በእስልምና በወላጆች ላይ ሀራም የሆኑ ነገርግን አሁን ላይ ሲደረጉ የምንመለከታቸው ነገሮች
1. ልጆች ኢባዳ ላይ ሲሳነፉ ዝም ማለት
የአላህ መልእክተኛ ( ) እንዲህ ብለዋል፡-
“ልጆቻችሁ ሰባት አመት ሲሞላቸው እንዲሰግዱ አስተምሯቸው፣ 1ዐ ዓመትም ሲሞላቸው ካልሰገዱ (በቀላል) ቅጧቸው እና ብቻቸውን መተኛት ____ (እንዲጀምሩ) አድርጓቸው።''
ምንጭ᎓ አቡ ዳዉድ (495) እና አህመድ (6650
2. ልጆችን ከልክ ባለፈ ሁኔታ መቀጥቀጥ
ማንኛውም አይነት በልጆች ላይ የሚደረግ አካላዊ ጥቃት በእስልምና በጥብቅ የተከለከለ ነው። ይህ በተለይ በፊታቸው ላይ መምታት፣ መደብደብ ወይም በሀገራችን የምንሰማው በርበሬ ማጠን የተባለው አቀጣጥ በአላህ ያስጠይቀናል።
ነቢዩ () እንዲህ ብለዋል᎓
"ልጆቻችንን የማይምር ፣ ሽማግሌዎቻችንንም የማያከብር ከእኛ አይደለም"
[ጃሚ` አት-ቲርሚዚ 1920፣ ኪታብ 27፣ ሀዲስ 25]
3. የልጆችን ስሜት መጉዳት
ስሜታዊ ጥቃት እንደ አካላዊ ጥቃት በልጆች ላይ ጎጂ ነው። ልጆችን መስደብ፣ የራስ መተማመን ማሳጣት፣ ያለማቋረጥ መተቸት ወይም በልጆች ላይ አደብ የሌለው ቃላትን መጠቀም በልጆች ላይ ጎጂ ነው።
ስለዚህ የልጆችን አእምሮ መንካት በአላህ ያስጠይቀናል።
4. በልጆች መካከል ማበላለጥ
በልጆች መካከል አድልዎ ማሳየት በእስልምና በጣም የተጠላ ስራ ነው። ይህ በልጆች ላይ ስሜት መጎዳት፣ መቀናናት እና የቤተሰብ ግንኙነቶችን ሊያበላሽ ይችላል። የቤተሰቡ መጨረሻ ልጅ ቢሆን እንኳን በእኩል አይን መታየት አለበት።
የአላህ መልእክተኛም () በዚህ ሀዲስ እንዲህ ብለዋል፡-
“አላህን ፍሩ እና ልጆቻችሁን በእኩልነት ተመልከቱ።“
ምንጭ : ሳሂህ አል ቡኻሪ 2587፣ ኪታብ 51፣ ሀዲስ 26
5. ልጆችን በጋብቻ ላይ ማስገደድ
በእስልምና ልጆችን ያለፍላጎታቸው ወደ ጋብቻ ማስገደድ በጥብቅ የተከለከለ ነው። በሸሪዓው ህግ መሰረት ጋብቻው እንዲፀና ሁለቱም ወገኖች ነጻ ፈቃዳቸውን መስጠት አለባቸው።
ነብዩ () በዚህ ሐዲስ እንዲህ ብለዋል፡-
" አግብታ ምታቅ ሴት ካላማከሯት በቀር ለጋብቻ ሰጠት የለበትም። ድንግልም የሆነች ሴት ከእርሷ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር አታግባ።“
ምንጭ: ሳሂህ አል ቡኻሪ 5136፣ ኪታብ 67፣ ሀዲስ 72
5. የልጆችን ውርስ መብት መከልከል
በዲናችን ልጆችን የውርስ መብታቸውን መከልከል የተከለከለ ነው። ነገርግን ውርስ የሚከለክልበት ሦስት ምክንያቶች አሉ ፡-
1. ግድያ፡- ሆን ተብሎ የሚደረግ ግድያ ውርስ የሚከለክልበት ምክንያት እንደሆነ በሁሉም ኡለማዎች የተስማማ ነው።
2. ባርነት፡- ድሮ የባርነት ነት ሥርዓት በነበረበት ዘመን አንድ ሰው ባሪያ ከነበረው ይሄ ባሪያ ንብረቱን መውረስ አይችልም ነበር።
3. ወራሹ እና ሟቹ ዘመድ የተለያየ እምነት ያላቸው ከሆነ መውረስ አይችልም።
