ አየር መንገድ አቶ ፍፁም አባዲን የካርጎ ዳይሬክተር አድርጎ ሾሟል።

አቶ ፍፁም አባዲ እ.ኤ.አ ከ2014 ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዳይሬክተር በመሆን ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን የኬንያ አየር መንገድ የጀመርኩትን የካርጎ አገልግሎት ማስፋፊያ በእጅጉ ያግዛሉ ብሏቸዋል።

የኬንያ አየር መንገድ በአመት ከ70,000 ቶን በላይ የካርጎ አገልግሎት እንደሚሰጥ ሲገለፅ የአዲሱ ዳይሬክተር የካበተ ልምድ የአፍሪካ ቁጥር አንድ የአትክልት ላኪ ለሆነችው ሃገር ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ታምኖበታል።


#MoE

" ከ2019 ጀምሮ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

በዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ ዓመት ሳይገቡ በፊት የአንድ ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ከ2019 ዓ/ም ጀምሮ ተግባር ላይ እንደሚውል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ጠቁመዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፤ " በሚቀጥለው ዓመት ላይደርስልን ይችላል ግን ህጋዊ ስርዓቱን በሙሉ ጨርሰን በ2019 ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች ከ2019 ጀምሮ 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይድረጋል " ብለዋል።

" ከዚህ በፊት የነበረ ነው አዲስ አይደለም በጃንሆይ ጊዜ (በአጼ ኃይለስላሴ ጊዜ ማለታቸው ነው) የነበረ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሁለት ጥቅም አለው ብለን ነው ይሄን የምናደርገው አንደኛ ልጆቹ ዝም ብሎ የቀለም ትምህርት ብቻ ተምረው ሳይሆን ተግባራዊ የሆነ ትምህርትም ለአንድ ዓመት ሄደው የሚሰሩበት ከማህበረሰቡ ጋር የሚተዋወቁበት ነው። ሁለተኛ የአስተማሪዎች እጥረትም ስላለ ልጆችን ወደ አስተማሪነት ለአንድ አመት ቢሆንም ለማስገባት ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA


" በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ፀያፍ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈፀም ወንጀል መሆኑ ተደንግጓል " - ፖሊስ

ከኢትዮጵያውያን ባህል፣ ኃይማኖትና ወግ ተቃራኒ የሆነ በርካታ ድርጊቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያስረጨ ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
      
ፖሊስ ግለሰቡ ሚሊዮን ድሪባ የሚባል እንደሆነና በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሚለቃቸው ተንቀሳቃሽ ምስል በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታቸውን ያነሱበት ጉዳይ እንደሆነ ገልጿል።

ከሚነሳው ቅሬታ ባሻገር የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ፀያፍ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈፀም ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል ብሏል።

ግለሰቡ በጎዳናዎች ላይ የተለያዩ አፀያፊ በተለይም የሴቶችን ክብር የሚነካ ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች በመፈፀም የቀረፃቸውን ምስሎች በመልቀቅ በፈፀመው ህገ ወጥ ተግባርና በለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።

በአንዳድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ አንዳንድ ምስሎች ተገቢነታቸውን የሳቱና ያፈነገጡ እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ ገልፆ ህገ ወጥ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በሚለቁ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

#AddisAbabaPolice


" የበዓል ገበያዉ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በማሳየቱ መሸመት ከአቅማችን በለይ ሆኗል " - የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች

➡️ " በዓሉን ታሳቢ በማድረግ  በቂ ምርት ለማቅረብ ተሞክሯል " - የከተማዉ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ

መጪዉን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ በሁሉም ምርቶችና ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የተባለ የዋጋ ጭማሪ ማስተዋላቸዉን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ " በቀናት ልዩነት ዉስጥ በእያንዳንዱ የሸቀጥና ሌሎች ለበዓሉ አስፈላጊ የሚባሉ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የተባለ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል " ብለዋል።

