ለሕወሓት አመራሮች መከፋፈል ምክንያት የፕሪቶሪያው ስምምነት እንደሆነ ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ
አንዳንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ረገብ እያለ የቀጠለው የሕወሓት አመራሮች ሽኩቻ መነሻው፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት ላይ የተሳተፈው የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን ምን መፈጸምና አለመፈጸም እንዳለበት በተገቢው ሁኔታ ሳይደራደር ትዕዛዝ ተቀብሎ በመምጣቱ ምክንያት መሆኑን፣ የሕወሓት አንደኛው ክንፍ ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ።
ደብረ ጽዮን (ዶ/ር) ዘ ኒው ሂዩማኒታሪያን ከተሰኘ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ‹‹የፕሪቶሪያ ስምምነት አሁን በትግራይ ፖለቲካ ልሂቃን መካከል ለሚታየው መቆራቆስ ዋነኛ ምክንያት ነው፤›› በማለት ስምምነቱን ‹‹የክፍፍሉ መነሻ›› ብለውታል።
አቶ ጌታቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ይዘውት የተጓዙት ተደራዳሪ ቡድን በጦርነት ለደቀቀችው ትግራይ፣ ‹‹ጦርነቱን ብቻ እንዲያስቆምና ከዚያ ያለፈም ያነሰም ነገር እንዳይፈጽም ነበር ተልዕኮ የተሰጠው፤›› ያሉት ደብረ ጽዮን (ዶ/ር)፣ የክልሉን መንግሥት የሚያፈርስ ትዕዛዝ ጭምር ይዘው መጥተዋል በማለት ተደራዳሪ ቡድኑን ኮንነዋል።
‹‹የስምምነቱ ሙሉ ውሎች በፌዴራል መንግሥት የተቀረፁ ናቸው። የእኛን ተደራዳሪ ቡድን ‹በቀላሉ ትዕዛዞችን እየተቀበላችሁ እንጂ እየተደራደራችሁ አይደለም› ብለን ነግረናቸዋል፤›› በማለት አክለዋል።
እነ አቶ ጌታቸው በፌዴራል መንግሥት ግፊት የትግራይን ክልላዊ መንግሥት የሚያፈርስ፣ የትግራይ ሠራዊትን በአጭር የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ትጥቅ የሚፈታበት፣ እንዲሁም በአማራ ኃይሎች የተያዙ የትግራይ ክፍሎችን ‹‹አወዛጋቢ ግዛቶች›› የሚል ስምምነት ፈርመው መጥተዋል ሲሉም አስረድተዋል።
ይሁን እንጂ አሁን የፕሪቶሪያ ስምምነት ራሱ መፈጸም አለመቻሉን ገልጸው፣ እሳቸውና ቡድናቸው ስምምነቱ ተፈጻሚ እንዲሆን ቁርጠኛ እንደሆኑ ደብረ ጽዮን (ዶ/ር) ተናግረዋል። ሕወሓት በሰላም ስምምነቱ መሠረት የአማራ ኃይሎችና የኤርትራ ወታደሮች የትግራይ ተዋጊ ኃይል ትጥቅ ከመፍታቱ በፊት መውጣት እንዳለባቸው፣ ተፈናቃዮች የሚመለሱበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠርና ምርጫ የሚደረግበትን ዓውድ ማመቻቸትን አሁንም እንደሚጠይቅ አስታውቀዋል።
የደብረ ጽዮን (ዶ/ር) ቡድን የአማራ ኃይሎች እንዲወጡ በፌዴራል መንግሥት ላይ ጫና ማድረግ ባለመቻሉ የአቶ ጌታቸውን ጊዜያዊ አስተዳደር ተጠያቂ ቢያደርግም፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በበኩሉ የፕሪቶሪያን ውል በመጣስና ድንበር ማስከበር ባለመቻሉ የፌዴራል መንግሥትን ሲወቅስ ይደመጣል።
የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የደብረ ጽዮን (ዶ/ር) ቡድን አጋር የሆኑት አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር)፣ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከፈለጉ በአንድ ጥሪ ጥያቄዎቹን መመለስ ይችሉ ነበር፤›› በማለት በአማራ ኃይሎች ተይዘዋል ስለተባሉት አካባቢዎች ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ሕወሓትን በተመለከተ ስብሰባ ካደረገ በኋላ ጠቅላላ ጉባዔ ለማካሄድ የተሰጠውን የጊዜ ገደብ ባለመጠቀሙ፣ ለሦስት ወራት በምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዳይሳተፍ ዕገዳ ጥሎበታል፡፡ ሕወሓት የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት ማክበሩ ይታወሳል።
Via REPORTER
የቴሌግራም ቻናሉን Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ📥
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ይህንን በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 🔽
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g