ሰላም የኢት- ዮጵ ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ??
ዛሬ ከጋሽ ስብአት ገ/እግዚአብሔር እግረ መንገድ የተቀነጨበች ስለ ምኞት አንድ ነገር ልላችሁ ፈለኩ። እነሆ በረከት ይሉ የለ
አሁንም ምኞት ብትሉ ንጉስ ሚዳስ ፣ዳዮኒስስ የተባለው አምላክ ''እንደ ምኞትህ ሰጥቼሀለው'' አለው። እና ምን ተመኘ ? ''የነካሁት ሁሉ ወርቅ ይሁን '' አለ ''ይሁን'' አለው አምላክየው። ድሀ እንኳን ቢሆን እሺ ንጉስን ያህል ሰው እኮ ነው ንጉስ ሚዳስ። ታዲያላችሁ ድንጋይ ሲያነሳ ድንጋዩ ወርቅ። የእንጨት ወንበር ላይ ሲቀመጥ ወንበሩ ወርቅ፣ ተገረመ፣ ሚዳስ ሆዬ ተደሰተ። ወርቅ በወርቅ ሆነ። ፈነጠዘ። ሆድ መቼስ ስለ ምግብ እንጂ ስለ ወርቅ ደንታ ስለሌለው ሰአቱ ሲደርስ ተራበ።
"ምሳ አቅርቡ" አለ ንጉስ። አቀረቡለት። ዳሩ ምን ይሆናል? ስጋውን ወርቅ! አዬ ጉድ! ሚዳስ ተራበ፣ ሚዳስ ተጠማ፣ ሚዳስ ተጨነቀ።
መች ይሄ ብቻ አትክልት ውስጥ ጭንቀቱንና ራሱን እያንጎራደደ በማሰላሰል ላይ እያለ ያቺ እንደ ነብሱ የሚወዳት ልጁ "አባዬ!" ብላ እየሮጠች መጣች እና ዘላ እቅፍ፤ ወርቅ፤ አዬ መአት! ሚዳስ እጅጉን አዘነ። ያ ሁሉ የልጁ ሙቀት ድምጽ እና ሳቅ ብጫ ብረት ሆኖ ቀረ። ወይ ጎዶሎ ቀን፣ ወደ አምላክየው ሄዶ " መልካም ፈቃድ ይሁን እና ወርቁ ይቅርብኝ " ሲል ጸለየ። ፖክቶሉስ ወንዝ ሂድና ታጠብ ተባለ። ታጠበ እና ዳነ። ለዚህ ነው እስከ ዛሬ ድረስ ፖክቶሉስ ወንዝ ውስጥ ወርቅ የሚገኘው።
ይሔን ታሪክ የምናገኘው እግረ መንገድ በተሰኘው መጸሀፍ ገጽ 190 ላይ ነው ጋሽ ስብአት ካለፉ በኋላ የታተመ ነው
ከታሪኩ እንደ ምንረዳው የሰው ልጅ ብዙ ነገር ይመኛል ሞኞት ደሞ ጥሩ ነው በትክክለኛው መንገድ ከሆነ አንዳንዴ አጉል ምኞትም ዋጋ ያስከፍላል። ተመኝተክ ሳይሳካ ሲቀር አንዳንዴ ለበጎ ነው በል ከኋላው ሌላ የተከለከለ ነገር ስለ ሚኖር🙏🙏
መልካም ቀን ተመኘን እኛም
©ፍራ ነኝ
@xobya
@xobya
@xobya
@telemondo
@kurazs