የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በ6 ወራት ያከናወናቸዉ የቅንጅታዊ እና መደበኛ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ትምህርት ቢሮ ላበረከተው አስተዋጽዎ የእውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥቷል።
(ጥር 21/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በ6 ወራት ያከናወናቸዉን ቅንጅታዊ እና መደበኛ ስራ አፈፃፀሙን የቢሮዉ አመራሮችና ሰራተኞች ፤ የሴክተር ተቋማትና የክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ኃላፊዎች እና የሴክተር ክላስተር አስተባባሪዎች በተገኙበት ገምግሟል፡፡
የቢሮዉ ፅ/ቤት ኃለፊ ወ/ሮ ነፃነት አለሙ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ 6 ወራት ጊዜ ዉስጥ እቅድን የጋራ በማድረግ ተግባብቶ በፍጥነት ወደ ተግባር በመግባት በየደረጃዉ ካሉ መዋቅሮች ጋር በሁሉም የከተማዋ አጀንዳዎች ላይ ግንባር ቀደም ሆነን በቅንጅት በመስራታችን የተሻለ ዉጤት ማምጣት ችለናል ብለዋል፡፡ ኃላፊዋ አክለዉም በከተማችን የሚታየዉን ፈጣን እድገት የሚመጥን ወቅታዊ፤ ፈጣንና ጥራት ያለዉ መረጃን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለዉን መዋቅር በሁለተናዊ መልኩ በማዘመን እና ስታንዳርዱን በማሳደግ ተወዳዳሪ ተቋም ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት በጋራ የበለጠ አበክረን እንሰራለንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ቢሮዉ በበጀት ዓመቱ በቅንጅታዊ አሰራር የተሻለ አፈፃፀም ላመጡ ተቋማት የእዉቅና ምስክር ወረቀት ሽልማት ያበረከተ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ለነበረው በጣም ከፍተኛ አስተዋጽዎ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc