University Students


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha


ይህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን ያተረፈ ለሁሉም ተማሪዎች የተከፈተ ጠቃሚ ቻናል ነው፣
Buy ads: https://telega.io/c/+BmKx2NUG8Nc1ZTU0
አባል ለመሆን ከታች 👇👇
🔸መረጃ እና መልእክት ለመላክ 📧 @Ethiiostudents_bot

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


Old telegram ግሩፖች ያላችሁ

✍️የ Group ሜምበር ብዛት አያስፈልግም

✍️በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛን እንገኛለን

ዋጋ
🟥  🔂አሁን ያለው የ group ዋጋ

✍️2018- 650ብር
✍️2019- 600ብር
✍️2020- 550ብር
✍️2021- 500ብር
✍️2022- 400ብር
✍️2023 - 100 ብር

✔️ክፍያ : 🏦 🏦 🏦 🏦 🏦 🏦 🏦

ለመሸጥ ምትፈልጉ  inbox
👉 @dag_arshavin

⚠️ ማሳሰቢያ ❗️

የግሩፑ Member ብዛት ''0'' ይሁን  ዋጋው እኩል ነው ❗️እኛ የምንፈልገው የተከፈተበትን አመተ ምህረት ብቻ መሆኑን ይገንዘቡ

two step verification ኦን መሆኑን check አርጉ   


➡️በተጨማሪም
📱ቴሌግራም premium እና
💎ቴሌግራም star  ከፈለጉ ያናግሩን @dag_arshavin
                                                   
FOR MORE  @ArshavinStore


#የመውጫፈተና

የከፍተኛ ትምህርት ቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ 10/ 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ብሄራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) መያዝ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) " የ2017 የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 10 /2017 ዓ.ም. በ51 ዩኒቨርስቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ይሰጣል " ብለዋል።

ፈተናውን በ238 የትምህርት መርሃ ግብሮች ለ190 ሺ 787 ቅድመ መደበኛ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች በበይነ መረብ ለመስጠት  አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

ለፈተናው 102 ሺ 360 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ፤ 88 ሺ 422 ተማሪዎች ደግሞ ዳግም የሚፈተኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ተማሪዎች ወደ ፈተና ማዕከላት ሲመጡ አገር አቀፍ ፋይዳ /ብሄራዊ መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸውም ኃላፊው አስገንዝበዋል፡፡

በፈተና ወቅት ፦
- ተንቀሳቃሽ ስልክ ፣
- ሜሞሪ ያለው የእጅ ሰዓት ፣
- የራስ ያልሆነ መታወቂያ፣
- ያልተፈቀዱ ሂሳብ ማሽኖች፣
- አጫጭር ማስታወሻዎች፣
- የተጭበረበሩ ሰነዶች
- ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት ክልክል መሆኑን አስገንዝበዋል።

ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ፦
° አደንዛዥ ዕጽ ተጠቅሞ መምጣት፣
° ከፈተና አስፈጻሚዎች ጋር አሉታዊ ተጽእኖ ያላቸው ውዝግቦችን መፍጠር ፣
° ያለመታወቂያ ካርድ ወደ ፈተና ማእከል መሄድ ፣
° ያለፈቃድ ፈተና ማዕከል መገኘት
° ለሌላ ሰው መፈተን ፍጹም የተከለከሉ ዲሲፒሊን ጥሰቶች መሆናቸውን አሳስበዋል።

ከሰኔ 2 እስከ 10/ 20017 በሚሰጠው አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና 4 ሺ 17 ፈተና አስፈጻሚዎች እንደሚሳተፉ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል ::

✅ University News ✅
✅ University News ✅


Sene 2017 Exit Exam Schedule.xls
235.5Kb
#ExitExamSchedule

የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂዎች በመውጫ ፈተናው መርሐግብር ላይ ለውጥ ተደርጓል ወይ ሲሉ ጠይቀውናል።

የ2017 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ ዕጬ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ከሰኔ 02-10/2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑንና ለውጥ አለመኖሩን ለማረጋገጥ ችለናል።

በዚህም የመውጫ ፈተናው ከሰኔ 02/207 ዓ.ም ጀምሮ ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

(የፈተናው ጊዚያዊ መርሐግብር ከላይ ተያይዟል።)


✅ University News ✅
✅ University News ✅


#RemedialExam

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከዛሬ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት ይሰጣል።

ፈተናው በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና በሦስት ክፍለ ጊዜ ይሰጣል።

✅ University News ✅
✅ University News ✅


May 30 revised-Sene2017-EXIT EXAM Schedule - 1 -(1).xls
235.5Kb
#ExitExam_schedule

ከአንድ ሳምንት በሗላ የሚሰጠው የ 2017 ሰኔ ወር ብሔራዊ የዩንቨርስቲ መውጫ ፈተና (university national exit exam) መርሐ ግብር(schedule)
➡️ሰኔ 2 management
➡️ሰኔ 3 Accounting
➡️ሰኔ 4 ህግ computer science, biology, sociology, social work.... እያለ ይቀጥላል
➡️ሰኔ 5 Midwifery, Pharmacy, Medical Radiology እያለ ይቀጥላል.........

