ቢሮው በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በቅንጅታዊ አሰራር የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት ዕውቅና ሰጠ።
(ነሀሴ 7/2016 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ ከትምህርት ቢሮ ጋር የትስስር ሰነድ ተፈራርመው የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውኑ የቆዩ ተቋማትን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በቅንጅታዊ አሰራር እቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የትምህርት ልማት ስራ የሁሉንም ባለድርሻ ተሳትፎ የሚፈልግ ሴክተር በመሆኑ ቢሮው ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ ትውልድ ለመገንባት የሚያከናውናቸው ተግባራት ውጤታማነት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት የሚሰራቸው ተግባራት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።
ዶክተር ዘላለም አያይዘውም በ2016 ዓ.ም ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት በተከናወኑ ተግባራት በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው በ2017 ዓ.ም በቅንጅት ከመስራት አንጻር ከተወሰኑ ተቋማት ጋር የነበሩ ክፍተቶችን በመቅረፍ የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።