በአቃቂ ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል የመጀመሪያ ደረጃና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲማሩ የነበሩ የሕግ ታራሚዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመውስድ ውጤት ለማስመዝገብ ችለዋል፡፡
(መስከረም 8/2017 ዓ.ም) በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል በመደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ከነበሩ 21 የተፈጥሮ ሳይንስ የህግ ታራሚ ተማሪዎች መካከል ሰባቱ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችለውን ውጤት ማምጣት ችለዋል፡፡
የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል የመጀመሪያ ደረጃና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሳምሶን ወንድሜነህ የህግ ታራሚ ተማሪዎች ምንም እንኳ በህግ ጥላ ስር ቢሆኑ ትምህርታቸውን በአግባቡ ሲከታተሉ መቆየታቸውንና ለውጤት እንደበቁ ገልፀዋል፡፡
ተማሪ የህግ ታራሚዎቹ የመልቀቂያ ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀውን የሙከራ ሞዴል ፈተና መውሰዳቸው ለውጤታቸው አበርክቶ መኖሩን የተናገሩት የትምህርት ቤቱ የጋይዳንስና ካውንስሊንግ ባለሙያ አቶ ለይኩን ግርማ የተቋሙ የስነ ልቦና ባለሙያዎችም ድጋፍ እንዳደርጉላቸው ተናግረዋል፡፡
ታራሚዎችን በማረምና ማነፅ ሂደት ሁሉም ዜጋ ተሳታፊ መሆን እንዳለበት የጠቆሙት በቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል የማረምና ማነፅ ትምህርትና ስልጠና ማስተባበሪያ ተወካይ አቶ ታሪኩ ጋዲሳ ተማሪ የህግ ታራሚዎቹን የትምህርት ሚኒስቴርም ሆነ የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ያመጡት የህግ ታራሚ ተማሪዎች እንደሚሉት በማረሚያ ቤት ውስጥ በእርምት ላይ ሆነው ፈተናውን መውሰድ ከባድ ተፅዕኖ ቢኖረውም ውጤታማ መሆን ችለናል ብለዋል፡፡