+ እግዚአብሔር ያልተቀየማቸው ተጠራጣሪዎች +
አባ ጊዮርጊስ እንዲህ አለ ፦ አረጋዊው ስምዖን ‘እነሆ ድንግል ትጸንሳለች’ የሚለውን ትንቢት ተጠራጠረ፡፡ ይህ ጥርጣሬው ግን በደል ሆኖ አልተቆጠረበትም ይልቁንም ስሙ አማኑኤል የተባለውን ሕፃን ለማቀፍ አበቃው እንጂ፡፡ [ወኢተኈልቈ ሎቱ ኑፋቄሁ ኀበ ጌጋይ አላ አብጽሖ ኀበ ሑቃፌ ሕፃን ዘስሙ አማኑኤል]
ቶማስም የጌታን ትንሣኤ ተጠራጠረ፡፡ ትንሣኤውን መጠራጠሩ ግን የጌታን ጎን ለመዳሰስ በችንካሩ እጁን ለማስገባት አበቃው፡፡ [ወአብጽሖ ኑፋቄሁ ኀበ ገሢሠ አጽልእቲሁ ለመድኃኔ ዓለም] በእውነት ‘መተላለፉ የቀረችለት ኃጢአቱም የተከደነችለት ምስጉን ነው’ (መዝ 32፡1) እግዚአብሔር የወደደው ሰው ቍስሉ አይመረቅዝም በደሉም አይታሰብም፡፡
ጌታ ሆይ እኔንም ስለ መጠራጠሬ አትቀየመኝ ልደትህን የተጠራጠረው ስምዖንን እንዲያቅፍህ ፈቀድክለት፡፡ ትንሣኤህን የተጠራጠረውን ቶማስ ጎንህን አስነካኸው፡፡ ያኛው ‘ዓይኖቼ ማዳንህን አዩ’ ብሎ ዘመረልህ ይኼኛው ደግሞ ‘ጌታዬ አምላኬ’ ብሎ መሰከረልህ፡፡
ጌታ ሆይ እኔ እምነተ ቢሱንም መጠራጠሬን አትመልከትብኝ፡፡ የሚዋዥቅ ሕሊናዬን አጽናልኝ፡፡ እንደዚያ የልጅ አባት ‘አለማመኔን እርዳው’ እንደ ጴጥሮስ ‘ወደ አንተ እመጣ ዘንድ እዘዘኝ’ በመጠራጠሬ አትቀየመኝ፡፡
መጠራጠሬን አይተህ አትቀየመኝ፡፡ አንድ ትቢያ ቢጠራጠርህ እንደማይጎድልብህ አውቃለሁ:: ስለዚህ ራርተህ እምነትን አድለኝ:: ምናለ ለእኔም ማዳንህን አይቼ እስካምን እንደ ስምዖን ዕድሜ ብትጨምርልኝ? መቼም ላንተ ዘመን አይቸግርህም፡፡ ሺህ ዓመት ለአንተ አንድ ቀን አይደለች? ቢያንስ አምኜ አሰናብተኝ እስክልህ እስከ ቀትር አቆየኝ፡፡ አንተን በእምነት እንዳቅፍህ እርዳኝ እንጂ ስምዖን አሰናብተኝ እንዳለህ እኔም ደስ ብሎኝ አርፋለሁ፡፡ ማዳንህን ሳልረዳ ፣ አንተን በእምነት መዳፍ ሳላቅፍህ መሞትን ግን እፈራለሁ፡፡
"አምላኬ ጌታዬ" ብዬ ብዘምርም እንደቶማስ ካልዳሰስሁህ ሰውነቴ በእምነት አይኮማተርም፡፡ ተጠራጣሪውን የማትንቀው ሆይ ጥያቄው የማያባራ ልቤን ጥርጣሬው የማያልቅ ከንቱ ሕሊናዬን እንደቶማስ ራራለት፡፡ ለእኔ የቆሰልከውን ቁስል በእምነት መዳፍ ካልነካሁ ፤ እጄን ከችንካርህ ካላገባሁ የፍቅርህ ጥልቀት አይሰማኝምና እባክህን ‘ና ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን’ በለኝ፡፡
ሳላውቅህ የኖርኩት ጌታዬ ሆይ እንደዚያ መቶ አለቃ ‘ለካስ የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ’ ብዬ ሳልመሰክርልህ አልሙት፡፡ እንደ ሌንጊኖስ ወግቼህ በፈሰሰው በጎንህ ውኃ ዓይኔን አብርተህ ካለማመን ብታወጣኝ ምናለ?
ያላመኑትን የማትንቀው ሆይ ተጠራጣሪዎችን ያልተቀየምከው ሆይ የሚጠራጠርህን ልቤን አትቀየምብኝ፡፡ የሚያስብ የሚጠይቅ አእምሮ ሠጥተህ ለምን ተጠቀምክበት ብለህ አትቀየምምና ስምዖን አቀፈህ ቶማስም ዳሰሰህ!
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 18 2013 ዓ.ም.
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ!
ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-
ዩቱብ
https://www.youtube.com/@12Samual
ቴሌግራም
https://t.me/tsidq
ቲክ ቶክ
https://vm.tiktok.com/ZMkpyjd6h/