"ዖፅ በሚባል አገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ነበረ።"
መጽሐፈ ኢዮብ ፩፥፩
መስከረም አንድ ቀን
ታላቁ ጻድቅ የትእግስትም አባቷ ቅዱስ ኢዮብ በጭንቅ ደዌ ለብዙ ዘመናት በመከራ ከኖረ በኋላ በዚህች ቀን በፈሳሽ ውሃ (በዮርዳኖስ) ታጥቦ ሰውነቱ ታድሷል፤ ክብርም ተመልሶለታል። በፈሳሽ ውሃ የምንጠመቅበት አንዱ ምክንያትም ይኄው ነው።
የጻድቁ ቅዱስ ኢዮብ በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። አሜን።
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