በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት አደረሳቹ አደረሰን!
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
___በዓለ ዕርገት
• ┈┈•┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈┈ •
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ በምድር ላይ ምስክሮቹ እንዲሆኑ ለመደባቸው ደቀመዛሙርቱ አርባ ቀን ሙሉ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምስጢር ሲነግራቸውና ሲያስረዳቸው በሃይማኖታቸውም ሲያጸናቸው ቆየ፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላም በቅዱስ መንፈሱ ወደዚህ ዓለም ተመልሰው ከእነርሱ ጋር አብሮአቸው እንደሚሆንም አበሰራቸው፡፡ይህ እስከሚሆን ድረስ ግን በኢየሩሳሌም እንዲቆዩ አዝዞአቸው እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ባለችበት እያዩት ወደ ሰማይ አረገ፡፡ በዓለ እርገት ይህችን ዕለት በማዘከር የምናከብርባት እኛም በቅዱሱ ኪዳን ክርስቲያኖች በትንሳኤ ሕይወት የኖርን የትንሳኤ ልጆች ስለሆንን በክርስትና ጥምቀታችንም ለመጀመሪያው የመንፈስ ቅዱስ የበቃንበትን መንፈሳዊ አካል ስለለበስን እያንዳንዳችን ጽዋችን ደርሶ በእረፍተ ሥጋ ከዚህ ዓለም በምንለይበት ጊዜ የመኖሪያችንን ፈለግ ተከትለን እንዲህ በአርባ ቀናችን ነፍሳችን ወደ ሰማያት የምታርግ መሆኗን የምናስታውስበት እለት ናት፡፡
ይህንም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ እንደተነሳ ለማርይም መግደላዊት ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው ብሎ ያሰማት የመልዕክት ቃል ከትንሳኤው በኋላ እንዲያዩት የተዘጋጀላቸው ሌላው የእግዚአብሔር ድንቅ ኃይል ምን ዓይነት እንደሆነ ያመለክታል፡፡
ደግሞሙ ከሙታን ተለይቶ የተነሳው ጌታ በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ የተሰበሰቡትን የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስካረገበት ቀን ድረስ አርባ ቀን እየታያቸው ስለእግዚአብሔር መንግስት ነገር እየነገራቸው በብዙ ማስረጃ ከህማማቱ በኋላ ህያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው፡፡ ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጣ አዘዛቸው፡፡ ነገር ግን ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ ዮሐንስ በውሃ አጥምቆ ነበርና፡፡ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ፡፡
እነርሱም በተሰበሰቡበት ጊዜ ‹‹ጌታ ሆይ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሰትህን ትመልሳለህ››ብለው ጠየቁት፡፡ እረሱም ‹‹አብ በገዛ ስልጣኑ ያደረገውን ወራትና አመታትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፡፡በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ፡፡››
ይህንንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፡፡ ደመናትም ተቀበለችው፡፡ እነርሱም ሲሄድ ወደሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳለ እነሆ ነጫጭ ልብስን የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፡፡ ደግሞሙ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደሰማይ እየተመለከታችሁ ለምን ትቆማላችሁ ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ተመልሶ ይመጣል አሉዋቸው፡፡የሚለው የወንጌላዊው ቃል ስለ እርገት ምስጢር የተነገረውን እውነታ የበለጠ ያረጋግጣል።
የሐዋ.2፥1-20
• ┈┈•┈••●◉ ✞✟✞ ◉●••┈┈ •
📚 የኢየሱስ ክርስቶስ ጾምና ስቃዩ ከዘወረደ እስከ ጰራቅሊጦስ
ከገፅ 80 ጀምሮ
✍🏽በሊቀ ኅሩያን የማና ብርሃን የተጻፈ ታህሳስ 2006 ዓ.ም
@fkl00
@fkl26