ለአብነትም ፦
- እንቁላል ከ13 እና 15 ወደ 20 ብር
- ሽንኩርት በኪሎ ከ45 ወደ 70 እና 80
- ቅቤ በኪሎ ከ800 ወደ 1000 ብር
- ቲማቲም በኪሎ ከ40 ወደ 65
- ዶሮ አንዱ ከ500-650 ወደ 850-1000
- ስኳር በኪሎ ከ110 ብር ወደ 650 ብር
- በርበሬ በኪሎ ከ600 ወደ  800 ብር
- ዘይት የሚረጋ የሚባለው
             ° 20 ሊትር ከ4500 ወደ 6200
             ° 5 ሊትር ከ1200 ወደ 1600
             ° 3 ሊትር ከ800 ወደ 1050
- ዘይት ባለ ሃይላንድ
             ° 5 ሊትር ከ1400 ወደ 1750
እየተሸጡ መሆኑንና የጤፍ እና የምስር ዋጋ በአንፃሩ መጠነኛ የዋጋ ቅናሽ ማሳየቱን ገልፀዋል።

አስፈላጊዉ ቁጥጥር ካልተደረገ እስከ በዓሉ መዳረሻ ቀናት የዋጋ ጭማሪዉ ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል የሚናገሩት ሸማቾቹ በበዓሉ ዋዜማ ቀናት ዋጋ ለመጨመር ምርት የሚሰዉሩና እያሉ " የለም " የሚባሉ ሸቀጦችና ምርቶች ስለመኖራቸዉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የሀዋሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " ለበዓሉ አስፈላጊ የሚባሉ ልዩ ልዩ የጥራጥሬ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የሸቀጥና ቅመማ ቅመሞች እጥረት እንዳይኖር በማህበራት ዩኒየኖች አማካኝነት በቂ ምርት ለማቅረብ ተሞክሯል " ያለ ሲሆን " የዋጋ ጭማሪዎች እንዳይኖር አስፈላጊውን የቁጥጥር ስራ እያከናወንኩ ነዉ " ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸዉ አንዳንድ ጅምላ አቅራቢ ነጋዴዎችና ማህበራት የተወሰኑ ነጋዴዎችና ድርጅቶች ምርት የማሸሽና በየመደበቅ ስራ እየሰሩ መሆኑንና ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ ብቻ መሸጥ የሚገባቸዉ ማህበራትም ለቸርቻሪ ነጋዴዎች እያሰራጩ መሆኑን ገልፀው ቁጥጥር እና ክትትሉ ካልተጠናረ የበዓል ገበያዉ ከዚህም በላይ ታይቶ የማይታወቅ የዋጋ ጭማሪ ሊታይበት ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።


" በስህተት ወደ አካውንቴ የገባልኝን 3.5 ሚሊዮን ብር ለባለቤቱ መልሻለሁ " - አቶ በህጉ ወ/ሚካኤል

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስህተት ወደ አካዉንቱ የገባን 3.5 ሚሊዮን ብር ተመላሽ ያደረገ ግለሰብ ምስጋና እየተቸረው ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ በስም ተጠቃሹን ግለሰብ አግኝቶ ያነጋገራቸው ሲሆን የባንክ ባለሙያ አስተያየት እና ምክርም ጠይቋል።

በስህተት የገባላቸዉን 3.5 ሚሊዮን ብር የመለሱት አቶ በህጉ ወ/ሚካኤል ምን አሉ ?

" ከባንክ ወደ ባንክ በሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉር ሂደት በተፈጠረ ስህተት ከሌላ ግለሰብ ወደ አካዉንቴ የገባን 3.5 ሚሊዮን ብር ለባለቤቱ ተመላሽ አድርጊያለሁ።

እኔም የስራ ሰዉ ነኝ እንደዚህ አይነት ክስተት ልያጋጥመኝ ይችላል፤ ስለዚህ ገንዘቡ የኔ ስላልሆነና ለባለቤቱ መመለስ ስላለብኝ ሳላቅማማ መልሻለሁ " ሲሉ ጉዳዩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

አቶ በህጉ አክለዉም " ብዙ ሰዎች ሞኝ እንደሆንኩ፣ መመለስ እንዳልነበረብኝና ብመልስም ከላዩ ቀንሼ መሆን እንደነበረበት አስተያየት ሲሰጡ ሰምቻለሁ፤ ዳሩ ግን ቅድም እንዳልኩት የኔ ያልሆነ ነገር የኔ አይደለም፤ በተለይም እኔም በቢዝነስ አለም ዉስጥ እንዳለ ሰዉ ነግ በኔ እንደሆነ በመረዳት ማድረግ ያለብኝ ነዉ ያደረኩት "ብለዋል።

የአዋሽ ባንክ ባለሙያ ስለሁኔታዉ ምን አሉ ?

የአዋሽ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ኦፕሬሽንናል ማናጀር አቶ ፉፋ አሰፋ ስለ ጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ " ከባንክ ወደ ባንክ በሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉር አቶ ቦንሳ ታደለ የተባሉ የባንካችን ደንበኛ ከአንዱ ባንክ አካዉንት ወደ ሌላ ባንክ አካዉንት በአካል ተገኝተዉ በማንዋል ፅፈዉ ሂሳብ ሲያስተላልፉ አንድ ቀጥር ተሳስተዉ ፅፈዉ በመስጠታቸዉ 3.5 ሚሊዮን ብር ወደ አቶ በህጉ ወ/ሚካኤል አካዉንንት ተላልፏል " ሲሉ ገልፀዋል።

ባንኩ ለአቶ በህጉ በመደወል ሁኔታውን ማስረዳቱንና አቶ በህጉም ተባባሪ በመሆን ለባለቤቱ ገንዘቡን ተመላሽ ማድረጋቸውን አስታውቋል።

ለሁሉም የባንክ ተጠቃሚዎች የባንክ ባለሙያዉ ምን አሉ ?

" ከባንክ ወደ ባንክ በሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉር ሂደት ይህ ዓይነቱ አጋጣሚ የመፈጠር ዕድሉ ሰፊ ነዉ። ሁሉም ሰዉ በብር ዝዉዉርና አጠቃላይ በባንክ አጠቃቀም ወቅት ተገቢዉ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት "


ሰሙነ ሕማማት !

ከሆሳዕና በዓል (እሁድ) ስድስት ሰዓት እስከ አርብ (ስቅለት) ማታ ድረስ ያሉት ቀናት ሰሙነ ሕማማት ናቸው።

ሳምንቱ " ዘመነ ፍዳ " የሚታሰብበት ጊዜ ነው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰሙነ ሕማማት ወቅት " የፈጣሪን ህመም " ታሳቢ ያደረግ ልዩ ህግና ስርዓት አለ።

ቤተክርስቲያን ወትሮ የምታከናውናቸው ስርዓቶች በሕማማት ቀናት አይከናወኑም።

ህዝበ ክርስቲያኑ በሰሙነ ሕማማት የፈጣሪውን መከራ በማሰብ በተለየ ስርዓት ነው ቀናቱን የሚያሳልፈው።

በሰሞነ ሕማማት የትኞቹ የቤተ ክርስቲያን ስርዓቶች አይተገበሩም ?

በሰሙነ ሕማማት በቤተ ክርስቲያን " ግብረ ህማማት " የሚባል መጽሀፍ ይነበባል ፤ ለሳምንቱ የተዘጋጀ ልዩ ጸሎት ይደረጋል።

የሌሎች ስርዓቶች ክዋኔ ይገታል።

በሰሙነ ሕማማት ፦
- ቅዳሴ አይቀደስም (ከጸሎተ ሀሙስ ውጭ)
- ማህሌት አይቆምም
- ጸሎተ ፍትሀት አይደረግም
- መስቀል አይሳለምም
- ክርስትና አይነሳም
- ኑዛዜ አይሰጥም አይቀበልም

እነዚህ ስርዓቶች በሆሳዕና ዕለት አስቀድመው የሚከናዎኑ ናቸው።

ምዕመናን ሰሙነ ሕማማትን በምን ስርዓት ይከውናሉ ?

በቤተ-ክርስቲያኗ " የመከራ ዘመን " የሚባለውን 5500 ዓመትን በመወከል አምስት ቀናት ተኩል የሆነው ሰሙነ ሕማማት በምመናን ዘንድ በተለያዩ ድርጊቶች ይታሰባል።

የሚተገበሩት ድርጊቶች ሀዘንን ለመግለጽ እንዲሁም ከአስተምሮ ጋር መልዕክ ያላቸው ናቸው።

ምእመናን በሰሙነ ሕማማት ፦
- ከመጨባበጥና መሳሳም በመራው
- በባዶ እግር በመቆም
- በስግደት
- በጸሎት
- ራስን ዝቅ ማድረግ ያስባሉ።

አባቶች በሕማማት ሳምንት ምዕመኑ ፦
° ወደ ራሱ ጠልቆ በመግባት መጸለይ እንዳለበት
° ሰው ስለ ኃጢያቱ ማሰብ እንዳለበት
° ስለ ሀገሩ ማዘን እንዳለበት
° ለሰላም መጸለይ እንዳለበት
° የሰው ልጅ ሰላም እንዲያገኝ ሰላም ያጣው ህዝብ ሰላም እንዲያገኝ መጸለይ እንዳለበት
° ፈጣሪ የተቀበለውን መከራ በማሰብ ለሀገር ሰላም እንዲሰጥ ህይወታችንን ያስተካክል ዘንድ መለመን እንዳለበት
- ከኃጢያታችን ይቅር እንዲለን መጸለይ እንዳለበት ያስገነዝባሉ።

(መላከ ገነት ክብሩ ገ/ጻድቅ - ከዚህ ቀደም ለአል አይን ከሰጡት ቃል)


" ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ ይዘው እንዳይሄዱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ የሚባል ነገር ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሚመሩት የትምህርት ዘርፍ ላይ ስለአፈጻጻምና ስለታቀዱ እቅዶች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሰጡት ማብራሪያም በሚቀጥለው ሳምንት ከትምህርት ቢሮዎች ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

በዚህም ወቅት ተማሪዎች ስልክ ትምህርት ቤት ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ ስለሚደረገው እንቅስቃሴ እንደሚመከር ገልጸዋል።

" የጋራ ስምምነት ላይ ከደረስን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርት መከታተል ነው እንጂ ከስልክ ጋር የሚጫወቱበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ይደረጋል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ


" የትኛውም አሽከርካሪ ላይ የሚደርስን የትኛውም አይነት ህገወጥ ተግባር አንታገስም ! " - ድሬዳዋ ፖሊስ

በድሬዳዋ " ፎርስ " እየተባለ የሚጠራው ተሽከርካሪ የሚያሽከረክር ሹፌር ላይ አፀያፊ ህገወጥ ተግባር የፈጸመ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የድሬዳዋ ፖሊስ አሳውቋል።

አሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸም ማንኛውም ህገወጥ ድርጊት አልታገስም ሲልም ገልጿል።

በድሬዳዋ ፖሊስ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ኃላፊ ም/ኮማንደር ይሔነው ሽፈራው ፥ " አፀያፊ ድርጊቱ የተፈጸመው ህብረተሰቡን በሰላማዊ ሁኔታ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚያጓጉዝ ፣ የሚያደርስ እና የሚመልስ የፎርስ አሽከርካሪ ላይ ነው " ብለዋል።

ድርጊቱ የተፈጸመው ' ሳቢያን አንበጣ ' አካባቢ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

" ግለሰቡ ከፎርስ አሽከርካሪው ጋር አለመግባባት ሲፈጠር የተሽከርካሪውን ቁልፍ ጭምር ነቅሎ ይዞ ሲሄድ የሚታይበት ምስል በቀጥታ ወደእኔ ነው የተላከልኝ ከዛ ወዲያ በአቅራቢያው ላለው ለጎሮ ፖሊስ ጣቢያ መረጃውን ሰጠናቸው እነሱም ወዲያው ድርጊቱን የፈፀመውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውለውታል " ብለዋል።

ህብረተሰቡ መሰል ህገወጥ ተግባራት ሲመለከት መረጃ እየሰጠ መሆኑ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።

ም/ኮማንደር " የትኛውም አሽከርካሪ ላይ የሚፈጸምን የትኛውም አይነት ህገወጥ ተግባር አንታገስም፤ እንዲህ ያለው ድርጊት የሚፈጽሙትን በትዕግስት አናይም " ብለዋል።

" በከተማችን ያሉ ሁሉም አሽከርካሪዎች በእኩብ አይን ነው የምናያቸው ፤ ከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ምንም አይነት ጥቃት ሳይደርስባቸው አገልግሎት እንዲሰጡ እንፈልጋለን " ሲሉ አክለዋል።

የጎሮ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር አበበ ጥላሁን ፥ " መጋቢት 5 ከምሽቱ 11 ሰዓት ተኩል ገደማ ላይ ነው ' በቀጠናችሁ የተፈጸመ ወንጀል ነው ' በሚል በቪድዮ መረጃው የደረሰን " ብለዋል።

" የተላከውን ቪድዮው ስንመለከት MM ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የታክሲ መሳፈሪያ ቦታ ላይ በታክሲ ተራ አስከበሪ አማካኝነት የተፈጸመ የወንጀል ተግባር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ድርጊት ፈጻሚው ተራ በአስከባሪነት እዛ ይሰራ የነበረ ኤርሚያስ ማሞ የተባለ ግለሰብ እንደሆነና ሚያዚያ 6 በስራ ቦታው ላይ እያለ ተይዞ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን አመልክተዋል።

" ማንኛውም ግለሰብ ድሬዳዋ ላይ ወንጀል ፈጽሞ ማምለጥ አይችልም " ብለዋል።

የድሬዳዋ ፖሊስ በቅርቡ በአንድ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌር ላይ " አጸያፊ " ሲል የጠራውን ተግባር የፈጸመ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል።


" ከ2019 ጀምሮ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

በዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ ዓመት ሳይገቡ በፊት የአንድ ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ከ2019 ዓ/ም ጀምሮ ተግባር ላይ እንደሚውል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ጠቁመዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፤ " በሚቀጥለው ዓመት ላይደርስልን ይችላል ግን ህጋዊ ስርዓቱን በሙሉ ጨርሰን በ2019 ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች ከ2019 ጀምሮ 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይድረጋል " ብለዋል።

" ከዚህ በፊት የነበረ ነው አዲስ አይደለም በጃንሆይ ጊዜ (በአጼ ኃይለስላሴ ጊዜ ማለታቸው ነው) የነበረ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሁለት ጥቅም አለው ብለን ነው ይሄን የምናደርገው አንደኛ ልጆቹ ዝም ብሎ የቀለም ትምህርት ብቻ ተምረው ሳይሆን ተግባራዊ የሆነ ትምህርትም ለአንድ ዓመት ሄደው የሚሰሩበት ከማህበረሰቡ ጋር የሚተዋወቁበት ነው። ሁለተኛ የአስተማሪዎች እጥረትም ስላለ ልጆችን ወደ አስተማሪነት ለአንድ አመት ቢሆንም ለማስገባት ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ


" በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ፀያፍ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈፀም ወንጀል መሆኑ ተደንግጓል " - ፖሊስ

ከኢትዮጵያውያን ባህል፣ ኃይማኖትና ወግ ተቃራኒ የሆነ በርካታ ድርጊቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያስረጨ ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
      
ፖሊስ ግለሰቡ ሚሊዮን ድሪባ የሚባል እንደሆነና በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሚለቃቸው ተንቀሳቃሽ ምስል በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታቸውን ያነሱበት ጉዳይ እንደሆነ ገልጿል።

ከሚነሳው ቅሬታ ባሻገር የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ፀያፍ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈፀም ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል ብሏል።

ግለሰቡ በጎዳናዎች ላይ የተለያዩ አፀያፊ በተለይም የሴቶችን ክብር የሚነካ ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች በመፈፀም የቀረፃቸውን ምስሎች በመልቀቅ በፈፀመው ህገ ወጥ ተግባርና በለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።