ገ. ኢስላማዊ ያልሆኑ ተግባራትን ማስተማር ወይም ማበረታታት
ወላጆች ለልጆቻቸው ኢስላማዊ አስተምህሮትን የሚቃረኑ ነገሮችን ማስተማር ወይም እንዲያደርጉ መፍቀድ የለባቸውም። ይህንንም ሚፈቅዱ ከሆነ በእስልምና የተከለከሉ ተግባራትን መዳፈር እንዲሁም ከቀጥተኛው መንገድ ሊያስታቸው ይችላል፡፡
ወላጆች ልጆቻቸውን በእስልምና ህግጋት መሰረት ትክክል የሆነውን ነገር እንዲያደርጉ መምራት እና ኢስላማዊ እሴቶችን የሚከተሉበት ቤት መፍጠር አለባቸው።
8. ልጆችን መዋሸት
ታማኝነት የእስልምና ዋና እሴት ነው እና ወላጆች ይህንን ለልጆቻቸው በማስተማር ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።
ልጆች ወላጆቻቸውን በመመልከት ይማራሉ ስለዚህ ወላጆች ሁልጊዜ እውነተኞች በመሆን ልጆቻቸው እውነትን እንዲከተሉት ጠንካራ ምሳሌ መሆን አለባቸው።
ትናንሽ ውሸቶች እንኳን ልጆች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል ስለዚህ ለልጆች ሁልጊዜ እውነቱን መናገር አስፈላጊ ነው። ይህ በቅንነት እና በመልካምነት የተሞላ ቤት ይፈጥራል።
9. ብቻቸውን እንዳይሆኑ መከልከል
ልጆች እያደጉ ሲሄዱ ብቻቸውን መሆን ያዘውትራሉ እና ይህንንም ወላጆች ከእስልምና ትምህርቶች ጋር ማመጣጠን አለባቸው፡፡ ለልጆች የግላቸውን ቦታ መስጠት በራሳቸው ላይ ያለውን እምነት ያጎለብታል፣ ከቤተሰባቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በመናፈቅ ጥሩ ያደርገዋል እንዲሁም ኃላፊነት እና ለራሳቸው ክብርን እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል።
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከምታስፈቅዱና በባለቤቶቿ ላይ ሰላምታን እስከምታቀርቡ ድረስ ከቤቶቻችሁ ሌላ የኾኑን ቤቶች አትግቡ፡፡ ይህ ለእናንተ መልካም ነው፡፡ እናንተ ተ ትገነዘቡ ዘንድ (በዚህ ታዘዛችሁ)፡፡'
ሱረቱ አን ኑር 24:27
10. በሙያ ምርጫቸው ላይ ማስገደድ
የወላጆች መመሪያ አስፈላጊ ቢሆንም ልጆች ከአቅማቸው ውጪ ወደሆኑ ሙያዎች ማስገደድ በእስልምና የተጠላ ተግባር ነው። ወላጆች ልጆቻቸውን ከችሎታቸው እና ከፍላጎታቸው ጋር ወደሚስማማ ሙያ መምራት አለባቸው ይህም በስራቸው እርካታን እንዲያገኙ ያስችላል።
ይህን ልጆች ላሏቸው ወንድሞች እና እህቶቻችን ሼር በማድረግ እናሳውቃቸው። ልጆች ለሌለንም saved message ውስጥ እናስቀምጠው ኢንሻአላህ ልጅ ይኖረን ይሆናል።
“አስታውስም፤ ማስታወስ ምእመናንን ትጠቅማለችና።
[ሱራቱ አዝ-ዛሪያት 51:55]
ነቢዩ () እንዲህ ብለዋል: “አንድን ሰው ወደ መልካም ነገር የመራ ሰው ከመራው ሰው እኩል ምንዳ አለው (ምንም ሳይቀንስበት)።*
[ሳሂህ ሙስሊም 1893]
@yasin_nuru @yasin_nuru