ማርከስ ራሽፎርድ በይፋ ክለቡን ለቀቀ !
የፕርሚየር ሊጉ ክለብ አስቶን ቪላ የቀያይ ሴጣኖቹን የፊት መስመር አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ በውሰት ውል ማስፈረማቸው ይፋ ሆኗል።
እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ በሚቆይ የውል ስምምነት ክለቡን የለቀቀው ማርከስ ራሽፎርድ በ 40 ሚልዮን ፓውንድ በቋሚነት የመፈረም የውል አማራጭ በስምምነቱ ተካቷል።
የአስቶን ቪላ ዋና አሰልጣኝ ኡና ኤምሬ የተጫዋቹ ፈላጊ መሆናቸው ሲገለፅ ለክለቡ በግል ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል።
ማርከስ ራሽፎርድ ባለፉት አስራ ሁለት ጨዋታዎች ለዩናይትድ ምንም ጨዋታ ማድረግ አልቻለም ነበር።
“ ይህ ስምምነት እንዲሳካ ላደረጉት ሁለቱ ክለቦች አመሰግናለሁ “ ያለው ራሽፎርድ “ አስቶን ቪላን መምረጥ ቀላል ውሳኔ ነበር “ ብሏል።
“ መጫወት እፈልጋለሁ ፣ በአስቶን ቪላ እስክጫወት ጓጉቻለሁ። በቀሪ የውድድር ዘመን ማንችስተር ዩናይትድ መልካም ነገር እንዲገጥማቸው እመኛለሁ “ ማርከስ ራሽፎርድ
ማርከስ ራሽፎርድ ለክለቡ የመጀመሪያው ጨዋታ ከጥቂት ቀናት በኃላ በ ኤፌ ካፕ ሌይተን ኦሬይንትን ሲገጥሙ ይሰለፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ራሽፎርድ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት እስከ 2028 የውድድር ዘመን የሚያቆይ ኮንትራት እንዳለው ይታወቃል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe