💛 የ መዝሙር ግጥሞች 💛 dan repost
✞ዘመነ ጽጌ✞
ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6
"ልጄን ከግብፅ ጠራሁት"
ት.ሆሴዕ ፲፩፥፩
ከመምህር ዮሐንስ ለማ
ክፍል አንድ
እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕግና ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው40 ቀን የእመቤታችንን እና የልጇን ስደትበማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች።ይህ 40ው ቀን የእመቤታችንና የጌታችን ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው።
ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታችን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡
በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሳው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አምሥቱን ጸዋትወ ዜማ ሲደርስ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሳው አባ ጊዮርጊስ ደግሞ ሰዓታትን ደርሷል፡፡
በዚሁ ዘመን ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ጥልቅ መንፈሳዊ ፍቅር የነበረው አባ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌ የተባለውን ድርሰት ደርሷል፡፡
ማኅሌተ ጽጌ ግጥማዊ አካሄድ ያለው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ሲሆን ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ ወቅት ተለይቶለት በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ የሚውለው ግን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና በልጇ የስደት ዘመን ማለትም ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው ዘመን ውስጥ ነው፡፡
በዚህ ወቅት በየሳምንቱ እሑድ ሌሊቱን በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ መሰደድና መንከራተት እየታሰበ በሊቃውንቱ የሚደርስ የምሥጋና ጸሎትም ነው።
ይህ ድርሰት በግጥም መልክ የተደረሰ ሲሆን በአብዛኛው አምስት ስንኞች ሲኖሩት ብዛቱም 158 ያክል ነው፡፡እመቤታችን ጣዕሟንና ፍቅሯን እንዲሁም ምስጋናዋን ሲናፍቁ የነበሩትን ቅዱስ ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን እንደገለጸችላቸው ሁሉ ለፍቅሯ ሲሳሳ ለነበረው ለአባ ጽጌ ድንግል ደግሞ ይህንን የማኅሌተ ጽጌን ድርሰት እንዲደርስ ምስጢርን ገልጻለታልች ።
በቅድስት ሐገር ሐገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የመስከረምና የጥቅምት ወራት የአበባ ወራት ወርኅ ጽጌ (ዘመነ ጽጌ) ናቸው።ይህም ወቅት ተራሮች በአበባ የሚያጌጡበትና ለዓይን ማራኪ የሚሆኑበት ጊዜ ነው፡፡
በዚህም ዘመን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ስለ ልብስ ስለምን ትጨነቃላችሁ ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፡፡አይደክሙም፣ አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡እግዚአብሔር፣ ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፣ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፣ እናንተንማ ይልቁን እንዴት፡፡ እንግዲህ ምን እንበላለን፣ ምንስ እንጠጣለን፣ ምንስ እንለብሳለን ብላችሁ አትጨነቁ።"ማቴ ፭÷፳፰-፴፫
በማለት የተናገረውን ቃል በማሰብ መጨነቅ የሚገባን መንግሥተ ሰማያት ለመግባት እንጂ በዚህ ዓለም ስላለው ነገር እንዳልሆነ ተራሮችን በአበባ ያለበሰ አምላክ በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረንን እኛን ለኑሮ የሚያስፈልገንን ምግብና ልብስ እንደማይነሳን እያሰብን የምንዘክርበት ወቅት ነው።
የሊቁ ድርሰትም ፍሬ ከአበባ÷ አበባም ከፍሬ እንደሚገኘ ሁሉ ማኅሌተ ጽጌም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመሰለ የሚ
ያስረዳ ድርሰት ነው።እርሷን በአበባ ሲመስል ልጇን በፍሬ እርሷን በፍሬ ሲመስል ልጇን ደግሞ በአበባ እየመሰለ ይናገራል
ነቢዩ ኢሳይያስ "ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ፣ ወየዓርግ ጽጌ እም ጕንዱ - ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፤ ከሥሩም ቁጥቋጦ ያፈራል።"ኢሳ ፲፩÷፩ብሎ ከእሴይ ዘር የምትገኘውን እመቤታችንን በበትር ፣ ከርሷ የሚገኘውን ክርስቶስን ደግሞ በጽጌ መስሎ ትንቢቱን ተናግሯል፡፡
አባ ጽጌ ድንግልም ድርሰቱን በዚሁ አንጻር በመቀመር እያንዳንዱን መልክዕ እመቤታችንንና ልጇን አስተባብሮ በጽጌና በፍሬ በመመሰል፣ ከዚያው በማያያዝ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ በምሥጢር፣ በታሪክ፣ በጸሎትና በመሳሰለው መልክ ድንቅ በሆነና በተዋበ ሁኔታ አዋሕዶ ደርሶታል።
ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ እመቤታችንን በአበባ እየመሰለ ከተናገረው ድርሰቱ መሐከል አንዱ "ማዕረረ ትንቢት ማርያም ዘዘመነ ጽጌ እንግዳ ወዘመነ ፍሬ ጽጋብ ዘዓመተ ረኃብ ፍዳ ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእምአውግሪሁ ለይሁዳ ፀቃውዐ መዓር ቅድው (ጥዑም) ወሀሊብ ፀዓዳ" በመከር ጊዜ አበባ፣ በአበባ ጊዜ ደግሞ መከር አዝመራ ማጨድና መሰብሰብ የለም፡፡ምክንያቱም ጊዜያቸው የተለያየ ስለሆነ።
ለምሳሌ በመስከረም ወር የአበባ ጊዜ በመሆኑ አዝመራ መሰብሰብ የለም፡፡ የትንቢት መከር መካተቻ የሆንሽ እንደ ዘመነ ጽጌ የረሃብን ዘመን ያስወገድሽ ማርያም ሆይ፣ የኤልዳ ነቢይ ኢዩኤል ከይሁዳ ተራሮች ጣፋጭ ማርና ፀዐዳ ወተት ይፈሳል ብሎ የተናገረው ትንቢት በአንቺ ታወቀ፣ ተፈጸመ።
እመቤታችን ነቢያት የተናገሩት የትንቢት ዘር ተፈጸመባት ማለትም ነቢያት የአምላክን ሰው የመሆን ነገር በተለያየ ሁኔታ ተናግረዋል።
ጌታችን ነቢያት የተናገሩት ትንቢት መፈጸሙንና ይህንን ፍጻሜ ለማየት የታደሉት ሐዋርያት መሆናቸውን "አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል"የሚለው ቃል እውነት ሆኗል፡፡
"እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኳችሁ።ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ።"በማለት ተናግሮአልዮሐ.፬÷፴፯-፴፰)፡፡
ይህም ነቢያት የዘሩት ትንቢት በሐዋርያት ዘመን ለአጨዳ ለፍሬ መድረሱን መናገሩ ነው።ስለሆነም "ማዕረረ ትንቢት"የትንቢት መካተቻ ማርያም አላት።
በሌላ በኩል ደግሞ ፍሬ ክርስቶስን ያስገኘችና ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች እየተባለ የተነገረላት በመሆንዋ ድንግል ማርያም በአበባ ትመሰላለች፡፡
ስለዚህ እመቤታችን በመከር ወራት የምትገኝ አበባ ናት።በመከር ጊዜ የአበባ መገኘት ያልተለመደ ስለሆነ "ወዘመነ ጽጌ እንግዳ "እንግዳ የሆነ አበባ አላት፡፡ ከዚህ በኋላ "ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ፣ ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእምአውጋሪሁ ለይሁዳ፣ ፀቃውዓ መዓር ጥዑም ወሀሊበ ፀዓዳ"በማለት ነቢዩ ኢዩኤል የተናገረውን ትንቢት አፈጻጸም ይናገራል፡፡
ነቢዩ ኢዩኤል በዘመኑ ጽኑ ረኅብ ነበር፡፡እግዚአብሔር ሕዝቡን በምሕረት እንደሚጐበኛቸውና ረሃቡ እንደሚጠፋ ይነግራቸው ነበር፡፡
"ብዙ መብል ትበላላችሁ÷ ትጠግቡማላችሁ፣ ከዚህ በኋላ እንዲህ ይሆናል፣ ተራሮች በተሃ ጠጅ ያንጠበጥባሉ÷ ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ÷ በይሁዳም ያሉት ፏፏቴዎች ሁሉ ውኃን ያጐርፋሉ"
ኢዩ ፫፥፲፰፣ ፪፥፳፮
ክፍል ሁለት ይቀጥላል....
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