✅ University News ✅
✅ University News ✅


ትምህርት በቤቴ® dan repost
ተማሪዎቻቸውን የመውጫ ፈተና ማሳለፍ ያልቻሉ ከ80 በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፈቃዳቸው ሥራቸውን ማቆማቸው ተገለጸ

በተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና በተከታታይ ሦስት ጊዜ ከ25 በመቶ በታች ያስመዘግቡ ተቋማት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የተቀመጠው መምሪያ ተግባራዊ ባይሆንም፤ ከ80 በላይ ተቋማት በፈቃዳቸው ሥራቸውን ማቆማቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ለአሐዱ አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴር መ/ቤቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ የወጣው መመሪያ እስካሁን ተግባራዊ ባይደረግም በራሳቸው ተነሳሽነት ዘግተው የወጡ እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡

"በተጨማሪም ሕብረተሰቡ አሁን ላይ የመውጫ ፈተናን መሠረት በማድረግ በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እያሳለፈ ነው" ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው፤"አነስተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማት የሚመዝገቡ ተማሪዎች እያጡ በመሆኑ ለመዘጋታቸው ምክንያት ሆኗል"ብለዋል።

መንግሥት እስካሁን የቅጣት እርምጃ ባይወስድም አሁን ያለው አካሄድ ግን ሌሎች ተቋማት የመማር ማስተማር ጥራትን በማሻሻል ላይ እንዲያተኩሩ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

"የመውጫ ፈተናው የተጀመረው በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎችን አቅም ለማሻሻል ነው" ሲሉም ተናግረዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በተከታታይ ሦስት ጊዜ በተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከ25 በመቶ በታች ውጤት በሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ እርምጃ እንደሚመወሰድ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፤ እርምጃውም በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል እንደሚወሰድ አስታውቋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በኦንላይን ለሚወስዱ ተማሪዎች #ሞዴል ፈተና በተለያዩ ቦታዎች እየተሰጠ ነው፡፡

#ሞዴል ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት እንዲሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መርሐግብር ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡

ሞዴል ፈተናው መልቀቂያ ፈተናውን በሁለት ዙር በኦንላይን የሚወስዱ ተማሪዎች አስቀድመው በተለያዩ የመፈተኛ ጣቢያዎች በመገኘት ልምምድ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ምስል፦ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

✅ University News ✅
✅ University News ✅


#RemedialExam

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከግንቦት 25-30/2017 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

መርሐግብሩ እንደሚያሳየው ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የባዮሎጂ ትምህርት ፈተና ይጀመራል፡፡

በኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት ፈተናው አርብ ግንቦት 29/2017 ዓ.ም የማይሰጥ መሆኑን መርሐግብር ያሳያል፡፡

ፈተናው ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጠው የእንግሊዝኛ ትምህርት ፈተና እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ግምገማ ከ100% ከማዕከል ብቻ እንደሚሆን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡

✅ University News ✅
✅ University News ✅


የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚወሰዱ ተማሪዎች ለቅድመ ዝግጅት የሞዴል ፈተና እየተሠጠ መሆኑ ተገለጸ

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወሰዱ ተማሪዎች ቅድመ ዝግጅት ሥራ እንዲሰሩ እና ተማሪዎች 'ምን ያህል ተዘጋጅተዋል?' የሚለውን ለማወቅ፤ በክልል እና በሀገር ደረጃ የሞዴል ፈተና እየተሠጠ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይልቃል ወንድሜነህ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ የሞዴል ፈተናው የሚሰጠው ተማሪዎች ከዋናው ፈተና በፊት የዝግጅት ደረጃቸውን እንዲገመግሙ ለመርዳት ነው።

"ፈተናው ተማሪዎች ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን እንዲለዩ፣ ጊዜያቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲቆጣጠሩ እና ከፈተና ጋር የተያያዘ ጭንቀትን እንዲቀንስ ያስችላቸዋል" ሲሉም ተናግረዋል።

