አይደለም በሙዚቃ በጦር መሳሪያ......!🔫
(ሰውሁን በለው"አቤኒ")
ትንሽ ዘግየት ብሏል ከአንዲት ልጅ ጋ ተያየን። አየኋት አየችን።ከዛም ገላምጣኝ ዞረች።እኔም ምን አስገላመጣት የሚለው ጥያቄ ውስጤን አብከነከነው።ለካስ ኋላ ላይ ስረዳው የመማረኪያ አመሏ ነው።ከቆይታ በኋላ በጓደኛዬ ምክንያት Hi Hi መባባል ጀመርን።አንድ ቀን ጓደኞቼን ስለ መጸሀፍ እያወሯዋቸው አንድ ያላነበብኩትን መጸሀፍ ስም ጠርተው እንዳነበቡት ሲነግሩኝ መጸሀፋን የት ላገኝ እንደምችል ጠየኳቸው።እናም መጸሀፋ የገላመጠችኝ ልጅት መሆኑን ነገሩኝ።ማናገሩም ቢደብረኝ የመጸሀፍ ነገር ሆኖ አላስችል አለኝና አወራዋት፡ችግር የለውም ውሰድና አንብበው አለችኝ፡በሁለት ቀን አንብቤ መለስኩኝ።እንደገና ሌላ መጸሀፍ ሰጠችኝ በ1ቀን አንብቤ መለስኩላት፡አደነቀችኝ፡ከዛም ሌላ መጸሀፍ ፡ በቃ መጸሀፍ አግባባን..............
እየተቀራረብን ስናወራ ልጅት ወሬዋ ሁሉ ስለ ሀይማኖት ሆነ።ስንገናኝም፣በቴሌግራምም፣ በስልክም.........ብቻ በተገኘው አጋጣሚ ወሬዋ ስለ ሀይማኖት ነው።እኔም እኔ ጋ ያለውን እርሷም እሷ ጋ ያለውን የሀይማኖት ነገሮች Share እንደራረግ ጀመር።በመሀል ከዕለታት አንድ ምሽት የፕሮቴስታንት መዝሙር ላኩላት። እሷም የእኛን የአዘማመር ሁኔታ አቃቂር ለማውጣት ተሰለፈች።እኔስ ማን ብሎኝ ዘራፍ የፓ/ር ...... ልጅ ዘራፍ ለአምልኮ ዘራፍ............
መዝሙሩን ሰምታ(የጨረሰችው እንኳን አይመስለኝም)"እንዲ አይነት በሙዚቃ መሳሪያ የተቀነባበረ መዝሙር አትስማ ከዚያ ይለቅ በበገና፣በከበሮ ፣በመሰንቆ፣በክራር እና እነዚህን በመሳሰሉት በቤተ ክርስቲያን ስርዓት ምናምን ባላቸው የተሰሩ መዝሙሮችን አዳምጥ እንጂ በሙዚቃ መሳሪያ ምናምን ኧረረ.........."
ይችን ይወዳል የ..............ልጅ ምን
የተናገረችው ነገር በጣም አናደደኝ ያዙኝ ልቀቁኝ (ውይ ብቻዬን ነኝ ለካስ)ዘራፍ.........እምቢ ለሚልኮን እምቢ..........ይህች የሚልኮን ልጅ የሚልኮን አልጋ ወራሽ(ሚልኮን ስል በቀጣይ በእሷ ዙሪያ ጽሁፍ ይጠበቅ)።
እናም ጨጓራዬ እየተቃጠለ፣አንጀቴ እያረረ ምን እንደምላት ማብሰልሰልን ተያያዝኩት🤔🤔🤔
አእምሮዬ ውስጥ የሚመጣው የዳዊት አምልኮ ሀገሬው ያከበረው ንጉስ ሆኖ ሳለ(በድሮ ግዜ ንጉስ እንደ አምላክ ነበር የሚታየው)ዳዊት ግን ክብሩን:ዝናውን፣ማንነቱን፣ንግስናውን ረስቶ፡ በጌታ መንፈስ ሰክሮ፡ሰው አየኝ አላየኝ ሳይል፡ እርቃኑን ጌታን እንዳመለከ ነው፦አእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሰው።
ከዚያም የሚቀጥለውን መልዕክት ላኩላት
"ስሚ ዳዊት ንጉሡ እንኳን እርቃኑን አምልኮት አይደል እንዴ..እንኳን እኔ።አልሆንልህ ብሎኝ፣ ሰው ይደነግጣል፣ይሸበራል፣ሰላሙን መንካት ይሆንብኛል ብዬ እንጂ አይደለም በሙዚቃ መሳሪያ በጦር መሳሪያ እንኳን እያንደቆደኩ ባመልከውስ...................
ሰው ዝም ብሎ ይከራከራል፤
ጌታን ለማምለክ ቅርፅ ያወጣጣል፤
አንዱ እንዲ ሲል አንዱ እንዲያ ይላል።
አምልኮ ለጌታ ነው ሰው ምን ነክቶታል፤
በመንፈስ ይሁን እንጂ አምላኬ ተቀብሎታል።....