✞አይዞህ ዶኪማስ✞
አይዞህ ዶኪማስ ሆይ ቢያልቅም ወይን ጠጁ
እድምተኛው ቢጎርፍ ቢሞላ በደጁ
ንግሥቷ ስላለች በእድምተኛው መሃል
ያለቀው መጠጥህ ይጨመርልሃል
ወይኑ አለቀ ብለህ ስትጨነቅ በእፍረት
ሰውም ቢስቅብህ ቢያደርግህ ለተረት
የጠራኻት ንግሥት ልጇ ጋር ያለችው
ከእፍረት አዳነችህ ጋኑን እስሞላችው
አዝ= = = = =
ስድስቱ መጥመቂያ ተሟጥጦ ከስሩ
ዶኪማስ ደንግጦ ሲጓዝ በግንባሩ
የአማኑኤል እናት የክብር እንግዳ
አትረፈረፈችው ያለቀውን ጓዳ
አዝ= = = = =
የጓዳህ ስብራት ተጠግኖልሃል
ጎዶሎህ በሙሉ ዳግም ሞልቶልሃል
ተትረፈረፈልህ በደስታ ላይ ደስታ
ሠርግህ ላይ ስላለ የሠራዊት ጌታ
አዝ= = = = =
የተራቆታችሁ ጸጋችሁ ያለቀ
የሕይወታችሁ ወይን ዛሬም የደረቀ
የልባችሁ ስፍራ ይደልደል ይዘርጋ
ክፈቱ እና አስገቧት ንግሥቷን ልጇ ጋ
መዝሙር
በኮምቦልቻ ደብረ ምሕረት ቅ/ገ/ሰ/ት/ቤት
ዘርዓይ ደርቤ እና ብዙአየሁ ተክሉ
ዮሐ፪፥፩-፲፭
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
አይዞህ ዶኪማስ ሆይ ቢያልቅም ወይን ጠጁ
እድምተኛው ቢጎርፍ ቢሞላ በደጁ
ንግሥቷ ስላለች በእድምተኛው መሃል
ያለቀው መጠጥህ ይጨመርልሃል
ወይኑ አለቀ ብለህ ስትጨነቅ በእፍረት
ሰውም ቢስቅብህ ቢያደርግህ ለተረት
የጠራኻት ንግሥት ልጇ ጋር ያለችው
ከእፍረት አዳነችህ ጋኑን እስሞላችው
አዝ= = = = =
ስድስቱ መጥመቂያ ተሟጥጦ ከስሩ
ዶኪማስ ደንግጦ ሲጓዝ በግንባሩ
የአማኑኤል እናት የክብር እንግዳ
አትረፈረፈችው ያለቀውን ጓዳ
አዝ= = = = =
የጓዳህ ስብራት ተጠግኖልሃል
ጎዶሎህ በሙሉ ዳግም ሞልቶልሃል
ተትረፈረፈልህ በደስታ ላይ ደስታ
ሠርግህ ላይ ስላለ የሠራዊት ጌታ
አዝ= = = = =
የተራቆታችሁ ጸጋችሁ ያለቀ
የሕይወታችሁ ወይን ዛሬም የደረቀ
የልባችሁ ስፍራ ይደልደል ይዘርጋ
ክፈቱ እና አስገቧት ንግሥቷን ልጇ ጋ
መዝሙር
በኮምቦልቻ ደብረ ምሕረት ቅ/ገ/ሰ/ት/ቤት
ዘርዓይ ደርቤ እና ብዙአየሁ ተክሉ
ዮሐ፪፥፩-፲፭
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