እንዲሁም ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉት ጥያቄዎች አወቃቀር እና አስቸጋሪነት እራሳቸውን እንዲያውቁ ጠቃሚ ዕድል ይሰጣቸዋል።

ሞዴል ፈተናው በክልልም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጥ ሲሆን፤ ይህም ተማሪዋቹ ምን ያህል ብቁ ናቸው የሚለውን ትክክለኛ ግምገማ እያስገኘ ነው ተብሏል።

እንዲህ ያለው ሁሉን አቀፍ የዝግጅት ስልት በሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎችን አጠቃላይ ውጤት ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የ2017 ትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ከሰኔ 23 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

አገልግሎቱ በወረቀት የሚፈተኑ እና በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች እንደሚያካትት ተገልጿል።

የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ፤ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪ መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ሊዘጋጅ እንደሚገባ አስተላልፏል።

✅ University News ✅
✅ University News ✅


⚡️የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምን ያህል ተማሪዎች ይወስዳሉ?

👉በአገር አቀፍ ደረጃ 608 ሺህ 588 ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል

👉309 ሺህ 547 የተፈጥሮ ሳይጓስ ተፈታኞች

👉299 ሺህ 41 የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች

👉150 ሺህ ተማሪዎች በኦላይን (በይነ መረብ) ፈተናቸውን ይወስዳሉ

✅ University News ✅
✅ University News ✅


#መውጫ ፈተና #ተፈታኞች በሙሉ፡-

ስለ ሀገራዊ ድጂታል መታወቂያ (National Digital ID card) ይመለከታል፡፡

#NationalIDEthiopia  *9779# በመደወል ማግኘት ይችላሉ

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ መደረጉ ይታወቃል። 

ዕጩ ተመራቂዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ አስፈላጊ የፋይዳ አገልግሎቶች፦

➫ የፋይዳ ቁጥር ከጠፋባችሁ ወይም ካልደረሳችሁ *9779# በመደወል በድጋሚ ማስላክ ትችላላችሁ።

➫ በምዝገባ ወቅት የተሳሳተ መረጃን ለማደስ በ National ID Ethiopia ድረ-ገፅ
id.gov.et/update ላይ በመግባት ወይም የፋይዳ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ ላይ በመግባት በቀላሉ ማደስ ትችላላችሁ።


✅ University News ✅
✅ University News ✅


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ6ኛና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ6ኛና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ በመጪው ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍለ ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 3 እና 4/2017 ዓ.ም ይሰጣል የተባለ ሲሆን የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ደግሞ ከሰኔ 10 እስከ 12 እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

✅ University News ✅
✅ University News ✅


#NationalExam

በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 608 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ/ም የሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ላይ 608 ሺህ ተማሪዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ፈተናው በወረቀት እና በበየነ መረብ ይሰጣል።

ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች እንደ ቀደሙት ዓመታት ሁሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ይወስዳሉ።

ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ ፦
- በዩኒቨርሲቲዎች፣
- በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣
- በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች
- በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ። ተማሪዎቹ ግቢ ማደር ሳይጠበቅባቸው ከቤታቸው እየተመላለሱ ነው ፈተናውን የሚወስዱት።

በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና በሁለት ዙር ሲሆን ይህም የሆነው በበይነ መረብ የመፈተን አቅምን እና የተፈታኝ ተማሪዎችን ቁጥር ለመጨመር እንዲሁም ያለውን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል አስረድቷል።

✅ University News ✅
✅ University News ✅


የመውጫ ፈተና በድጋሚ መውሰድ ለምትፈልጉ በሙሉ


የዳግም ምዝገባ ቀነ ገደብ  እስከ ግንቦት 14 ተራዝሟል ፣ ምዝገባችሁን በቀነ ገደብ ውስጥ እንድታጠናቅቁ በድጋሚ እናሳስባለን ።

ለመመዝገብ👇
https://exam.ethernet.edu.et

Step 1 Provide Username

Step 2 Verify Fayda ID

Step 3 Review Fayda Profile

Step 4 Update Preference

Step 5 Complete Payment and Registration

✅ University News ✅
✅ University News ✅


የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?

➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 26 ፣ ሰኔ 27 እና ሰኔ 30/2017 ዓ/ም

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል ?