በአንዳድ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ አንዳንድ ምስሎች ተገቢነታቸውን የሳቱና ያፈነገጡ እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ ገልፆ ህገ ወጥ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በሚለቁ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።


" ለመንገድ ስራ የተከማቸ አፈር በህፃናት ላይ ተደርምሶ የአንድ ታዳጊ ሕይወት አጥፍቷል " - የወላይታ ከተማ ፖሊስ

በወላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ለመንገድ ስራ ተብሎ የተከማቸ አፈር በአካባቢው ሲጫወቱ የነበሩ ሕፃናት ላይ ተደርምሶ የአንድ ታዳጊ ሕይወት ማለፉን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሀብታሙ አስፋዉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አደጋዉ የተከሰተው በትናትናዉ ዕለት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አከባቢ መሆኑን የገለፁት አዛዡ በስፍራው የነበሩት ከ7 እስከ 9 ዓመት የዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ሶስት ሕፃናት እንደነበሩ ተናግረው ሕይወቱ ካለፈዉ ታዳጊ በስተቀር በሌሎቹ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን ገልጸዋን።

ሕፃናቱ እየተጫወቱ የነበረበት ቦታ ለአደጋ ተጋላጭ መሆን እየጣለ ካለዉ ከባድ ዝናብ ጋር ተዳምሮ ለአደጋዉ መከሰት መንስኤ ሆኗል ሲሉ አስረድተዋል።

ምክትል ኮማንደር ሀብታሙ አስፋው ፥ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እንደሚሰራና በሶዶ ከተማ አስተዳደር የዉስጥ ለዉስጥ የአስፋልት መንገድ ስራ እያከናወነ የሚገኘዉ የቻይና ተቋራጭም አደጋ ሊያስከትሉ በሚችሉ ቦታዎችን ጥበቃ እንዲያስቀምጥ ትዕዛዝ እንደሚሰጥ አስታዉቀዋል።

ከአደጋው ጋር ተያይዞ በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ከአስር በላይ ሕፃናት ሕይወት እንዳለፈ ተደርጎ የሚሰራጨዉ መረጃ ከእዉነት የራቀ ነዉ ያሉት ፖሊስ አዛዡ እንደዚህ ዓይነት መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHW


#Update

ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምን ምላሽ ሰጠ ?

" ለሀገራዊ ፕሮጀክት ሲባል በቦታዉ የነበሩ ነዋሪዎችና የፌደራል ፖሊስ ካምፕን ወደ ሌላ ቦታ በማዛወር የፀዳ ቦታን የመስጂድ ይዞታ እንደነበረ አስመስሎ ማቅረብ  የተሳሳተ መረጃ ነው " - ክፍለ ከተማው

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፤ በቅድሚያ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በኃላም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት " ጨለማን ተገን በማድረግ ፈርሷል " ስላሉት የተባረክ መስጂድ አጥር ጉዳይ አሁን ለሊት መግለጫ አውጥቷል።

ክፍለ ከተማው ፤ " በዛሬው እለት እሁድ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ሜክሲኮ አካባቢ  የመንግስት አካላት የመስጂድ አጥርን አፈረሱ የሚል መረጃ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትን ጨምሮ በተለያዩ  ሚዲያዎች ሲዘዋወር መዋሉ ይታወቃል " ብሏል።

ማንኛውም የመንግስትና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ህገወጥ ድርጊቶች ሲፈፀሙ በህግ አግባብና ህጋዊ ውሳኔን መነሻ በማድረግ ሲከላከል መቆየቱን ወደፊትም የሚተገብረው ትልቁ ኃላፊነቱ መሆኑን አንስቷል።

" በዛሬው እለት በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘዋወር የዋለው መረጃ ቤተ እምነትን ሽፋን በማድረግ መንግስት ዉሳኔ ያልሰጠበት መሬትን ያለአግባብ ከህግ ዉጪ ለመያዝ የተደረገ ተግባራዊ እንቅስቃሴን ለመከላከልና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተወሰደ እርምጃ ነው " ብሎታል።

