ማህበራዊ ሚድያ ላይ ትችት በማቅረብ የሚታወቀው ሰመረ ካሳዬ (ሰመረ ባርያው) ታሰረ
በቅርብ አመታት ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚለቀቁ ቪድዮዎችን መነሻ በማድረግ ትችት እና ሽሙጥ በማቅረብ የሚታወቀው ሰመረ ካሳዬ (ሰመረ ባርያው) በትናንትናው እለት በፀጥታ አካላት አዲስ አበባ ውስጥ ተይዞ እንደታሰረ ታውቋል።
ሰመረ ትናንት እኩለ ቀን ገደማ ምሳ ከጓደኞቹ ጋር በልቶ እየወጣ በነበረበት ወቅት በፀጥታ አካላት ተይዞ ተወስዷል።
ሰመረ ብዙውን ግዜ ትችት የሚያቀርበው በማህበረሰቡ ዘንድ ጥያቄ በሚያስነሱ እና አነጋጋሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሆኖ ሳለ ለእስር መዳረጉ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ስራዎቹን በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሲያቀርብ እንደነበር ይታወሳል።
Via መሰረት ሚዲያ