➡️ በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም

➡️ በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 4 ፣ ሐምሌ 7 እና ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም


✅ University News ✅
✅ University News ✅


❗️አርምጃ ይወሰድባቸዋል

በተከታታይ ሦስት ጊዜ በተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከ25 በመቶ በታች ውጤት በሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ እርምጃ እንደሚመወሰድ ተገለፀ።

ይህ የተገለጸው የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተከታታይ ሦስት ጊዜ በተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ውጤት ከ25 በመቶ በታች የሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል እርምጃ እንደሚወሰድ አመላክተዋል።

የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በብቃትና በችሎታ እንዲመደቡ እየተደረገ መሆኑን አንስተው " አሰራራቸውን ለማዘመንም የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ማሰልጠኛ ተቋም ለማቋቋሞ እየተሠራ ነው " ብለዋል።

✅ University News ✅
✅ University News ✅


የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ ዓመት በኑክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት መስጠት ይጀምራል።

እ.አ.አ. በ2026 ከ2ዐ እስከ 25 ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር እንደሚጀምር ዩኒቨርስቲው ገልጿል።

ለዚህም ዩኒቨርሲቲው ከቻይናው ሽንግዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን የካሪኩለም ቀረጻ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የአፍሪካ ኑክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል እንዲሆን መመረጡን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ተናግረዋል።

ከዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እና የቻይናው ሽንግዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስር የአፍሪካ ኑክሌር ሳይንስ ማዕከል እንዲቋቋም ስምምነት ተደርጓል፡፡

ማዕከሉ ከኢትዮጵያ ባለፈ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት የሚመጡ ተማሪዎች የሚቀበል መሆኑ ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው አምስት ኢትዮጵያውያንን ወደ ሩሲያ እና ቻይና በመላክ በኑክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በመጀመርያ ዲግሪ ሥልጠና ላይ መሆናቸውንና የመጨረሻ ዓመት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

የኑክሌር ሳይንስ ቴክኖሎጂ ማዕከሉን ሥራ ለማስጀመር ብቻ 200 ሚሊዮን ብር ይፈጃል የተባለ ሲሆን፤ ወጪውን ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ እንደሚሸፍን ተገልጿል፡፡ #ሪፖርተር

✅ University News ✅
✅ University News ✅


ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ቅፅ አዘጋጅቶ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መላኩ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ኃላፊዎች ከትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሸኔ ጋር በመውጫ ፈተና እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል።

በዚህም ልኩ ሰርተፊኬቱ የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ወስደው የማለፍያ ነጥብ ላላመጡ ተማሪዎች ብቻ መሆኑን ገልፀዋል።

የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች አዲሱ ሰርተፊኬት የማይመለከታቸው ሲሆን፤ በፊት ይሰጥ በነበረው ፎርማት እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ከዘንድሮ ጀምሮ ማለትም በሰኔ 2017 ዓ.ም ከሚሰጠው የመውጫ ፈተና አስቀድሞ ሁለም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት #ሞዴል የመውጫ ፈተና በአስገዳጅነት ለተማሪዎቻቸው እንዲሰጡ ይደረጋል ብለዋል።

✅ University News ✅
✅ University News ✅


ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎች ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሔዱ የሚያደርግ ሕግ ሊተገብር መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

ሕጉን ወደ መሬት ለማውረድ ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች እና ከዘርፉ አመራሮች ጋር ውይይት ለማድረግ ዕቅድ ይዟል፡፡

በሕጉ ዙሪያ ሸገር ኤፍኤም ያነጋገራቸው መምህራን ውሳኔው ጥሩ መሆኑን ገልፀው፤ ሊታዩ የሚገባቸው ሌሎች ነገሮች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

ተማሪዎች አሁን ላይ ክፍል ውስጥ ሞባይል ስልክ ይዘው ሲማሩ ‘’ትምህርታቸው ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ፣ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን መከታተል እንደሚያበዙ" ጠቅሰዋል፡፡

ስልክ መያዛቸው ከትምህርታቸው እንዲናጠቡ እያደረጋቸው መሆኑን ያነሱት መምህራኑ፤ መፅሐፍት እና ጥናት ላይ ከማተኮር ይልቅ ሌሎች ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂዎች ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ አድርጓል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ትምህርት ቤቶች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ጉዳዮች እንዳሉ ገልፀዋል፡፡ በቂ የመፅሐፍት አቅርቦት፣ የICT ላብ፣ የኮምፒውተር ግብዓቶች እንዲሁም የተለያዩ አጋዥ መፅሐፍት ሊሟሉ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡


✅ University News ✅
✅ University News ✅

19 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.