" ጉዳዩን በተሳሳተ መንገድ መተርጎም በምንም ዓይነት ተቀባይነት ያለው ድርጊት አይሆንም ፤ ህዝባችንም እጅግ አስተዋይ ህዝብ በመሆኑ ጉዳዩን በሚዛኑ የሚረዳ እንደሚሆን እናምናለን " ብሏል።

" ተባረክ መስጂድ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ከመስጂዱ አባቶችና ምዕመናኑ ጋር በቅርበት አብሮ  ከሚሰራቸው፣ ወደፊትም አብሮነቱን ከሚያጠናክራቸው  የእምነት ተቋማት መካከል አንዱ ነው " ያለው ክ/ከተማው ፥ " ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ  የመስጂዱ አስተዳደር ከህጋዊ ይዞታዉ ዉጪ ያለ መሬት ላይ የማስፋፊያ ጥያቄ ለአስተዳደሩ አቅርቧል በሚል ሰበብ ለሀገራዊ ፕሮጀክት ሲባል በቦታዉ የነበሩ ነዋሪዎችና የፌደራል ፖሊስ ካምፕን ወደ ሌላ ቦታ በማዛወር የፀዳ ቦታን የመስጂድ ይዞታ እንደነበረ አስመስሎ ማቅረብ  የተሳሳተ መረጃ ነው " ሲል አሳውቋል።

" ቦታው ከዚህ በፊት የፌደራል ፖሊስ ካምፕና የነዋሪዎች የነበረ ሲሆን ቦታውን በማፅዳት ሀገራዊ ፋይዳ ላለዉ ፕሮጀክት በሀገራዊ ፕሮጀክት ኮንትራክተሩ አማካኝነት ሙሉ ባዶ ቦታዉ በኤጋ ቆርቆሮ እንዲታጠር ተደርጎ የቆየ ነው " ብሏል።

" ነገር ግን ይህ እውነት ሆኖ ሳለ አሁን ግን ቦታውን ያለምንም ህጋዊ ፍቃድ የመስጂዱ እንደሆነ በማስመሰል በመንግስት የታጠረዉን ቦታ ያለምንም ህጋዊ ፍቃድ የመስጂዱን ታፔላ እና በር በመስራት የመስጂዱ አካል በማስመስል ህገ ወጥ ተግባር ከመፈጸሙም በተጨማሪ በመስጂዱ ይዞታ ስር ያልነበረ ቦታ ' መንግስት አፈረሰዉ ' በሚል እየተሰጡ ያሉ መግለጫዎች ፍፁም ህጋዊ መሰረት የሌላቸዉ መሆኑን የእምነቱ አባቶችና ተከታዮች በሚገባ ልትረዱት ይገባል " ሲል አስገንዝቧል።

" ያለአግባብ በተዛባ መረጃ ላይ ተመስርታችሁ ያልተገባ እንቅስቃሴ የምታደርጉ አካላትም ከድርጊታችሁ መታቀብና ቀረብ ብሎ መረጃና ማስረጃ አጣርቶ መረዳትን እንድታስቀድሙ " ሲል በመግለጫው አሳስቧል።

ክፍለ ከተማው ተጨማሪ መረጃ ለሚፈልግ ለማንኛውም አካል መረጃ ለመስጠት በሩ ክፍት መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia


Promotion


#መቄዶንያ

በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ቀደምት ተገልጋይ የነበረው የጌዲዮን ሙላቱ ስርዓት ቀብር መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ፊት ለፊት በሚገኘው አያት መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።

በስርዓት ቀብሩ ላይ የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠን ጨምሮ የማዕከሉ አረጋውያን አንዲሁም ወዳጆቹ ተገኝተዋል።

ጌዲዮን በትልልቅ ሆስፒታሎች የልብ ሕክምና ሲደረግለት የነበረ ሲሆን፤ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በድንገተኛ ሕክምና ክፍል ተኝቶ ልዩ ክትትል እየተደረገለት በትናትናው ዕለት ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በሕክምና ላይ እያለ በ37 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

መረጃው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.