የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት "የላቀ ትጋት ለትምህርት ጥራትና ለሀገር ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል የትምህርት ጉባኤውን አካሄደ።
(ነሀሴ 30/2016 ዓ.ም) በፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ም/ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ዘሪሁን ሽፈርዳ እንደተናገሩት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን በእውቀትና በክህሎት እንዲዳብሩ በማድረግ ለሀገራቸው አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ማስቻል ዓላማቸው መሆኑን ገልጸው የተማሪዎችን ውጤት በማሻሻልና በሀገራቸው የብልጽግና ጉዞ ላይ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ በማድረጉ በኩል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የድርጅት ጉዳዮች ኃላፊ ወ/ሮ እጅጋየሁ አድማሱ በበኩላቸው በ2016 በጀት ዓመት በመማር ማስተማሩ ላይ በተሰራው ውጤታማ ስራ የተማሪዎች ውጤት ላይ መሻሻል የታየበት እንደነበር ገልጸው ሀገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን ተማሪዎች በእውቀትና በአመለካከት የዳበሩ እንዲሆኑ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብና ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
ጉባኤው የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የውጤት ትንተና እና የ2017 ዕቅድ ላይ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በ2016 በጀት ዓመት ጥሩ አፈጻጸም ላሳዩ ባለሙያዎች ፣ ቡድኖችና ወረዳዎዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።።