...የእግዚአብሔር የምስክር ወረቀት...
የአዳም ቤተሰብ እግዜሩን አልፈልግም አለ። የተገፋ አምላክ ዳግም ከዚህ ቤተሰብ ጋር ቁርኝትን ሻተ። ከእርሱ ጋር የሚገናኙበትን ''የመስዋዕት ሥርዓት'' መስመር አበጀ።
በዚህም መሠረት በአንድ ወቅት አቤል እና ቃየን ለአምላክ የተገባውን መስዋዕት አቀረቡ። አቤል ትጉ አርብቶ-አደር ነው። የቤቱም ሁለተኛ ልጅ ነው። ቃየን ደግሞ ታላቅዬው ልጅ ነው፤ ጎበዝ አርሶ-አደርም ነው። ታዲያ ሁለቱም ከብዙ ልፋት በኋላ ያረሱትን እና ያረቡትን ፍሬያቸውን ያገኛሉ። ካገኙትም ፍሬ ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ዘመቱ። አምላክም ቁም-ነገር ይዞ በወቅቱ በቦታው ተገኝቷል። “አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ።”[ዘፍ 4፥4] ቃየንም “ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ፤”[ዘፍ 4፥3]
በቅጽበትም አምላክ መስዋዕታቸውን አሽትቶ ምላሽ ይሰጣቸዋል። ምላሹ ግን እጅግ አስደንጋጭ ነው።[😭😭] አምላክም የአቤልን ተቀብሎ የቃየንን አልተቀበልም!!🙄 እንደሁልጊዜዬ ብዙ መብሰልሰል፡ ብዙ በማሰብ መወጣጠር ጀመርኩኝ።[🙄🙄🙄] "ፍትሕ ባህሪው የሆነለት አምላክ እንዴት ኢ-ፍትሐዊ የሆነ ነገር ያደርጋል አልኩኝ።" ''አይ አይ የሆነ የተደበቀ ነገር'ማ ቢኖር እንጂ አምላክ እንዲህ አይደለም አልኩኝ!!!'' ሁለቱም ያላቸውን ነው ያቀረቡት! እግዚአብሔር ደግሞ ሰው የሌለውን ነገር የሚጠይቅ አምላክ አይደለም!
ታዲያ ለምን?!...
የምድር ፍሬው ቃየን ጥሮ፡ ግሮ ያመጣው ነው። ቃየን ሰርቋል የሚልም አላነበብኩም። እንዲያውም ጠንካራ አራሽ እንደነበረ አንበብቢያለሁ። ታዲያ ለምን አምላክ ቃየንን 'ወግድ' አለው። KJV የተሰኘው የእንግሊዝኛው ትርጉም ስለ አቤል መስዋዕት የእግዚአብሔርን ምላሽ ሲናገር:- እግዚአብሔር እንዳከበረው ያትትልናል!! በተቃራኒውም የቃየንን እንደተጸየፈው ይተርክልናል።
ለሰዓታት ጥናቴን ገታ አደረኩኝ። ስለዚህ ጉዳይ የሚተርክ ክፍል [ዕብ:-11v4] ላይ አገኘሁኝ። ነፍሴ እጅግ ሀሴት አደረገች። ብዙ ጊዜ የጌታን ቃል እያነበብኩኝ ጌታ ሊል የወደደው ምን እንደሆነ ስገነዘብ የሚወረኝን ሀሴት ልገልጠው አልችልም።
እንዲህ ነው የሆነው ዕብ :-11v4 ፍንትው አድርጎ የአቤል መስዋዕት የሚበልጥ እንደነበር ያስቀምጥልናል። ይህም “አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ...”[ ዕብ 11፥4]
[በእምነት] :- ለካ አቤልን እና ቃየንን የለያየቺው ቃል ይህች ቃል ናት።
አቤል በእምነት አቀረበ። አቤል የሚያቀርበው መስዋዕት እግዜሩን እንደማይመጥነው ያውቃል። አቤል መስዋዕቱ ብቁ እና አምላክን የሚያረካ እንደሆነ እና ደግሞ ለጌታ ውለታ እንደሚውልለት የሚያስብ ትዕቢተኛ የሆነ 'ልቦና' አልነበረውም። አንድ ነገር ግን ያውቃል:- አምላክ ሊረካ የሚችለው ወደፊት ስለ ሰው ልጅ ሁሉ [ስለ ራሱም፣ ስለ አቤልም] ሊያቀርብ ስላለው የእግዚአብሔር በግ[ኢየሱስ ክርስቶስ] ያምን ነበረ።
በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር አቤልን እና መስዋዕቱን አከበረ። እግዚአብሔር የመስዋዕት [የበግ፣ የምድር ፍሬ እና የመሳሰሉት] ጠኔ ያለበት አምላክ አይደለም። የመስዋዕት ሥርዓቱ ሰዎች ለአምላክ ያላቸውን ልባዊ መስዋዕትነታቸውን የሚገልጡበት ማሳያ ምልክት እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም።
ምድር እና ሞላዋ የእግዜሩ ናት። ታዲያ ይህ አምላክ የመስዋዕት ሥርዓት ያበጀው የራሱ ያልሆነን ነገር እንደማያመጡ ያውቃል። ነገር ግን አንድ ነገር ነበረ ናፍቆቱ:- [ከተሰዋ ማንነት ውስጥ የሚወጣ መስዋዕት] [ከታረደ ማንነት ውስጥ የሚወጣ የታረደ መስዋዕት]
ይኸው ነው የእግዚአብሔር ናፍቆት!!!
በመጨረሻም ስለስሙ የተሰዋን መስዋዕት ከማሽተት እና ስለመስዋዕቱ ምላሽ ከመስጠት ያልቦዘነ አምላክ ስለ አቤል መስዋዕት እንዲህ ብሎ መስክሯል:-“...በዚህም፥ እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል።”[ዕብ 11፥4]
ፍጹም ንፁህ የሆነ አምላክ ስለ አቤል ስጦታ ብሎ መሰከረ!!!
ምንም የማይሸሸግበት፣ ሁሉም ነገር በፊቱ እርቃኑን የሆነለት አምላክ ለአቤል ጻድቅ የሚል ሰጠው።
ተወዳጆች ሆይ ሰው የሚመሰክርልን ጥሩ ጥሩ ንግግራችንን፣ አካሄዳችንን እና ውጫዊ እንቅስቃሴዎቻችንን አይቶ ነው። ሰዎች ብዙ 'ቁሸታችንን' ሳያዩ ይመሰክሩልን ይሆን ይሆናል። እግዚአብሔር ግን እንዲያ አይደለም!! የማይታየው የህይወታችን ክፍል የለውም። ታዲያ በዚህ አምላክ ፊት ጻድቅ መባል ምን አይነት ዕድል ነው። አቤት አቤል ታድሎ!!!
ጌታ እንደ አቤል ከተሰዋ ማንነት ውስጥ የሚወጣን መስዋዕት ማቅረብ እንድንችል ይርዳን!
✍️ Tesfatsion Feleke
💐💐
@wengelbeArt 💐💐