የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን በብርሀን የአይነስውራን አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጉብኝት አካሄደ።
(ታህሳስ 7/2017 ዓ.ም) በጉብኝቱ የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ዶክተር ፍጹም አሰፋ (ዶክተር) ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በለጠ ሞላ(ዶክተር) እንዲሁም የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች የሱፐር ቪዥን ቡድኑ አባላት የተገኙ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እና በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ወይዘሮ አለም ከበደ አማካይነት ስለ አዳሪ ትምህርት ቤቱ ገለጻ ተደርጓል።
አዳሪ ትምህርት ቤቱ ለተማሪዎቹ በሚመች መልኩ ተገንብቶ ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ 312 ተማሪዎችን በመቀበል የትምህርት አገልግሎቱን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ለሱፐር ቪዥን ቡድን አባላቱ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ገልጸዋል።
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በህክምና መስጫ ክሊኒክ ፣ የመመገቢያ እና የመኝታ ክፍሎች፣የመማሪያ ክፍሎች ፣ የቤተ መጽሀፍ ክፍል ፣ የአይሲቲ ክፍሎች ፣ የመጸዳጃ ቤቶች ፣ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረጊያ ክፍሎችን ጨምሮ አጠቃላይ ምድረ ግቢውን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ትምህርት ቤቱ ለአይነ ስውራን ተማሪዎች ምቹ ሆኖ ከመገንባቱ ባሻገር በትምህርታቸው ውጤታማ መሆን እንዲችሉ የሚያግዙ ግብአቶችን አሟልቶ የመማር ማስተማር ስራውን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል።