“ የግብፅ ጨዋታ 70 ሺ ዶላር የምናገኝበት ነው “ አቶ ባህሩ ጥላሁን
⏩ “ ጨዋታውን ገና እጣው ሲወጣ ሸጠነዋል “
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ብሔራዊ ቡድኑ ሞሮኮን የመረጠው ከሚገኘው ጥቅም አንፃር መሆኑን ገልጸዋል።
ሀገር ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም ባለመኖሩ ብሔራዊ ቡድኑ ከሀገር ወጥቶ ለመጫወት መገደዱ የሚታወቅ ነው።
ዋልያዎቹ በቀጣይ የሚያደርጓቸውን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ሞሮኮ ላይ የሚያደርጉት “ የፋይናንስ ጥቅም ስላለው ነው “ ሲሉ የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ተናግረዋል።
አቶ ባህሩ ጥላሁን አክለውም “ የማረፊያ እና ስታዲየም ወጪዎችን የሞሮኮ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይሸፍናል “ ብለዋል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ከሞሮኮ ፌዴሬሽን ጋር ባላቸው ጥሩ ግኑኝነት ይህ ሊሆን እንደቻለ አቶ ባህሩ ጠቁመዋል።
" ከግብፅ ጋር የምናደርገውን ጨዋታ ገና ከሁለት አመት በፊት ነው የሸጥነው " ያሉት አቶ ባህሩ ጨዋታው ላይ ብዙ ፍላጎቶች ነበሩ ብለዋል።
አቶ ባህሩ ጥላሁን አክለውም ከማርኬቲንግ ጋር በተያያዘ ጥሩ ስራ መሰራቱን ያነሱ ሲሆን “ ይሄ ጨዋታ ብቻ 70 ሺ ዶላር የምናገኝበት ነው “ ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe