@ ራእይ'እንዳየ 'አስተዋሉ።!)
በአንዲት እለት ካህኑ ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ለእግዚአብሔር የዕጣን መሰዋዕት በማቅረብ ላይ ነበረ። ለዚህ ጻድቅ ሰው ታዲያ ድንገት በእጣኑ መሰዊያ በስተቀኝ ቅዱስ ገብርኤል ታየው። መላዕኩ ለዚህ አረጋዊ ለብዙ ዘመናት የተመኘውን ጸሎቱን እግዚአብሔር እንደተቀበለውና ሚስቱ ኤልሳ ቤጥ ታላቅ የሚሆን ልጅ እንደምትወልድ ለት ነገረው ዘካርያስ ይኽንን የመላዕኩን ብስራት በሰማ ግዜ
ምንም እንኳን አብርሃም ና ሳራ በስተርጅና ወለዱ የሚለውን ታሪክ ሲያስተምር የኖረ ካህን ቢሆንም ለማመን ተቸግሮ "ይኽ እንደሚሆን በምን አምናለሁ "ብሎ ምልክትን ጠየቀ
ቅዱስ ገብርኤል ለዚህ ጥያቄ "እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ "ብሎ መለሰለት። ይኽ ምላሽ እንደሊቃውንቱ ትርጓሜ "እኔ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆንሁ ለአንተ መገለጤ ምልክት አይደለምን "?
እኔ ኮ "በነበያት መጻሕፍት የምታውቀኝ ገብርኤል ነኝ። በፊትህ የቆምኩት እኮ በእግዚአብሔር ፊት የመቆመው ነኝ
የምነግርህን እንዴት አታምነኝም "?የሚል ትርጉም ያለው ነበረ።
+++++
ቅዱስ ገብርኤል በዚህ አላበቃም "በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሰሩ ይቅር አይልምና እዳታስመርሩት "ተብሎ ከተነገረላቸው የእግዚአብሔር ሹመኞች
አንዱ ነውና ቃሉን ያላመነውን ዘካርያስን ቀጣው (ዘጸ23፥21)የእምነትን ቃል ሊናገር ሲጠበቅበት የጥርጥር ቃል የተናገረውን አንደበቱን ዘጋው እንዴት የተዘጋ ማህጸን ሊከፍት ይችላል ብሉ ለተጠራጠረው ልቡ አንደበቱ ዘግቶ በመክፈት ማህፀንን የዘጋ አምላክ መልሶ እንደሚከፍት ምልክት አድርጓ ሠጠው።
ዘካርያስ በቤተ መቅደሱውስጥ ከመላዕኩ ጋር ሲነጋገር ህዝቡ በውጪ ቆመው ይጠብቁት ነበር እንደ ኦሪቱ ስርአት ካህኑ "እግዚአብሔር ይባርካችሁ ፊቱንም ያብራላችሁ ሀገር"ብሎ ሳያሰናብታቸው ወደ ቤታቸው አይሄዱም ነበረና ዘካርያስ እስኪወጣ ይጠብቁት ነበረ"ስለዘገየም ይደነቁ ነበረ።" እንጂ እንደ ዘመኑ አስቀዳሽ "እነዚህ ካህናት ከጀመሩ ማብቂያ የላተውም ብለው ተንገሽግሸው የካህኑን ማሰናበቻ ቡራኬ ሳይቀበሉ ወደቤታቸው ጥለው አይሄዱም ነበር።
++++++
ከሁሉም የሚያስደንቀውና በዚች አጭር ስብከት የምናሰላስለው ዘካርያስ ከቤተ መቅደስ ዲዳ ሆኖ ከወጣ ቡዃላ ያለውን የሕዝቡን ምላሽ ነው።ሕዝቡ ዘካርያስን ይጠብቁት ነበር በቤተመቅደስ ምን ስለዘገየ ይደነቁ ነበር
በወጣም ግዜ ሊነግራቸው አልቻለም በቤተመቅደስ ራእይ እንዳየ አስተዋሉ።እርሱም ይጠቅሳቸው ነበረ ዲዳ ሆኖ ኖረ የማገልገሉም ወራት ሲፈጸም ወደ ቤቱ ሄድ።(ሉቃ1፥21-23)
ወዳጄ ሆይ እስኪ ቀና ብለህ ለአፍታ ባለንበት ዘመን ቢህን ብለህ አስበው
አንድ ሰንበት ምዕመናን አስቀድሰው ካህኑ ወተው እስከሚባርኳቸው ሲጠባበቁ ቄሱ በጣም ዘግይተው ሲወጡ ዲዳ ሆነው ቢወጡና ሕዝቡን ማነጋገር ቢያቅታቸው ሕዝቡ ምን የሚህ ይመስልሃል "ራዕይ አይተው ወጡ "ብሎ የሚደነቅ ይመስልሃል ከሆነ ድንቅ ነው።
እውነቱን ለመናገር ግን ይኽ ተከስተው መረጃን ለአለም ለማዳረስ ጥቂት ደቂቃዎች በሚበቁበት በዚህ የኢንተርኔት ዘመን ቢሆን ሕዝቡ ከቤተ ክርስቲያኑ ሳይወጣ ወሬው ለአለም በተሰማ ነበር ካህኑ ዲዳ የሆኑት "ተቀስፈው ነው" ለማለትና እርሳቸውም ድፍረቱን አብዝተውት ነበር ዋጋቸውን ሰጣቸው ብሎ በደላቸውን ለማብዛት ሰውሁሉ ሳይረባረብ አይቀርም። ዘካርያስ "በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ"ሆኖ ሳለ ዲዳ ሆኖ ሲወጣ ሰው እራዕይ አየ ብሎ አሰበለት በዚህ ዘመን ግን ሰውዬው መልካም ሰው ቢሆንም እንኳን ይኽ ክስተት ቢከሰትበት "እንግዲህ ላይ ላዩን ጥሩ መስሎ ውስጡ ችግር ይኖር ይሆናል "እንላለን እንጂ ራእይ አይቶ ይሆናል የሚል ግምት ጨረሶ አይኖረንም።
የዚያ ዘመን ሰዎች ግን ለመንፈሳዊነገር በቅርብ የሆነ አስተሳሰብ ነበራቸው ራእይ አየ ብለው መገመታቸውን ሳይበቃ ዲዳሆኖ የወጣ ሰው ሰሞነኛ ነቱን እስኪፈጽም አገልግልቱን ሲቀጥል
ዲዳ ያደረገው የሆነ ጥፋት ቢያይበት ነው ለምን ያገለግለናል ? ብለው አላጉረመረሙም። ይህ የዚያ ዘመን ሰዎችን መንፈሳዊ ህሊና በዚህ ዘመን ሆነን ስናየው ትልቅ ወቀሳ ያለው ነው።
ምክንያቱም ከፓትርያሪክ እስከ ቀሳውስት አባቶችን ማቃለል የዚህ ዘመን ሙያ ከሆነ ሰንብቷል የፖለቲካ ባለስልጣናትን ሲተቹ እንኳን በጥንቃቄና በፍርሃት የተሸበበባቸው ሰዎች ከመንግስት ስልጣን የሚበልጥ መንፈሳዊ ስልጣን ያላተውን አባቶች መቼም በሰማይ እንጂ በምድር እስር ቤት አይወረውሩንም ብለው ነው። መሰል አንዳንዶች ሲሳደቡ ይታያል ። በዚህ ዘመን ካህናትን ማቃለል ጀግና ለእውነት የቆመ የሚያሰኝ ተግባር እየመሰለ መቷል።
++++++
ይኽንን ስል "ካህናቱም እኮ አልከበር አሉ እንዲህ እያደረጉ ብሎ የሚሞግት አይጠፋም ሆኖም አንድን ካህንነ ጥሩ ስለሆነ ብናከብረው ያስከበረው ጥሩነቱ ነው እንጂ እኛ ክህነቱን አስበን አከበርነው ሊባል አይችልም። እንዲያውም እውነተኛ አክባሪ የሚባለው መጥፎ ምግባር የለውን አባት ስለአባትነቱ የሚያከብር ነው። እውነተኛ አክባሪ የሚባለው እንደኖህ ሰክሮ እርቃኑን የጣለ አባቱን እያየ የሚስቅና ለሌሎች የሚናገር ሳይሆን እንደ ሴምና ያፌት እንኳን ለሌላው ላሳይ ራሴም የአባቴን ውርደት አላይም የሚል ነው።
ቅዱስ ጳውሎስ ያደረገውን እናስታውስ በሸንጎ ቀርቦ ሳለ በዳኛው ትዕዛዝ በጥፊ ተመታ። ይኽን ግዜ ሳይፈረድበት መመታቱ አበሳጭቶት ዳኛውን "አንተ ቀኖራ የተለሰነ ግድግዳ እግዚአብሔር አንተን ይመታ ዘንድ አለው አንተ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለ ያለ ሕግእመታ ዘንድ ታዘለሕን አለው ጳውሎስ ይህንን ሲናገር ከአጠገቡ የቆሙት "የእግዚአብሔር ን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህን አሉት። ጳውሎስ እንዲህ ሲሉት "እንደሊቀካህንነቱ አልከበር ሲል ምን ላርግሽ " አላለም ወይንም በዚያ ዘመን የነበረውን የነቀዘ የፈሪሳውያን ህይወት እንደማስተባበያ አልተጠቀመም
ጳውሎስ ያለው እንዲህ ነበር "ወንድሞቼ ሆይ ሊቀ ካህናት መሆኑን ባላውቅ ነው
በሕዝብ አለቃ ላይ ክፉ አትናገር ተብሎ ተጽፏልና (ሐዋ23፥2-5)
**
ልብአድርጉ የእብራውያንን መልዕክት የጻፈው ጳውሎስ ለምን ሊቀ ካህናት ትሳደባለህ ሲሉት "የሐዲስ ኪዳን ካህናት ኢየሱስ ነው ማለት አቅቶት አይደለም። በጥፊ እያስ መታውም እንኳ ቢሆን
ሊቀ ካህናት መሆኑን ሲረዳ "ሊቀ ካህናት መሆኑን ባላውቅ ነው። "አለ።
በዚህም ካህናትን እንኳን ወሬ ሰምተን ቀርቶ በጥፊ ቢያስመቱን እንኳ
አክብሮታችን እንዳይቀንስና ከተሰደብንም "ካህን መሆናቸውን ባላውቅ ነው ፣ፓትርያሪክ መሆናቸውን ባላውቅ ነው "እያልን እንድንጸጸት አስተማረን።