ካህናት በሚሰሩት ኃጢአት እግዚአብሔር ይቀጣቸዋል እንዲያውም ከራሳቸው በደል አልፎ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ "የሲኦል መሬቱ በካህናት አጥንት ተደምድምድሞ ይገኛል "እስከማለት ደርሶ የሓላፊነቱን ክብደት እንደገለጠው ካህናት በአግባቡ ባልጠበቋቸው
በጎቻቸውንና በምዕምናን በደል ሳይቀር ይጠየቃሉ ሆኖም በካህናቱ ድክመት አሳብበን እነሱን ብናቃልል ደግሞ እነሱ ለጥፋታቸው ሲቀጡ እኛ ደግሞ በእግዚአብሔር ካህናት ላይ ባሳየነውንንቀታችን ምክንያት እንቀጣለን።
አንዳድ ሰዎች የቤተክህነትንና የካህናትን ክፉ ዜና ከመስማት ብዛት ተማርረው "እግዚአብሔር እንዴት ይታረቀን በእነርሱ እጅ ንስሃ ገብተን እውነት ይቅር ልንባል ነው እውነት ፈጣሪ በእገሌ አድሮ ይሠራል? "ብለው ተስፋ ቆርጠው ይጠፋሉ። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ግን
እግዚአብሔር እጅግ የረከሰ ሕይወት በነበራቸው ካህናትአድሮ ሲሠራ ታይቶል።
እግዚአብሔር ቤተመቅደሱን ሲዳፈሩ የነበሩት ልጆቹን እያየ ዝም ባለውና መቅደሱን የምናምንቴዎች መፈንጫ ባደረገው በካህኑ ኤሊ አድሮ ስራ ሰርቷል። ኤሊ ለራሱ መጨረሻው ባያምርም በካህንነቱ ግን ሕዝቡ ተጠቅመው መሥዋዕታቸው አርጓል ሰክረሻል "ብሎ ያስቀየማት መካኒቱ ሐናም ለዘመናት ስታነባ ቆይታ ያልተመለሰላት ጥያቄ መልስ ያገኘው ናት ዕንባናልቅሶዋ ውጤት አምጥቶ ሳሙኤልን የመሰለ ልጅ እናት ለመሆን ያበቃት "በደህና ሂጂ የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ልመና ይስጥሽ "በሚለው በካህኑ ኤሊ ቡራኬ ነበር(1ሳሙኤል1፥17)
ካህን ለራሱ ለልጆቹ የማይጠቅም እንኳ ቢሆን በተሰጠው ስልጣን እግዚአብሔር ስለማይለየው ጸሎት የሚያሳርግና ዕንባን የሚያብስ ለመሆኑ ማሳያ ነው።ጌታችን እንዲሰቀል ነገር ጎንጉነውና በጨለማ ግፍ ሸንጎ የፈረደበትን በማለዳም በጲላጦስ ከፊት ያስፈረደበትን ሊቀ ካህናቱን ቀያፋንስ ማን ይረሳዋል
በነቀዘ የቤተ ዘመድ ሹመት ሊቀ ካህናትነቱን አማትና ምራት እየተፈራረቁ ሲያዙበት በነበረው በዚያብልሹ ወቅት በቤተ መቅደስ በጸሎት ፋንታ የገበያተኞች ጫጫታና የሚሸጡ እንሰሳት ጩኸት እንዲሞላ በተደረገበት ዘመን እግዚአብሔር በክፉው ሊቀ ካህናት አድሮ ይሰራ ነበር።ይህ ክፉ ሰው ክርስቶስ እንዲሞት ነቀሥሲጎነጉን
"ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡምን "?ብሎ ነበር ወንጌላዊው ስለዚህ ንግግር ሲያብራራ"ይሕንም የተናገረከራሱ አይደለም ነገር ግን በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ነበረና ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ ሊሞት እንዳለው
ትንቢት ተናገረ"ይላል(ዮሐ11፥50-51)
በሰቃዮቹ ላይ እንኳን አድሮ በሊቀ ክህነታቸው የሚሠራ አምላክ እንደምን ያለ ነው።የካህንን ክፋት ስንሰማ እንደ ዘካርያስ ዘመን ሰዎች ራእይ አይቶ ይህናል የሚል የዋሕ ልብ ይስጠን።
(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ!
ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-
ዩቱብ
https://www.youtube.com/@12Samual
ቴሌግራም
https://t.me/tsidq